For the CIPESA DPI Journalism Fellowship – Eastern Africa; Extract from Radio Program, By Ayele Addis Ambelu
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እቅድ ከ5 ዓመታት በፊት ይፋ የተደረገ ዕቅድ ሲሆን፤ የበይነመረብ አገልግሎትን እንደ መሳሪያ በመጠቀም የዜጎችን የዲጅታል ቴክኖሎጂ አቅም የማጎልበት እና በ2025 አካታች የሆነ ዲጅታል ኢኮኖሚን የመገንባት ዓላማ ያለው መሆኑን የዚህ ዕቅድ ሰነድ ያሳያል።
ዲጂታል ኢኮኖሚ መገንባት አገሮች ለደረሱበት የልዕለ ኃያልነት ደረጃ ብቻም ሳይሆን የዜጎቻቸው የዕለት ተዕለት ሕይወት
ቀላልና የተሳለጠ ለማድረግ ቁልፍና ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
የቴክኖሎጂን ጥቅም የተረዱ አገሮች ዲጂታል ቴክኖሎጂን ከመጠቀም ባለፈ በሠሩት ግኝትና ስርፀት ዛሬ ሁሉ ነገራቸውን
በዲጂታል መንገድ እንዲዘውሩ አግዟቸዋል፡፡ ዓለም መሽቶ በነጋ ቁጥር በተለያዩ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ተጥለቅልቃ
እንደመዋሏ ከተቻለ ከጊዜው ጋር አብሮ መራመድ ካልሆነም ከቀደሙት ላለመራቅ መሥራት ግዴታ መሆኑን ብዙኃኑ
ይስማሙበታል፡፡
ኢትዮጵያ ከምዕተ ዓለም በላይ የዘለቀ የቴክኖሎጂ ቁርኝት ያላት አገር መሆኗን ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ ዓለምን ያስገረሙ
የቴክኖሎጂ ውጤቶች ይፋ በተደረገበት ወቅት ብዙም ሳይቆይ ተቋዳሽ ከሆኑት አገሮች ውስጥም ትመደብ ነበር፡፡ ነገር ግን
ቴክኖሎጂዎችን ከመጠቀም ባለፈ በማዘመን፣ በማሳደግ፣ በጥናትና ምርምር ግኝቶች ላይ ሌሎች አገሮች የሄዱበትን ርቀት
ያህል ጥረት ባለመደረጉ ዲጂታላዊው በሆነ ዘመን ላይ ያላት ደረጃ ብዙ መሥራት እንዳለባት የሚያሳይ መሆኑን ባለሙያዎች
ያስረዳሉ፡፡
ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ቀርፃና አፅድቃ ወደ ሥራ ከገባች ሰነባብታለች፡፡ ዲጂታል ኢትዮጵያ የዲጂታል
ቴክኖሎጂ ዕድሎችን በመጠቀም ፈጠራ የታከለበትና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል በሚል
በመንግሥት ተነሳሽነት የሚመራ ዕቅድ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት የዲጂታል ክህሎትና ዕውቀት ለአገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡ በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርናና
በማንኛውም መስክ የሚሠሩ ሥራዎች የዲጂታል ክህሎትን ይፈልጋሉ፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ኋላ የቀረችበትና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ችግሮች በመፍታት ካደጉት አገሮች ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ መንግሥት
የቴሌኮም ዘርፉን ለገበያ ክፍት እንዳደረገ፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወደ ገበያ እያስገባ እንደሆነ፣ የትምህርት
ካሪኩለሙን እንደቀየረ የመንግሥት አሠራርን በዲጂታል መንገድ አስገዳጅ ማድረግ መጀመሩን እንዲሁም የአገልግሎት
ክፍያዎች በዲጂታል መንገድ ለማድረግ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝ ሲገለጽ ይደመጣል፡፡

የበይነመረብ መዘጋት እና የኤለክትሪክ መቆራረጥ ከተግዳሮቶቹ መካከል ናቸው
ለመሆኑ መንግሥት ከላይ የጠቀሳቸውን ሥራዎች በመተግበር ሒደት ውስጥ ውጤታማነቱ ምን ይመስላል? ከሌሎች የአፍሪካ
አገሮችስ ጋር ሲነፃፀር አገሪቱ የት ደረጃ ላይ ትገኛለች? የሚለውን ጉዳይ በተመለከተ ጂኤስኤምኤ (GSMA) የተባለው ዓለም
አቀፍ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች መረጃ አቅራቢ አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
በኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ባለፈው ሳምንት በተለያዩ መርሀግብሮች የዶጂታል ሳምንት ተከሂዷል። ይህ መርሀ ግብር በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጄ ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ የዛሬው የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዝግጅት ከ5 ዓመታት በፊት ይፋ በሆነው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች ላይ ፍተሻ አድርጓል።
በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ የዲጂታል ሳምንት ከየካቲት 18 እስከ የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተካሂዷል። በኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የተካሄደው እና ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጄው ይህ የዲጂታል ሳምንት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብሮች እንደነበሩት የመርሀ ግብሩ አስተባባሪ አቶ ቲዎድሮስ ታዘዘ ገልፀዋል።


አስተባባሪው እንደገለፁት መርሀ ግብሩ የተካሄደው የዲጅታል ግንዛቤ አስፈላጊነትን ታሳቢ በማድረግ ነው። አንድ ሳምንት በዘለቀው በዚህ መርሀ ግብር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ጉዞ ለውይይት ከቀረቡ ጉዳዮች መካከል ነው።
የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንዛቤን ማሳደግ ኢትዮጵያ ከ5 ዓመታት በፊት ይፋ ካደረገችው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጅን ለማሳካት ከሚረዱ መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ ነው። ይህ ስልት የበይነመረብ አገልግሎትን እንደ መሳሪያ በመጠቀም የዜጎችን የዲጅታል ቴክኖሎጂ አቅም የማጎልበት እና በ2025 አካታች የሆነ ዲጅታል ኢኮኖሚን የመገንባት ዓላማ እንዳለው የዚህ ዕቅድ ሰነድ ያሳያል። በአማራ ክልል የኢንተርኔት መቋረጥ በባንክ አገልግሎት፣ በግብረ ሰናይ እና የምርምር ሥራዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ
ያም ሆኖ የኢንተርኔት አገልግሎት ውስንነት እና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ፣ የሀይል አቅርቦት እጥረት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት ማነስ እና ቴክኖሎጂን ገዝቶ ለመጠቀም የኢኮኖሚ አቅም አነስተኛ መሆን አሁንም በሀገሪቱ ውስጥ ያልተፈቱ ችግሮች ናቸው።
በግላቸው በሶፍትዌር ልማት ላይ የተሰማሩት እና የሶፍትዌር መሀንዲስ የሆኑት አቶ ይግረማቸው እሸቴ ይህ ዕቅድ ከ5 ዓመት በፊት ይፋ ሲሆን አራት መሰረታዊ ምሰሶዎች እንደነበሩት ያስታውሳሉ።የመጀመሪያው የቴሌኮም ግንኙነትን እና የሀይል አቅርቦትን የሚያጠቃልለው የመሰረተ ልማት ግንባታ መሆኑን ይጠቅሳሉ።

ጂኤስኤምኤ ዓለም ባንክን ጠቅሶ ይፋ እንዳደረገው በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ተቋማት ኢንተርኔት የሚጠቀሙት 34 ከመቶ
የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ ግብርና ላይ የሚሠሩ ተቋማት ያላቸው የኢንተርኔት ተጠቃሚነት ድርሻ 13 በመቶ
ብቻ ሲሆን፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች 40 ከመቶውን እንዲሁም አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት 34 በመቶውን ይሸፍናሉ፡፡ ይኽም
በመሆኑ ሳቢያ ከአጠቃላይ አገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ተቋማት ድረ ገጽ ያለው 11 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው፡፡ ማኅበራዊ
ሚዲያ፣ ለቢዝነስ የሚጠቀሙት ደግሞ 25 በመቶ ብቻ የሚሆኑ ተቋማት እንደሆኑ ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
የአገሪቱን የዲጂታል ስትራቴጂ ቀረፃን ብሎም የቴሌኮም ማሻሻያ እንቅስቃሴዎች በጎነት እንደ ጥሩ ጅማሮ ተወስዶ ነገር ግን
ተስፋ የተጣለበትን ስትራቴጂ ግቦች ዕውን እንዲሆኑ ከተፈለገ በመንግሥት፣ በቴሌኮም ኦፕሬተሮች እንዲሁም በዘርፉ
