ምክር ቤቱ ጋዜጠኞች ሚመዘግባቸዉ እውቅና ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ፣ ፍረጃዎችን ለማስቀረት፣ ከጥቃት ለመከላከል እና ጥቃት ሲደርስባቸው ለመከላከል እና ጥብቅና ለመቆም የሚያስችል መሆኑ ጠቁሟል።

ባለሥልጣኑ ያወጣው መግለጫ ገፅታዬን የሚያበላሽ ነው ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ገለጸ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ‘ምክር ቤቱ ለሚመዘግባቸዉ ጋዜጠኞች እዉቅና አልሰጥም፤ ኃላፊነቱም አደለም’ ሲል በትናንትናው ዕለት ያወጣው መግለጫ ገፅታዬን የሚያበላሽ ነው ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በአዋጅ ደረጃ ጋዜጠኞችን የመዝገብ እና እውቅና የመሰጠት ሕጋዊ ኃላፊነት እንደተሰጠው አስታውቋል፡፡የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ምዝገባ፣ የሙያ ማረጋገጫ እና በብሔራዊ ሚዲያ ሽልማት እውቅና ዙሪያ ያተኮረ አውደ ጥናት መጋቢት 9 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ማካሄዱ ይታወሳል። በዚህም መድረክ ላይ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ዓለም ዓቀፍ የሙያ ምስክርነትን የሚያረጋግጥ አንድ ወጥ መታወቂያ ሊያዘጋጅ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ይህም ጋዜጠኞች እውቅና ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ፣ ፍረጃዎችን ለማስቀረት፣ ከጥቃት ለመከላከል እና ጥቃት ሲደርስባቸው ለመከላከል እና ጥብቅና ለመቆም የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል። ከዚህም ጉዳይ ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት፤ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን “ምክር ቤቱ ጋዜጠኞችን ወይም የሚዲያ ባለሙያዎችን የመመዝገብም ሆነ የሙያ ማረጋገጫ የመስጠት ተግባርና ኃላፊነት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1239/2013 አልተሰጠውም” ያለ ሲሆን፤ በመሆኑም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለዚህ የምክር ቤት ተግባር እውቅና የማይሰጥ መሆኑን ማስታወቁን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል።
ከመግለጫው ጋር በተያያዘ፤ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤቱ የባለሥልጣኑ መግለጫ አግባብነት የጎደለውና፣ ግልጽ ያልሆነ፣ ገፅታን የማጠልሸት ድርጊት እንደሆነና በንግግር የሚፈቱ ጉዳዮች በመግለጫ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮች ሊኖሩ እንደማይችል ጠቁሟል። በተጨማሪም ለምክር ቤቱ ግልጽ ያልሆነና አጭር ደብዳቤ እንደተጻፈበት አንስቷል። “ባለሥልጣኑ ከምክር ቤቱ ጋር ያሉ አለመግባባቶችን በመነጋገር መፍታት እየተቻለ በሌላ ወገን ያሉ ሐሳቦችን አካታች ሳያደርግ የሚወጡ መረጃዎች፤ የጋዜጠኞች የሙያ ማንነት ምዝገባ እና እውቅና ማረጋገጫ ፅንስ ሐሳብ ካለመረዳት የመነጨ መግለጫ አውጥቷል” ሲልም ወቅሷል፡፡በተጨማሪም ውይይት ሳይደርግ መሰል መግለጫዎችን ፣ ይፋ ማድረግ አግባብ እንዳልሆነ ምክር ቤቱ አጽንኦት ሰጥቷል።
ፅንሰ ሐሳቡ መሰል ችግሮችን ለመፍታት ኹነኛ የመፍትሔ መንገድ እንደሆነም አስረድቷል። እንዲሁም፤ የሙያ ማንነት ምዝገባና እውቅና ማረጋገጫ ሐሳብ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት ከባለሥልጣኑ ጋር ውይይትና በፊርማ ደረጃ ስምምነት ተፈፃሚ ተደርጎ ወደትግበራ መገባቱን አስታውሷል። ከዚህ ቀደም የነበሩ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች ስለጉዳዩ በቂ ግንዛቤ ያላቸው ቢሆን፤ አዲስ ኃላፊነት ላይ ያሉት ግን መሰል ግንዛቤ ባለመኖሩ የተፈጠረ ክስተት ሆኖ ሊታመን እንደሚችል ገልጿል። ለጉዳዩ በመግለጫ መልኩ ምላሽ ለመስጠት ከባለሥልጣኑ ጋር ውይይት ለማድረግ መታቀዱንም ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡ሽልማትንና እውቅናን በተመለከተ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የገለጸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት፤ እቅዱ ወደ ሥራ ከመገባቱ በፊት አባላት መካከል ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖር ለማድረግ ከመገናኛ ብዙኃን ባለቤቶች ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር በዛሬው ዕለት የመጨረሻ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቋል።
(ወልደሐዋርያት ዘነበ – አሐዱ) @ Ahadu TV / አሐዱ ቴሌቪዥን’s Post
Climate on the Brink: Mapping the Deadly Nexus of Droughts, Displacement, and Violence in the Horn of Africa
Addis Ababa, Ethiopia— April 25, 2025, EMMA NEWS; Investigative Climate and Conflict News Analysis by Ayele Addis Ambelu “We used to predict the rains by the moon. Now, even the moon is silent,” says Halima, a pastoralist from Garissa, Kenya. In Mogadishu, displaced youth cite conflict over wells as their biggest fear. In Ethiopia’s Somali […]