Skip to content
• ዜና
• ፖለቲካ
• ንግድ
• ጤና
• ስልጣኔ
• አካባቢያዊ
• መዝናኛ
• የኢትዮጲያ ቆንጆ
• የኢትዮጲያ ሙዚቃ
• የኢትዮጲያ ድራማ
• ልዩ ዕትም
• ምርጫ እና ዲሞክራሲ
• ሰብዓዊ መብት
• ኢመብድ
• ስፖርት
• ራዲዮ እና መክስተትርዒት
• ጉብኝት
• ዕድሎች
• የትምህርት ዕድል
• የስራ ማስታወቂያ
• የተለያዩ ስልጠናዎች
• ኢመብድ ሽልማት
• AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
• ትምህርቶች
• ጋዜጠኝነት
• የሚዲያ ጥናት
• የህዝብ ግንኙነት
• የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
• የጥበብ ትምህርት ቤት
• Afaan Oromoo
• Tigrinya (ትግርኛ)
• Advertising and Media Services
• Radio Service
• TV & Digital
• EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
• ዜና
• ፖለቲካ
• ንግድ
• ጤና
• ስልጣኔ
• አካባቢያዊ
• መዝናኛ
• የኢትዮጲያ ቆንጆ
• የኢትዮጲያ ሙዚቃ
• የኢትዮጲያ ድራማ
• ልዩ ዕትም
• ምርጫ እና ዲሞክራሲ
• ሰብዓዊ መብት
• ኢመብድ
• ስፖርት
• ራዲዮ እና መክስተትርዒት
• ጉብኝት
• ዕድሎች
• የትምህርት ዕድል
• የስራ ማስታወቂያ
• የተለያዩ ስልጠናዎች
• ኢመብድ ሽልማት
• AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
• ትምህርቶች
• ጋዜጠኝነት
• የሚዲያ ጥናት
• የህዝብ ግንኙነት
• የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
• የጥበብ ትምህርት ቤት
• Afaan Oromoo
• Tigrinya (ትግርኛ)
• Advertising and Media Services
• Radio Service
• TV & Digital
• EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now

Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
• Home
• General

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

• AFRICA
• General
• Investigative Reports
• Latest
• Magazine
• News
• TOP STORIES

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

Ayele Addis September 8, 2026September 8, 2026

የአንድን ዓመት ታሪክ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱን ቀጣይ አቅጣጫ የሚወስኑ ጥያቄዎችን አስቀርተዋል፡፡

2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅጣጫ፣ የኢኮኖሚ መዋቅር፣ የሰላም ጥያቄ፣ የቀጠናዊ ተፅዕኖ እና የዜጎች የኑሮ ሁኔታ በአንድ ዓመት ውስጥ በተደጋጋሚ የተፈተኑበት የተለየ ዓመት ነበር። አንድ ዓመት፤ ብዙ ድሎች፣ ብዙ ቁስሎች፣ እና ለ2019 የተሻገሩ ከባድ ጥያቄዎች አልተጠናቀቁም። ኢትዮጵያ ከምርጫ ወደ ብሔራዊ ምክክር፣ ከጦርነት ወደ ጦርነት፣ ከአስተዳደራዊ ኢኮኖሚ ወደ ገበያ ተኮር ማሻሻያ፣ ከውስጣዊ ፖለቲካ ወደ ቀይ ባሕርና የቀጠናዊ ኃይል ፖለቲካ ተሻግራለች።2018 ዓ.ም. የቀውስ ታሪክም ነው። የልማት ዓመት ብቻ አይደለም፤ የኑሮ ጫና የተሰማበትም ዓመት ነው። የሰላም ጥሪ ተሰምቷል፤ በተመሳሳይ ጊዜ የጦርነት እሳት በተለያዩ አካባቢዎች እየነደደ ነው።

አንድ ዓመት ሊያልቅ ነው። ግን የ2018 ዓ.ም. ጥያቄዎች አልተጠናቀቁም።

ኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም.ን እንደዳመነ፣ የስሜኑ አለመረጋጋት ለአራትኪሎው መንበር እንዳስጨነቅ፣ ለአፍሪካ ዲፕሎማሲ ግራ ገብ፣ ለአውሮፓ እና አሜሪካዎች በተለይ ትግራይ ሁኔታው ጅሮ ገብ፣ 7ኛው ሐገራዊ ምርጫ የመንግስት የማጫዎቻ ሜዳ ስፋት ፣ ጥልቀት ፣ ፈቃደኝነት ብዙ አይኖችን ስቦ 2017 ለ2018 ተሻገረ፡፡  ኢትዮጵያም  በታላቅ ፖለቲካዊ ውጥረት ቀጠለች፤ በምርጫ፣ በብሔራዊ ውይይት፣ በኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በጦርነትና በዲፕሎማሲ መካከል ተጓዘች።