ተቆጣጣሪ የመንግሥት አካል ሊጤኑ የሚገባቸውን ጉዳዮች የጂኤስኤምኤ ሪፖርት አመላክቷል፡፡
ለአብነትም ከሞባይል ጋር የተገናኙ ፖሊሲዎች መሻሻል የሚገባቸው ሲሆን፣ ይህም ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን መገልገያዎች
ለአገሪቱ ዜጎች እንዲደረሱ ማድረግ የኢንዱስትሪውን የፋይናነስ ዘላቂነት ስለሚያሻሽል ነው፡፡ ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ የሞባይል
መገልገያዎች እንዲያገኙ የሚያስችል ፖሊሲ መቀረፁ የዜጎችን ፍላጎት በመጨመር የሞባይል ግንኙነትና ገንዘብ አገልግሎት
ኢንቨስትመንቶች እንዲጨምር ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አዋጅን መሠረት በማድረግ እያዘጋጃቸው ያሉ
የተለያዩ መመሪያዎች ቢኖሩም ይህንን ሒደት አጠናቆ ሥራ ላይ ማዋል አገሪቱ የተለመችውን የዲጂታላዊነት ዕቅድ ለማሳካት
የሚረዳ እንደሆነ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ጂኤስኤምኤ ትኩረት ሊያገኝ ይገባል ካለው ጉዳዮች ሌላኛው በቴሌኮም ዘርፉ ላይ የተጣሉ ታክሶች በተለይም ከአገልግሎት
አቅራቢዎች ይልቅ ተጠቃሚው ኅብረተሰብ ላይ ጫና ማሳደሩን ነው፡፡
ምንም እንኳን አንዳንድ ታክሶች በቴሌኮም ወይም በሞባይል ኦፕሬተሮች ላይ የሚጣሉ ቢሆንም አብዛኛውን ወጪያቸውን
ወደ ደንበኞች በከፍተኛ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት መተላለፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች እንደተመለከተው 90 በመቶ
የሚሆነው ተጠቃሚው የሚከፍሉ ታክስ ዋጋ ላይ የሚደረጉ ጭማሪዎች በሽያጭና በአገልግሎት ታክስ አማካይነት ወደ
ተገልጋዩ የሚመጡ ናቸው፡፡
ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስማርት ስልኮች አሥር በመቶ የኤክሳይስ ታክስ እንደሚጣልባቸው በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ፈርጀ ብዙ የድህነት መለኪያ ከ68.7 በመቶ በላይ ይሆነው
የአገሪቱ ሕዝብ በብዙ መለኪያዎች በከፍተኛ ድህነት ውስጥ እንደሚገኝ በተገለጸው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር
መሆኑን ተጠቅሷል፡፡ እነዚህንና መሰል ታክሶችን ማስወገድ አሊያም መቀነስ የስማርት ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽነትና
የሞባይል ብሮድባንድ አገልግሎት እንደሚያበረታታ ምክረ ሐሳብ የቀረበ ሲሆን፣ አገሪቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ላይ
ያስቀመጠችው ግብ በርካታ ዜጎች አገልግሎቱን ካልተጠቀሙ ዕውን እንደማይሆን ተጠቅሷል፡፡
ከቅርቡ መንግሥት ተግባራዊ ያደረገውን የቫት አዋጅ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎትን ጨምሮ በሌሎች የፋይናንስ አገልግሎቶች
ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ጂኤስኤምኤ አልሸሸገም፡፡
ታክስ ምንም እንኳን የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ ትልቅ መሣሪያ ቢሆንም፣ ነገር ግን በአስገዳጅነት በሞባይል
አገልግሎቶች ላይ የተጣለው ሕግ በኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ላይ ያልተጠበቀና አሉታዊ ውጤት ሊያስከትል
እንደሚችል በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡
ጂኤስኤምኤ ያዘጋጀውን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፖርት በሳምንቱ አጋማሽ በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል
በተዘጋጀ መርሃ ግብር ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ሁነት ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ
አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄለፑት እንዲሁም የጂኤስኤምኤ
ከፍተኛ ኃላፊዎች የተሳተፉበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
