#ሰባቱ_ሰማያት – ሰባቱ ሰማያት የሚባሉት፦
፩. ጽርሐ አርያም፡- ሰማየ ሰማያት፣ ከሰማያት ኹሉ በላይ ያለች ሰማይ ናት። ዳር ድንበሯን ከእግዚአብሔር በቀር ማንም አያውቀውም፡፡
፪. መንበረ ስብሐት(መንግስት)፡- አራት ቅርጽ ያላት ሲኾን ድንኳን ትመስላለች። የምንኖርባትን ዓለም ታክላለች፤ ሥላሴ በፈለጉት መጠንና መልክ ለቅዱሳን ይገለጡባታል፤ ሰባት የእሳት መጋረጃዎችም አሏት። /ዘፍ.28፡12-17፣ ኢሳ.6፡1-2/፡፡
፫. ሰማይ ውዱድ፡- ኪሩቤል የሚሸከሙት የሥላሴ ዙፋን ነው /ሕዝ.10፡19-20/፡፡፬. ኢዮር፣
፭. ራማ እና ፮. ኤረር፡- እነዚህ ሦስቱ የመላእክት ከተሞች ሲኾኑ ከአድማስ እስከ አድማስ የተዘረጉ ናቸው፡፡ ከላይ ወደ ታች፦ ሰማይ ውዱድ፣ ኢዮር፣ ራማና ኤረር የተያያዙ ናቸው፡፡ ስፋታቸውም እኩል ነው፡፡
፯. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፡- አራት ማዕዘን፣ ፲፪(12) በሮች አሏት፡፡ በውስጧ የብርሃን ሳጥን የተቀረጸ ከሥላሴ ፀዳል የተሣለባት ታቦት ዘዶር አለች፡፡ ይህቺም የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዓይን ያላየው፣ ጆሮ ያልሰማው፣ በሰውም ልብ ያልታሰበ፣ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጃት ናት ያላት ይይችን ነው። /1ኛ ቆሮ.2፡9-10/፡፡ መጠኗም የተወሰነ ነው፡፡ ባለ ራእዩ ዮሐንስ አዲሲቱ ሰማይ ያላትም ይህቺው ናት /ራእ.21፡2-3/፡፡ በጕበኖቿ የ12ቱ ሐዋርያት ስም፤ በመድረኮቿ የ12ቱ ነገደ እስራኤል ስም፣ በአዕማዶቿ የጻድቃን የሰማዕታት ስም ተጽፎባታል /ራእ.21፡11-15/

Key Highlights From THE ETHIOPOAN HERALD SATURDAY AUGUST 23, 2025
✍️ Ethiopian Airlines flies high as Africa’s no.1 carrier ✍️ Japan backs Africa’s call for UNSC seat ✍️ Djibouti to foster economic, security cooperation with Japan ✍️ Nat’l Dialogue to include Diaspora voices, citizens in custody ✍️ China, Africa forge partnership on anti-colonial solidarity, mutual respect ✍️ Contesting parties unite behind peaceful sea access effort […]