የዓመቱ ታሪክ በአንድ ቃል አይገለጽም። ድልም አለ፤ ቀውስም አለ። ዕድገትም አለ፤ የኑሮ ጫናም አለ። የሰላም ጥሪም አለ፤ የጦርነት እሳትም እየነደደ ነው፡፡ አየለ አዲስ ነኝ፡፡  እነሆ 2018 ዓ.ም.ን የተለየ ዓመት ያደረጉት 18 ትልልቅ ክስተቶች እንተነትናል አብራችሁን ቆዩ ፣ ከገፃችን ጋር ተዋሃዱ፤ መንግስትን ካልፈራን ሳናደላ እውነቱን ብቻ እየነገርናችሁ ለ2019 የመረጃ ምንጭ ለመሆን እንጥራለን። ግን እንፈራለን፡፡

2018 ለኢትዮጵያ ደግ አመት ነው የተባለበት ክስተት  የቀደሞው ጠቅላይ ሚንስትር የወጠኑት ሃይለማርያም ደሰላኝ አስጉዘውት ፣ አብይ ያገባደዱት እና ሪባን ለመቁረጥ የታደሉበት  የህዳሴ ግድብ ተመረቀ ፡፡ የኢትዮጵያ ትልቁ የልማት ምልክት ወደ እውነት ተለወጠ፡፡

2018 ዓ.ም. ከጀመረ ጥቂት ቀናት በኋላ፣ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም.፣ ኢትዮጵያ የታላቁን የህዳሴ ግድብ በይፋ መረቀች።

የግድቡ አቅም 5,150 MW የሚደርስ ሲሆን ኢትዮጵያ ይህንን ፕሮጀክት የኢኮኖሚ ልማትና የኃይል ነፃነት መሠረት አድርጋዋለች።

ግን የግድቡ ታሪክ እዚያ አያበቃም። ግብፅና ሱዳን የውሃ ደህንነት ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። አሁንም ሰሜ ጅሮ ከአቢሲኒያ ህዝቦች ቢያጡም የውስጥ ፖለቲካ አጀንዳ ማራገቢያ ከመሆን ርዕሱን አላወረዱትም፡፡

ስለዚህ ግድቡ የኃይል ፕሮጀክት ብቻ አይደለም፤ የናይል ዲፕሎማሲ የሚቀጥልበት አዲስ ምዕራፍ ነው።

ሁለተኛው ክስተት ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ኛው አጠቃላይ ምርጫ ተካሄደ። የምርጫ ቦርድ ሂደቱን በአዲስ የቴክኖሎጂና የአስተዳደር አቅም ለማካሄድ ሞክሪያለሁ ብሏል። ቀድሞ የተወሰነ በሚመስል ስሌት ገዥው ብልፅግና በብቸኛነት አብላጫ እጩ አቅርቦ ፣ ራሱ ደግሶ ፣ ራሱ የተሸለመበት ፣ ተቃዋሚዎች ልባቸው እንዳይጋ ለአንዳንዶቹ በቸርነት ቦታ የለለቀበት አመት ነበር፡፡  የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ የፓርላማ ብልጫ አግኝቶ የመንግሥት የፖለቲካ ቁጥጥርን አጠናከረ። ግን የምርጫው ውጤት ብቻ የዓመቱ ጥያቄ አይደለም። የምርጫ ውጤት የፖለቲካ ሥልጣንን ሰጠ፤ ግን የፖለቲካ ሕጋዊነት፣ የተቃዋሚዎች ተሳትፎና የተቋማት ነፃነት ጥያቄ አሁንም ቀጥሏል።

ሶስተኛ የሀገሪተቱ ክስተት ብሔራዊ ምክክር ያለቸውን ሁነት  ኢትዮጵያ ጠመንጃ እንደታጠቀች  ወደ ጠረጴዛ  የተመለሰችበት ክስተት ነው?