የፓናሉ ተሳታፊዎች እንዳስታወቁት ሪፖርቱ የኢትዮጵያን ዲጂታል ህልም ለማሳካት አንድ ዕርምጃ የሚያራምድ ሰነድ ሲሆን፣
ልዩ ልዩ የፖሊሲ ማሻሻያ ጥቆማዎች፣ በገበያው ውስጥ ያሉ ዕድሎችን እንዲሁም የሞባይል ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያን የዲጂታል
ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚያግዝበትን ሁኔታዎች የሚተነትን ነው።
ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው የበጀት ዓመት የቴሌኮም ሽፋንን በመጨመር የቴሌኮም ስርፀት መጠንን የሚያሳድጉ 1,298 አዲስ
የሞባይል ጣቢያዎችን ለመገንባት፣ 500 ተጨማሪ ከተሞችን የ4ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ፣15 ተጨማሪ ከተሞችን
የ5ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ፣ በተጨማሪም ኩባንያው አቅርቦትን ከማረጋገጥ አንጻር ከ1.1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ
የቴሌኮም መሣሪያዎች ለግለሰብና ድርጅት ደንበኞች ለማቅረብ ማቀዱን ወ/ሪት ፍሬሕይወት አብራርተዋል፡፡

በይነመረብ አገልግሎትን በተመለከተ ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ተደራሽነቱ 30 በመቶ መድረሱ አወንታዊ ቢሆንም በግጭቶች ሳቢያ በየጊዜው የሚደረገው የበይነመረብ መዘጋት እንዲሁም የጥራት ጉድለት አሁንም ፈተናዎች ናቸው።
ለዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ሁለተኛው መሰረታዊ ጉዳይ የዲጂታል አስቻይ ሁኔታ መኖር ነው:: ይህንን ለመፍጠርም የዲጂታል መታወቂያ ፣የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት እና ዲጅታል ደኀንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ነገሮች ናቸው። ከዚህ አንፃር ጅምሮች እንዳሉ የገለጹት ባለሙያው ነገር ግን ውስኑነቶች አሏቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚዘጋው፣ የሚገደበው ኢንተርኔት እና ያስከተለው ኪሳራ
ከሳይበር ደህንነት አንጻርም ምንም እንኳ በግለሰብ ደረጃ ችግሮች ቢኖሩም በተቋም ደረጃ ያን ያህል ስጋት አለመታየቱን አብራርተዋል።
ሌላው በሦስተኛ ደረጃ የተቀመጠው ዲጂታል መስተጋብር /ዲጂታል ኢንተራክሽን/ ሲሆን፤ እንደ ባለሙያው ገለፃ ለዘርፉ መሰረት የሆኑት የዲጂታል ገበያ እና የክፍያ ሥርዓቶች እንዲመቻቹና በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ፈጣን እንዲሆን ዲጅታል መስተጋብር ላይ ሊሰሩ የሚገባቸው በርካታ ሥራዎች አሉ።አሳሳቢው የኦንላይን ባንክ ዘረፋ
አራተኛው እና የመጨረሻው የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ዕቅድ መሰረታዊ ነገር የዲጂታል ሥነ-ምህዳር /የዲጂታል ኢኮሲስተምን/ ማልማት ነው። ለዚህም ሰዎች በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ አገልግሎቱን ለማግኘትም ሆነ ለመስጠት የዲጂታል ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል።የሶፍትዌር መሀንዲሱ አቶ ይግረማቸው እንደሚሉት አሁን ያለው የዲጂታል ሥነ-ምህዳር የተበታተነ ፣አባካኝ እና የተወሳሰበ ነው ይሉታል።ለዚህም የገንዘብ ተቋማትን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። ክላውድ፤መረጃን ከመጥፋት የሚታደገው ቴክኖሎጂ

ከዚህ በተጨማሪ የዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለማዳበር የውጭ የጥቃት ተጋላጭነትን የሚቀንስ የሀገር ውስጥ የባንክ አሰራር ስልትን መዘርጋት፣ የሰው ሀይልን ማብቃት እና ተጨማሪ ፖሊሲና መመሪያዎችን ማውጣትም የዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለማልማት አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በዲጅታል 2025 ዕቅድ የምታደርገው ዲጂታል ጉዞ የተወሰኑ ለውጦች የታዩበት ቢሆንም፤ ከላይ ከተጠቀሱት ተግዳሮቶች
