ወደ ዓለም መድረክ፤ ኢትዮጵያዊው መሐንዲስ ወሰን አማረ ገላው በዓለም ታሪክ ውስጥ ስሙን አስፈረመ
በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ታላቅ ኩራትና ደስታ የፈጠረ ታሪካዊ ድል ተመዝግቧል። ኢትዮጵያዊው መሐንዲስ ወሰን አማረ ገላው በዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ አቡዳቢ የተገነባውን በዓለም ላይ በሕንፃ ላይ የሚገኝ ከፍተኛው የሩጫ ትራክ (Highest Running Track on a Building) ግንባታ በማስፈጸም የጊነስ ዓለም አቀፍ ክብረ ወሰን ለመመዝገብ ችሏል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት የተገኘው በአቡዳቢ የሚገኘው አል አይን ታወር (Al Ain Tower) ላይ ሲሆን፣ የሩጫ መስመሩ ከመሬት ወለል 179.7 ሜትር (589 ጫማ ከ6.8 ኢንች) ከፍታ በኢንጀነሪንግ ሙያው በመምራት እንዲፈፀም ላሳየው ብቃት ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ እና ኢትዮጵያን ከስሙ ጋር አሰስመዝግቧል። ይህም በጊነስ ወርልድ ሬከርድስ በይፋ ተረጋግጦ በ ሰኔ 17 ቀን 2026 በታሪክ ውስጥ ተመዝግቧል።

ከባሕር ዳር የተነሳ የዓለም ደረጃ ስኬት
ወሰን አማረ ገላው ኢትዮጵያ ዛሬ ደግሞ የጊነስ ዓለም ዓቀፍ ክብረ ወሰን ያስመዘገበ መሐንዲስ ልጅ በማፍራቷ አዲስ ታሪክ ጽፋለች።
የወሰን ጉዞ የሚያሳየው ከኢትዮጵያ ተነስቶ በዓለም መድረክ የሚደረስ ስኬት እውነታ መሆኑን ነው። ለሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችም ይህ ስኬት የተስፋ መብራት ሆኗል።
የምህንድስና ድንቅ ሥራ
ይህ ፕሮጀክት በቀላሉ የሩጫ መስመር ብቻ አይደለም። ወደታች ለመመልከት ዳመና ጠቀስ በሆነ ከፍተ በ180 ሜትር የሚጠጋ ከፍታ ላይ የሚገኝ የመሩጫ ሜዳ መስመር በመገንባት ከፍተኛ የምህንድስና እውቀት፣ የደህንነት ዲዛይን፣ የሕንፃ ቴክኖሎጂ እና የከተማ እቅድ አዘገጃጀትን የሚጠይቅ ስራ ነው።
የሩጫ መስመሩ ለነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች ልዩ የጤና እና የእንቅስቃሴ ተሞክሮ ከመስጠቱ ባሻገር የአቡዳቢን የከተማ ገጽታ ከላይ ሆኖ ለማየት ያስችላል።
ይህ የምህንድስና ስኬት የዘመናዊ ከተሞች ለጤና፣ ለኑሮ ጥራት እና ለማህበረሰብ ተሳትፎ የሚሰጡትን ትኩረት የሚያሳይ ነው።
በዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ ኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር፦ “ኢትዮጵያ ትኮራበታለች” ብለዋል፡፡
በዚህ ታሪካዊ ስኬት ላይ የመጀመሪያዎቹ እንኳን ደስ አለህ መልዕክቶች ከኢትዮጵያ አምባሳደር በዩኤኢ ዶ/ር ጀማል በከር የተላለፈ ነው።
አምባሳደሩ በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልዕክት፦
“ለኢትዮጵያ ታላቅ የኩራት ጊዜ ነው። በኢትዮጵያ መንግሥትና በራሴ ስም መሐንዲስ ወሰን አማረ ገላው ይህን ክቡር የጊነስ ዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገቡ እንኳን ደስ አለዎት” ብለዋል፡፡
በመቀጠልም ይህ ስኬት የኢትዮጵያውያንን ተሰጥኦ፣ ፈጠራ እና ልቀት ለዓለም እንዳሳየ ገልጸው፣ ለወጣቶች ደግሞ ታላቅ መነሳሳት እንደሚሆን ጠቁመዋል።
“ኢትዮጵያ ከእኔ ጋር ናት” ያለው ኢንጅነር ወሰን አማረ ፣
የወሰን አማረ ገላው ስኬት የግል ድል ብቻ አይደለም። በውጭ ሀገር ቢሰራም በማንነቱ ኢትዮጵያዊነቱን የሚያኮራ ባለሙያ ነው። ይህ ሽልማት እንደተገኘ በኋላ ብዙዎች እንደገለጹት ወሰን ይህን ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጠ ክብር አድርጎ ይመለከተዋል።
የእርሱ ታሪክ አንድ ቀላል መልዕክት ይዟል፦
ኢትዮጵያን ከስሙ ጋር በማፃፍ አዲስ ታሪክ መወለድ ችሏል፤ ነገር ግን ዓለምን አስደንቋል።“
የጊነስ ወርልድ ሬከርድ የመስመሩን ከፍታ 179.7 ሜትር መዝግቦታል።
ኢትዮጵያውያን ግን የሚያዩት ከፍታ የሩጫ መስመሩን ብቻ አይደለም።
የሚያዩት የኢትዮጵያ ተሰጥኦ ከፍታ፣ የኢትዮጵያ እውቀት ከፍታ እና የኢትዮጵያ ልጆች ዓለምን የማስደነቅ አቅም ነው።
ዛሬ ኢትዮጵያ ትኮራለች።
ዛሬም ዓለም አንድ ኢትዮጵያዊ መሐንዲስ የሰራውን ድንቅ ሥራ እያከበረ ነው።
እንኳን ደስ አለዎት መሐንዲስ ወሰን አማረ ገላው! ኢትዮጵያ በእርስዎ ትኮራለች!

By Ayele Addis Ambelu (ayeleradio@gmail.com)
<strong>BLOOD ON THE HARVEST: the Hidden Cost of Foreign Farms: How Corrosive Capital Is Rewriting Ethiopia’s Land, Labor, and Future</strong>
By Amisale Genet & Meselch Zelalem | Ethiopian Mass Media (EMMA NEWS) “They told us development was coming. Instead, our land disappeared.” The old man points toward a stretch of land that once held sorghum fields, grazing grounds, and ancestral burial sites. Today, the horizon is dominated by commercial farms, fenced boundaries, and machinery that […]