ከዓመቱ በጣም ትልቁ የፖለቲካ ሙከራ አንዱ የብሔራዊ ምክክር ነበር።

ከሐምሌ 15 ጀምሮ ወደ 4,000 የሚጠጉ ተሳታፊዎች ለ40 ቀናት በሀገሪቱ የሚገኙ ትልልቅ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የተቋማዊ ጉዳዮችን መክረዋል።

ስምንቱ ዋና የውይይት አጀንዳዎች ላይም ስምምነት መድረሱ ተገልጿል። አዋዘጋቢ የሆነ ያልተፈረመበት ዘጠነኛ አጀንዳ ፣ በኦሮሞ አሰተሳሰብ አዲስ አበቤ አካሌ ናት ፤ ሌላውን ከአካሌ ዞር በል የሚል ትዕይንት አስተናግዶ ፣ ኢትዮጵያውያንን የኦሮሞ ፖለቲከኞች እንደሚሉት ኮንፊዩዝ (ወይም ግራ ያጋባ) አጨራረስ ላይ ቆመ፡፡ ተሰታፊዎች እንደሚተቹት ኮሚሽን ባልተሰጠው ስልጣን ፣ ሂደቱን በሻረ ሁኔታ አጨራረሱን አበላሸ፡፡ ያልፈረሙበትን አጅንዳ ያገባኛል ብሎ አነበበ፡፡ ግን ትልቁ ጥያቄ አሁን ይጀምራል፦

ባልፈረሙበት የውይይት ሰነድ፣ የብሄረ ብሄረሰቦች ናት ራሷን የቻለች አዲስ አበባ ትቀጥላለች ወይስ እንደኦረሙማ ፖለቲከኞች ፍላጎት የፖለቲካ ማረጋጊያ እና የስልጣን መተማመኛ ያሏት አዲስ አበባ ትወረሳለች፡፡  የብሄር ብሄረሰቦች ድምፅ ወደ ተግባር ይቀየራል? ወይስ ታሪክ የሚያስታውሰው ሌላ የፖለቲካ ሰነድ ብቻ ይሆናል?

አራተኛው ክስተት  ትግራይ — የፕሪቶሪያ ሰላም እንደገና ተናወጠ

የ2022 የፕሪቶሪያ ስምምነት ጦርነትን አቁሞ ነበር። ግን 2018 ዓ.ም. የሰላሙ መሠረት እንደገና ማናወጡን ፣ አለመረጋጋቱን አሳየ።

በሚያዝያ 2026 የትግራይ ሕዝባዊ ነፃነት ግንባር የቅድመ፤ጦርነት የክልሉን አስተዳደር ለመመለስ እንደሚፈልግ ገለጸ፤ Reuters ይህንን የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚያሰጋ እርምጃ ብሎ ዘግቧል።

ከ2026 ጀምሮ የታዩ የታጠቁ ግጭቶችም የሰላሙን ደካማነት አሳይተዋል።

ጦርነት ቆሟል፤  አገርሽቷል፣  ወይስ እንደሰሜናዊቷ ኮከብ መቀሌ ፖለቲከኞች አሁንም አዲስ ፖለቲካን ለመመለስ ተንቤን ድርስ የሚያሽሽ ሁኗል፡፡ 2018 ለ2019 ያሸጋገረው ሌላ እዳ ነው?

ይህ የ2019 ዓ.ም. ትልቁ ጥያቄ ሊሆን ይችላል።

አምስተኛው አስፈሪ እውነት አማራ እና አማራ ላይ  የጦርነት ጥላ አልተወገደም፡፡

በአማራ ክልል የፋኖና የመንግሥት ኃይሎች ጦርነት በ2018 ዓ.ም.ም ቀጥሏል።

ይህ ግጭት የሰው ሕይወት፣ የጤና አገልግሎት፣ ትምህርት፣ ገበያና የመንግሥት አገልግሎትን በስፋት እየጎዳ ነው። Reuters ቀደም ሲል በግጭቱ ውስጥ በሲቪሎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን ዘግቧል።

በ2018 ዓ.ም. ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ከኤርትራ ወደ አማራ ታጣቂዎች ተላከ ያለውን 56,000 ጥይቶች መያዙን ገለጸ፤ ኤርትራ ግን ክሱን አስተባብላለች።

ይህ ግጭቱ ከአካባቢያዊ ችግር በላይ ወደ ክልላዊ ደህንነት ጉዳይ ተቀይሯል ፤ መንግስትም ድንበር ተሻጋሪ እና በክልል የማይቆም  አስጊ ምልክት ነው ሲል የአስቸኳይ አዋጅ እንደነበር ባለፉት አመታት ይታወሳል።

ስድስተኛው ክስተት ኦሮሚያ — የረጅም ጊዜ የጸጥታ ቁስል ሁና ቀጥላለች፡፡

በኦሮሚያ የተለያዩ የታጠቁ ግጭቶች የ2018 ዓ.ም. የሀገሪቱን የጸጥታ አጀንዳ አስቸጋሪ አድርገዋል።

ይህ ሁኔታ በአካባቢዎች የመንግሥት አገልግሎት፣ የንግድ እንቅስቃሴ፣ የሰብዓዊ ደህንነትና የልማት ሥራዎችን ይፈትናል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር አሁንም በጠመንጃ እየተፈታ ከሆነ፣ የብሔራዊ ውይይቱ ስኬት ምን ያህል ይሆናል?