በተጨማሪ በተቋማት የመሰረተ ልማት ዝርጋታ አነስተኛ መሆን፣በየተቋማቱ ያሉ ሰራተኞችም የዲጅታል ቴክኖሎጂ ግንዛቤ ደካማ መሆን ብዙ ሥራ የሚፈልግ ነው። በመሆኑም የሰው ሀይልን ለማብቃት ስልጠናዎችን መስጠት፣ተማሪዎች ከታች ጀምሮ የቴክኖሎጅ እውቀት እንዲኖራቸው በመስራት የዲጅታል እውቀትን ማስፋፋት ፣ የሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማበረታታት እና በገንዘብ መደገፍ እንዲሁም የዲጅታል ቴክኖሎጅ መሳሪያዎችን በአነስተኛ ዋጋ ማቅረብ ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ ከሚያግዙ ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ መሆናቸውን ባለሙያው አስረድተዋል።
ጂኤስኤምኤ በሪፖርቱ የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ እ.ኤ.አ. በ2028 ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ በጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት
ላይ ሊጨምር እንደሚችል ተንብዩዋል፡፡ በተጨማሪም በ2028 ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ከሞባይል ኢንተርኔት ጋር
እንደሚገናኙ በዚህም የተነሳ በተጠቀሰው ዓመት በግብርና ዘርፉ ላይ 140 ቢሊዮን ብር እንዲሁም በአምራች ኢንዱስትሪው
ላይ የ114 ቢሊዮን ብር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሷል፡፡
ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሱት ቁጥሮች አበረታችነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ነገር ግን ዛሬም ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ
የቴሌኮም የአጠቃቀም ክፍተት እንዳለ በመቀጠሉ፣ 76 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኔትወርክ ሽፋን ውስጥ ቢሆንም
አሁንም የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚ አለመሆኑ፣ አልፎ ተርፎም በሞባይል ኢንተርኔት አጠቃቀም ዙሪያ ያለው ጉልህ የጾታ
ልዩነትን ሪፖርቱ ዳሷል፡፡
ኢትዮጵያ እንደ አይሲቲ (ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ)፣ ፋይናንስና ቴክኒካል አገልግሎቶችን በማሳደግ በተለይ የንግድ አገልግሎቶችን
የማሳደግ ዕምቅ አቅም እንዳላት ይገለጻል፡፡ እነዚህ ንዑስ ዘርፎች ታዲያ ዕውቀት ተኮር፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚሳለው
እንዲሁም ብዙኃኑ ለሌሎች ዘርፎችም ግብዓት ሆነው የሚያገለግሉ በመሆናቸው፡፡ ይህ እንዳለ ቢሆንም የኢትዮጵያ አይሲቲ
አገልግሎት ኤክስፖርት በጠቅላላው የአገሪቱ አገልግሎት ዘርፍ ኤክስፖርት የሚሸፍነው ሦስት በመቶ ብቻ ያህሉን ሲሆን ይህም
ከሰሃራ በታች ካሉ አገሮች በጣም ያነሰ ነው፡፡
የሳፋሪኮም ኢትዮጵ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም በበኩላቸው የሳፋሪኮም አበርክቶ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቲጂ ሰነድ ላይ
ከተቀመጡት ግቦች ጋር እጅግ የሚጣጣም መሆኑን አስታውቀው ይሄንን የጋራ ዓላማ ከግብ ለማድረስ የመሠረተ ልማት
ግንባታና ማስፋፊያ፣ አስተማማኝና ፈጣን የኢንተርኔት አቅርቦት ላይ ትኩረት አድርገው እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

<strong>Power and People: The Nile, Climate, and Hydropower Energy Future</strong>
(Produced by EMMA Radio & TV Media in collaboration with the Pulitzer Center on Crisis Reporting) This story was produced by EMMA Radio & TV Media in collaboration with the Pulitzer Center on Crisis Reporting, as part of the investigative series Power and People: Ethiopia’s Climate and Energy Future. The project combines webinar, participative radio, […]