ሰባተኛው ክስተት  ኢትዮጵያ እና ኤርትራ: የ2018 ዓ.ም. አዲሱ የጦርነት ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡

አንድ ወቅት የሰላም ሽልማት የተቀበለው መንግስት አሁን  የኢትዮጵያ–ኤርትራ ግንኙነት እንደገና ወደ ውጥረት ተመለሷል።

የባህር በር ጥያቄ፣ የትግራይ ጉዳይና የድንበር ደህንነት ጉዳዮች የሁለቱን አገሮች ግንኙነት እንደገና ውጥርት እና ጭንቀት ታይቶበታል። Reuters በጥር 2026 የሁለቱ አገሮች የጦርነት ንግግር እየጨመረ መምጣቱን ዘግቧል።

2018 ዓ.ም. ኢትዮጵያ አንድ እውነትን አሳያታለች፦ የቀድሞ ሰላም ማለት የዘላቂ ሰላም ዋስትና አይደለም።

ስምንተኛው ሁነት የቀይ ባሕር ጥያቄ ፤ “ወደ ባሕር መመለስ” አዲሱ የሀገር ስትራቴጂ ሁኖ ተመዝግቧል፡፡

ኢትዮጵያ ከባሕር የተለየች አገር መሆኗን በመጠቀም የባህር በር ፍላጎቷን እየገፋች ነው።

ይህ ጉዳይ ከንግድና ከወደብ ችግር በላይ ሆኖ ወደ የደህንነትና የብሔራዊ ሉዓላዊነት አጀንዳ ተሸጋግሯል።

በተመሳሳይ ጊዜ ቀይ ባሕርና የአፍሪካ ቀንድ የአለም ኃያላን የስትራቴጂ መድረክ እየሆነ ነው።

የባህር በር ጥያቄ 2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ፖሊሲ ፈተና ሊሆን ይችላል።

ዘጠነኛው ክስተት  የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ፤ ታላቅ ማሻሻያ፣ ከባድ ዋጋ ንረት የፈጠረው የዜጎች የህይዎት ጫና ነው፡፡

2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከአስተዳደራዊ ቁጥጥር ወደ ገበያ፤ተኮር ሥርዓት የሚሸጋገርበት ሂደት ተጠናከረ።

የውጭ ምንዛሪ ገበያ፣ የወለድ ፖሊሲ፣ የግል ዘርፍና የዕዳ ማሻሻያ የኢኮኖሚውን መልክ እየቀየሩ ናቸው። IMF ማሻሻያዎቹ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛኖችን እያሻሻሉ እንደሆነ ገልጿል።

World Bank ደግሞ በ2026 የኢኮኖሚ ሁኔታዎች መሻሻል፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢ፣ ሪዘርቭ እና የድህነት ምልክቶች መሻሻል መኖሩን ገልጿል።

ግን የኢኮኖሚ ቁጥሮች ከቤተሰብ ማዕድ ጋር ተመሳሳይ ናቸውን?

ይህ ጥያቄ አሁንም ልጆቻችንን ትምህርት ቤት ለመላክ እና ማዕድ ለመቋጠር ፈትኖናል የሚሉ በዝተዋል።

አስረኛው የብር ዋጋና የውጭ ምንዛሪ፤ አዲሱ የኢኮኖሚ ጦርነት ሁኖ ተመዝግቧል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ገበያ ማሻሻያ አንድ በኩል የገበያ እውነታን ለማስተካከል ተብሎ ተጀምሯል፤ በሌላ በኩል ግን ለዋጋ ግሽበትና ለዜጎች የግዢ አቅም ፈተና ፈጥሯል።

IMF በ2026 የኦፊሴላዊና የጥቁር ገበያ የምንዛሪ ልዩነት መቀነሱን ገልጿል፤ ግን የውጭ ምንዛሪ ገበያው ሙሉ በሙሉ ነፃና የተረጋጋ አለመሆኑንም ጠቁሟል።

ማሻሻያው በኢኮኖሚ መጽሐፍ ላይ ድል ሊመስል ይችላል፤ በገበያ ዋጋ ግን የሚለካው በዜጎች የኑሮ ሁኔታ ማሽቆልቆል ጭምር ነው።

አስራ አንደኛው የዕዳ ቀውስ ፤ ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር በአዲስ ውይይት ላይ ናት፡፡

2018 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳዋን መልሶ ለማዋቀር ከፍተኛ ጥረት ያደረገችበት ዓመት ነበር።

በ2025 ከOfficial Creditor Committee ጋር የተደረሰው ስምምነት ከ$3.5 ቢሊዮን በላይ የዕዳ እፎይታን ያካተተ ሲሆን፣ በ2026 የ$1 ቢሊዮን Eurobond መልሶ ማዋቀር ጉዳይ ወደ አዲስ ደረጃ ደርሷል።

ይህ ምን ያሳያል?

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብቻውን የዕዳ ችግር እየፈታ አይደለም፤ የዓለም የዕዳ ሥርዓትንም እየፈተነ ነው።

አስራ ሁለተኛው ክስተት የIMF ፕሮግራም ፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ መንገድ መከተል ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከIMF ጋር ያላት የ$3.4 ቢሊዮን የአራት ዓመት ፕሮግራም በ2018 ዓ.ም. በተግባር ቀጥሏል።

በሰኔ 2026 IMF የአምስተኛው ግምገማ ላይ የሰራተኞች ደረጃ ስምምነት መድረሱን ገልጾ፣ ወደ $468 ሚሊዮን የሚጠጋ ተጨማሪ ፋይናንስ ሊከፈት እንደሚችል ገልጿል።

ይህ የውጭ እምነትን ሊያጠናክር ቢችልም፣ የማሻሻያው ዋጋ ለዜጎች ምን ያህል ነው የሚለው ጥያቄ አለ። ዜጎችም በከፋ ድህነት እንደከተታቸው የሚያሳይ ነው፡፡

አስራ ሶስተኛው የግብርና ለውጥ ፤ ኢትዮጵያ ከእርዳታ ወደ ምርት ልትሸጋገር ትችላለች? የተባለበት ነው፡፡

ግብርና አሁንም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋና መሠረት ነው። World Bank ወደ 70% የሚጠጋው የሥራ ኃይል ከግብርና ጋር የተያያዘ መሆኑን ይጠቁማል።

በ2018 ዓ.ም. ስንዴ፣ የምግብ ዋስትና፣ የመስኖ ልማትና የግብርና ምርታማነት በልማት አጀንዳው ውስጥ ትልቅ ቦታ ያዙ። የግብርና ሚኒስቴርም ስንዴን ከቀዳሚ የሀገር ምርቶች መካከል አስቀምጦታል።

ግን የምግብ ምርት መጨመር ብቻ በቂ ነው? ወይስ የምግብ ዋጋን ዝቅ ማድረግም ያስፈልጋል? የሚለው ለመሪዎች መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፡፡

አስራ አራተኛው ክስተት ዲጂታል ኢትዮጵያ ፤ ገንዘብ ከኪስ ወጥቶ ወደ ስልክ የተለወጠበት አመት ነው፡፡

የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በ2018 ዓ.ም. ከፍተኛ ፍጥነት አሳይቷል።

National Bank of Ethiopia አዲሱን National Digital Payments Strategy 2026–2030 “BRIDGE 2030” በማስተዋወቅ ወደ የበለጠ ዲጂታልና ጥሬ ገንዘብ፤አልባ ኢኮኖሚ ለመሄድ እቅድ አስቀምጧል።

ይህ ዕድል ነው።

ግን ዲጂታል ኢኮኖሚው የዲጂታል ክፍተት፣ የሳይበር ደህንነት፣ የግላዊነትና የዲጂታል እምነት ጥያቄዎችንም ይዞ መጥቷል።

አስራ አምስተኛው ሁነት የጤና ቀውስ የሀገሪቱ ፈተና ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ጦርነት ብቻ አይገድልም፡፡ በ2018 ዓ.ም. የጤና ዘርፍም ከግጭትና ከሰብዓዊ ችግር ጋር ተያይዞ ትልቅ ፈተና ገጥሞታል።

WHO በአማራ ክልል የኮሌራ ስጋት ከግጭት፣ ከመፈናቀል፣ ከንጹህ ውሃና ከንጽህና እጥረት ጋር መያያዙን ገልጿል።

ይህ አንድ አስፈላጊ እውነትን ያሳያል፦

የጸጥታ ቀውስ በጥይት ብቻ አይለካም፤ በሆስፒታል ባልደረሰ ሕፃን፣ በተዘጋ ጤና ጣቢያና በተበከለ ውሃም ይለካል።

አስራ ስድስተኛው ጫና የሰብዓዊ ችግር ነው፡፡ የጦርነት ዋጋ ከጦር ሜዳ ውጭ ዋጋ እያስከፈለ ነው፡፡

የትግራይ ጦርነት ያስከተለው መፈናቀል፣ በአማራና በሌሎች አካባቢዎች ያለው ግጭት፣ ድርቅና የኑሮ ጫና የሰብዓዊ ሁኔታን አስከብደዋል።

World Bank በቅርብ የሀገሪቱን የድህነትና የሰብዓዊ ጫና ሁኔታ ሲገመግም፣ የትግራይ ጦርነት፣ ድርቅ፣ ግሽበትና ሌሎች ቀውሶች የኑሮ ደረጃን እንደጎዱ ጠቁሟል።

ስለዚህ 2018 ዓ.ም. የልማት ታሪክ ብቻ አይደለም፤ የችግር ዋጋ የተከፈለበትም ዓመት ነው።

አስራ ሰባተኛው የሱዳን ጦርነት የኢትዮጵያ የቀጠናዊ ስጋት ሁኗል፡፡

የሱዳን ጦርነት ለኢትዮጵያ ቀጥተኛ የድንበር፣ የስደተኞች፣ የንግድና የደህንነት ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል።

በግንቦት 2026 የሱዳን ጦር ኢትዮጵያን ከድሮን ጥቃቶች ጋር አገናኝቶ ክስ አቀረበ፤ ኢትዮጵያ ግን ክሱን “መሠረተ ቢስ” ብላ አስተባበለች።

ይህ ክስ በራሱ ተረጋግጧል ማለት አይደለም፤ ግን በቀጠናው የሚጨምረው የደህንነት ግፊት እውነተኛ ነው።

2018 ዓ.ም. አስራ ስምንተኛው ሁነት ኢትዮጵያ በአዲስ የሥልጣን ፍለጋ ከውስጥ ፖለቲካ ወደ ቀጠናዊ ኃይል የተለየበት ዋና ለውጥ ይህ ነው፦

ኢትዮጵያ የውስጥ ፖለቲካ ችግሮቿን ብቻ እየፈታች አይደለም፤ በቀጠናው ያላትን የኃይል ቦታ እንደገና ለመገንባት እየሞከረች ነው።

GERD፣ የቀይ ባሕር መዳረሻ፣ ከኤርትራ ጋር ያለው ውጥረት፣ ከሱዳን ጋር ያለው የቀጠና ጉዳይ፣ የሶማሊያ እና የSomaliland ጉዳዮች ኢትዮጵያን በHorn of Africa የኃይል ሚዛን መካከል አስቀምጠዋል።

የቀጠናው ኃያላን እና የባሕረ ሰላጤው አገሮች በHorn of Africa ያላቸው የፖለቲካና የወታደራዊ ተፅዕኖም እየጨመረ ነው።

2018 ዓ.ም. የተወው ትልቁ ቅርስ፤ 2018 ዓ.ም.ን በአንድ ቃል መግለጽ ካስፈለገ፦

“ውግርግር ያለ ሽግግር” ልንለው እንችል ይሆናል፡፡  ኢትዮጵያ ከአንድ የፖለቲካ ዘመን ወደ ሌላ ዘመን እየተሸጋገረች ነው። ከአስተዳደራዊ ኢኮኖሚ ወደ ገበያ፤ተኮር ኢኮኖሚ፤ከጦርነት ወደ የውስጥ ፖለቲካ ወደ ቀጠናዊ ስትራቴጂ፤ ከጥሬ ገንዘብ ወደ ዲጂታል ክፍያ፤ ከየግል ፓርቲ ውድድር ወደ ጠንካራ የፓርቲ ቁጥጥር፤ ከዕዳ ቀውስ ወደ የዕዳ መልሶ ማዋቀር መቀየሯል ታይቷል።

ግን ይህ ሽግግር ማንን እያሻገረ ነው? መንግሥትን? ኢኮኖሚውን? ወጣቱን? ገበሬውን? ተቃዋሚውን? ወይስ ተራውን ዜጋውን? ብለን ለመጠየቅ መልሱ ሙሉ ስለማይሆን ትተነዋል፡፡

2019 አዲሱ ዓመት በሩ ላይ ቆሟል። 2018 ዓ.ም. ጥያቄዎችን አከማችቶ እየሄደ ነው። ጦርነት ይቆማል?  የአማራ ላይ የሚካሄደው ጦርነት መቸ ያበቃል፣ ትግራይ እንደገና ወደ ግጭት ትመለሳለች ወይስ የፕሪቶሪያ ስምምነት ይድናል? የአማራና ኦሮሚያ ግጭት በፖለቲካዊ ውይይት ይፈታል ወይስ ማዕከላዊ መንግስትን ይበትናል? የኢኮኖሚ ማሻሻያው በቤተሰብ የኑሮ ደረጃ ላይ ይታያል? የብር ዋጋና የዋጋ ግሽበት ይረጋጋሉ? የዕዳ ችግሩ ይዘጋል?የባህር በር ጥያቄ በዲፕሎማሲ ይፈታል? ኢትዮጵያ በቀጠናው ኃይሏን ታጠናክራለች ወይስ አዲስ የግጭት መድረክ ይፈጠራል?

2018 ዓ.ም. የፈተናም ዓመት ነበር። ኢትዮጵያ ግድብ አስመረቀች። ምርጫ አካሄደች። ብሔራዊ ውይይት አደረገች። ኢኮኖሚዋን ለመለወጥ ገባች። የዕዳ ጫናዋን ለመቀነስ ተደራደረች። ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ተራመደች።

ግን ሰላም አልተረጋጋም። የፖለቲካ እምነት አልተጠናከረም። የኑሮ ጫና አልጠፋም።
የቀጠናው ውጥረት አልቀነሰም። ስለዚህ 2018 ዓ.ም. በታሪክ የሚቀረው በተሳካላቸው ፕሮጀክቶች ብቻ አይደለም። በመፍትሔ ያልተገኙ ጥያቄዎችም ነው።

2018 ዓ.ም. ተሰናበተች። ጥያቄዎቹ ግን 2019 ዓ.ም.ን ተከትለው ገብተዋል።

“ኢትዮጵያ ከቀውስ ወደ ሰላም ትሻገራለች? ወይስ ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ?”

የ2019 ዓ.ም. ታሪክ የሚመልሰው ጥያቄ ይህ ነው።

2018 ዓ.ም.፡ አንድ ዓመት፣ ብዙ ኢትዮጵያዎች ፤ ወዴት እየሄድን ነው? ምርጫ፣ ሥልጣን፣ ጦርነት፣ ኢኮኖሚና የባህር በር ጥያቄ፤ ኢትዮጵያ አንድ ዓመት ውስጥ ብዙ ዓመታትን ኖራለች!

አዲስ ዓመት ሊመጣ ፤ ዓመት በቁጥር ሊቀየር ፤ 2018 ዓ.ም. በታሪክ ገጽ ላይ ሊቀር ነው። ግን ይህ ዓመት ምን አስተማረን? ኢትዮጵያ ወዴት ተጓዘች? ምን አገኘች? ምን አጣች? እና 2019 ዓ.ም. ምን ይዞ ይመጣል?

2018 ዓ.ም. በቀላሉ የሚታለፍ ዓመት አልነበረም። የምርጫ ዓመት ነበር፤ የብልፅግና ሥልጣን ማጠናከሪያ ዓመት ነበር፤ የኢኮኖሚ ለውጥ ዓመት ነበር፤ የጸጥታ ፈተና ዓመትም ነበር።

2018 ዓ.ም. ምን አስተማረን?

2018 ዓ.ም. ኢትዮጵያን አንድ ቀላል እውነት አስተምሯታል፦ ሀገር በፕሮጀክት ብቻ አትገነባም። መንገድ ያስፈልጋል። ድልድይ ያስፈልጋል። ግድብ ያስፈልጋል።
ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል።የማዳበሪያ ፋብሪካ ያስፈልጋል፤ አምራች ስራ ፈጠራ ያስፈልጋል፡፡

ግን ከሁሉ በፊት ሰላም፣ ፍትሕ፣ ተቋማት፣ እምነት እና የዜጎች ተሳትፎ ያስፈልጋሉ።

2019 ዓ.ም.፣ የተስፋ ዓመት ወይስ የፈተና ዓመት?

አዲሱ ዓመት በቀናት፣ በስዓታት ውስጥ ይመጣል። ነገር ግን አዲስ ዓመት ብቻ አዲስ ኢትዮጵያ አያመጣም። 2019 ዓ.ም. የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ግልጽ ናቸው፦ ሰላም ይመጣል? በአማራ ክልል ያለው እሳት መቸ ይበርዳል? በትግራይ የተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ በውይይት ይፈታል? በአማራና ኦሮሚያ የሚቀጥለው ግጭት ይቆማል? የኢኮኖሚ ማሻሻያው የተራ ዜጋን ኑሮ ያሻሽላል? የምርጫ ውጤት ወደ ጠንካራ ዴሞክራሲ ይተረጎማል? የባህር በር ጥያቄ ወደ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ይሄዳል?

2018 ዓ.ም. አልተዘጋም፡፡ ታሪኩ ወደ 2019 ተሸጋግሯል!

2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የለውጥ ዓመት ነበር። ግን ለውጡ አልተጠናቀቀም። የምርጫው ውጤት ተገልጿል። የኢኮኖሚ ማሻሻያው ቀጥሏል። ግድቡ ተመርቋል። የባህር በር ጥያቄ ጠንክሯል። የሰላም ጥያቄ ግን አሁንም በጠረጴዛው ላይ ነው።

ስለዚህ 2019 ዓ.ም. የሚሆነው ቀጣዩ የቀን መቁጠሪያ ዓመት ብቻ አይደለም።

የኢትዮጵያ ቀጣይ የፖለቲካ ታሪክ የሚጻፍበት ዓመት ነው። 2018 ዓ.ም. ይሰናበታል።  2019 ዓ.ም. ይመጣል።
ጥያቄው ግን አንድ ነው፤ “ኢትዮጵያ ወዴት ትሄዳለች?”

እኔ ምን አውቃለሁ

ቸር ወሬ ያሰማን

Next Post
• AFRICA
• General
• Health
• Human Rights
• Latest
• Magazine
• News
• Radio & TV
• Special Edition
• TOP STORIES

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

Ayele Addis November 2, 2026

By Meserete Abebe Abay, Health CorrespondentPublished November 2, 2026 A Virus Outpacing History One hundred and seventy-four days after the initial declaration of the current outbreak, the continent faces an invisible enemy moving faster than its systems of containment. Speaking to journalists from the Africa Centres for Disease Control and Prevention (Africa CDC) headquarters during […]

Related Post

• AFRICA
• FEATURED
• Female
• Latest
• News

መንግስት መር አሳሳች መረጃዎች በታገቱ ተማሪዎች ዙሪያ የሳለፉት የጊዜ ሂደት እና ክንውኖች፡፡

Ayele Addis January 30, 2020July 12, 2021

Timeline of government #Disinformation & #Misinformation about Amhara Innocent University Girls Kidnap in Oromia region ህዳር 2012 መጨረሻ ንፁሀን የአማራ ክልል ተማሪዎች በብሄር በደረሰባቸው ጥቃት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ መንግ,ገድ  ላይ እንዳሉ በታጠቁ ሃይሎች ታገቱ፡፡ የአካባቢው ኗሪም የልጆችን ጩህት እየሰማ ለመታደግ አልሞከረም፡፡  ታህሳስ 1/2012 ዓ.ም ድረስ መታገታቸውን የሰሙ ወላጆች ለመንግስት አቤቱታ አሰሙ ፤ የስልክ ግንኙነታቸው ተቋረጠ፡፡ […]

• News

Is Ethiopia’s $2.49 Billion Steel Backbone a Gateway to Growth or a Trap of Corrosive Capital?

Ayele Addis May 30, 2026May 30, 2026

By Ayele Addis & Team The Grand Ambition: A Steel Corridor to the Sea At dawn on the outskirts of Addis Ababa, inside a maintenance compound lined with imported Chinese electrical panels, Ethiopian technicians begin the grueling work of keeping one of Africa’s most ambitious transport systems alive. These engineers inspect the braking and signaling […]

• AFRICA
• General
• Health
• Human Rights
• Investigative Reports
• Latest
• Magazine
• News
• Radio & TV
• TOP STORIES

The Woman Who Smiles Outside the Clinic

Ayele Addis March 21, 2026September 21, 2026

By Amisale Genet Demelew EMMA NEWS – Ethiopian Mass Media Publication No. 048 | Date: March 24, 2026 There is a moment in the infertility clinic that few people outside it ever see. A woman walks through the door. She may greet the receptionist. She may answer questions. She may smile when someone speaks to […]

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

• Privacy Policy
• ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
• Status
• የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

• ዜና
• ልዩ ዕትም
• ኢመብድ
• ስፖርት
• ራዲዮ እና መክስተትርዒት
• ጉብኝት
• ዕድሎች
• ኢመብድ ሽልማት
• AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
• ትምህርቶች
• Afaan Oromoo
• Tigrinya (ትግርኛ)
• Advertising and Media Services
• Radio Service
• TV & Digital
• EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress