Skip to content
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now

Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • Latest

Internship Opportunity at the Ethiopian Media Women Association (EMWA)

<strong>“Striving for Community Change” – More than a Motto, A Movement</strong>

  • AFRICA
  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • Education
  • Election & Democracy
  • Human Rights
  • Investigative Reports
  • Journalism and Communication
  • Latest
  • Magazine
  • Media Litracy
  • News
  • Public Relation
  • Radio & TV
  • TOP STORIES

የጋዜጠኞች ስወራ ተጠያቂነትን ማስከተል አለበት

Ayele Addis August 24, 2025August 24, 2025

የጋዜጠኞች ስወራ ተጠያቂነትን ማስከተል አለበት

ከሕግ አግባብ ውጪ የታፈኑት ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ እና ጋዜጠኛ አብዱሰመድ መሐመድ፤ ከሁለት ሳምንት ገደማ በኋላ ከስወራ ነጻ ወጥተዋል። ጋዜጠኛ አብዱሰመድ ከ12 ቀናት በኋላ፤ ጋዜጠኛ ዮናስ ደግሞ ከ10 ቀናት ስወራ ነጻ ወጥተው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር አረጋግጧል።
ማህበሩ ሁለቱ ጋዜጠኞች ታፍነው መወሰዳቸውን እና መሰወራቸውን ተከትሎ የድርጊቱን ህገወጥነት በመቃወም ጋዜጠኞቹ ከስወራ ነጻ ወጥተው የተጠረጠሩበት ወንጀል ካለ በሕግ አግባብ እንዲዳኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር በመግጫ መጠየቁ ይታወሳል።

ምንም እንኳን የተፈጸመው ሕገ ወጥ ድርጊት አሳሳቢ ቢሆንም፤ ጋዜጠኞቹ ነጻ መውጣታቸውን ማኅበሩ የሚደግፈው እርምጃ ነው።

ጋዜጠኞቹ ያሉበት በማይታወቅበት ሁኔታ ከ10 ቀን በላይ ተሰውረው መቆየታቸው ሕገ ወጥ ተግባር በመሆኑ፤ የድርጊቱ ፈጻሚዎች በግልፅ ታውቀው በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።

ጋዜጠኞች የሚያስጠይቃቸው ወንጀል ቢፈጽሙ እንኳን በሕግ አግባብ ከመጠየቅ ይልቅ፤ ማፈን እና ማዋከብ ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው። መሰል ድርጊቶች አንደ አገር የሚዲያ ምህዳሩን የሚያጠቡና የዜጎችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሚገድቡ ስለሆነ፤ ጋዜጠኞች የአገርና የሕዝብን ጥቅም መሰረት አድርገው በነጻነት እንዲሰሩ ባለድርሻ አካላት አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጥሩ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ለጋዜጠኞች መብት ጥበቃ እና ለፕሬስ ነፃነት መጎልበት አዎንታዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን ይቀጥላል።

መንግሥት ለዜጎች ማድረግ ያለበት ጥበቃና ተጠናክሮ የቀጠለው ስወራ @ሲሳይ ሳህሉ

የእንግሊዝ የፖለቲካ ልሂቅና የሞራል ፈላስፋ የነበረውና እ.ኤ.አ. ከ1588 እስከ 1679 የኖረው ቶማስ ሆብስ፣ ‹‹ሌቪያታን››
በሚባለው መጽሐፉ፣ መንግሥት በቀዳሚነት ሕግ በማውጣትና ያወጣውን ሕግ ተግባራዊ በማድረግ በመንግሥት አልባ
ዓለም ውስጥ ለማከናወን አስቸጋሪ የሆነውን ሕዝባዊ ሥርዓት በማስፈን፣ የሕዝቡን ደኅንነት መጠበቅ ይገባዋል ብሏል፡፡
ፈላስፋው ሌቪያታን የተሰኘውን መጽሐፉን ጨምሮ ሌሎች የፍልስፍናና የፖለቲካ መጻሕፍቱ በኢትዮጵያ በሚገኙ የማኅበራዊ
ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች በብዛት ይገኛሉ፣ ለማስተማሪያነትም ይውላሉ።
ፈላስፋው ከ400 ዓመታት በፊት ትቶት ያለፈው ፍልስፍና በ21ኛው ክፍለ ዘመን አገሮች ተሰባስበው በመሠረቷቸው
ድርጅቶችና ስምምነቶች በተለይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተመድ (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ፣ በአፍሪካ
የሰዎችና የሕዝቦች መብት ድንጋጌ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የዜጎች የማይደፈሩና የማይገሰሱ መብቶችና የአካልና
የነፃነት መብቶች መከበርና መጠበቅ እንዳለባቸው በግልጽ ተደንግገዋል፡፡
በአገሮች መካከል በሚካሄድ ጦርነትና በአገር ውስጥ የእርስ በርስ ግጭት፣ የሥልጣን ሽኩቻ፣ አምባገነን መንግሥታት፣ የባለ
ብዙ ወገን ድርጅቶች አቅም ውስን እየሆነ መምጣት፣ በሕዝብና በመንግሥት መካከል በሚፈጠር አለመተማመን፣ የጂኦ
ፖለቲካ ፍትጊያ፣ መንግሥታት በሙስና መዘፈቅ፣ ደካማ የመንግሥት ተቋማት፣ ኢፍትሐዊ የሆነ አገልግሎት፣ በድህነትና ሌሎች
ምክንያቶች የተነሳ መንግሥታት ለዜጎቻቸው የሚሰጡት ጥበቃና ከለላ ውስን እየሆነ መጥቷል
በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ታጣቂዎች በንፁኃን ዜጎች ላይ ዕገታ መፈጸማቸው፣ በመንግሥት የፀጥታ አካላት ከመኖሪያ ቀዬአቸው
ወይም ከሥራና መዝናኛ ቦታዎች ታፍነው ተወስደው ለቀናት ተሰወሩ የሚባል ዜና ወይም ሪፖርት መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡
የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ይጠብቃሉ በሚባሉት የመንግሥት የፀጥታ አካላት ተወስደው ያሉበት ሳይነገር ለቀናት ተሰውረው
ከቆዩት ሰዎች መካከል ደግሞ፣ የመብት ተቆርቋሪዎችና ጋዜጠኞች የመጀመሪያ ተጠቃሾች ናቸው።
የአሜሪካ መንግሥት ባለፈው ሳምንት ባወጣው እ.ኤ.አ. የ2024 ዓመታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብች አያያዝና የሚዲያ
ምኅዳር ሪፖርት፣ የመንግሥት ኃይሎች ጋዜጠኞችን፣ ፖለቲከኞችና የማኅበረሰብ አንቂዎችን እንደሚሰውሩ አስታውቋል፡፡
ሪፖርቱ ጋዜጠኞችን ከሕግ አግባብ ውጪ ማሰርና በቁጥጥር ሥር ማዋልና መሰወር የተለመደ ድርጊት እየሆነ መምጣቱን፣
እንዲሁም የሚዲያ ምኅዳሩ ማሽቆልቀልን ጠቅሶ እ.ኤ.አ. ከ2020 ጀምሮ 54 ጋዜጠኞች አገር ጥለው መሰደዳቸውን

ኢንተርናሽናል ሚዲያ ስፖርት (አይኤምኤስ) የተሰኘውና በሚዲያ ምኅዳር ላይ የሚሠራው ድርጅት ከወራት በፊት የጋዜጠኞች
ደኅንነትን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት፣ እ.ኤ.አ. በ2024 ብቻ 43 ጋዜጠኞች ታፍነው ወይም ከሕግ አግባብ ውጪ ታስረው
እንደነበር ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት በጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃትና
የደኅንነት ሥጋት እየጨመረ መሆኑን አክሏል።
በተጠናቀቀው እ.ኤ.አ. 2024 በጋዜጠኞች ላይ የተፈጸሙ እስርና አስገድዶ የሚፈጸም ሥወራ እ.ኤ.አ. በ2025ም የቀጠለ
ሲሆን፣ ቢያንስ 11 ጋዜጠኞች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ ሦስት
ጋዜጠኞች ጭምብል ባጠለቁ አካላት ተወስደው የገቡበት ሳይታወቅ ከሳምንት በላይ ሆኖታል።
በአሐዱ ሬዲዮ 94.3 ‹ቅዳሜ ገበያ› የተሰኘ ፕሮግራም አዘጋጅ ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ፣ የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ
አዘጋጅ ዮናስ አማረ፣ እንዲሁም ሳሎን ቲዩብ የተሰኘ የኢንተርኔት ሚዲያ አውታር ባለቤት የሆነው ሐሰን ሰይድን ጨምሮ
ሦስቱም ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ታፍነው የገቡበት አልታወቀም።

ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ ነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ከነበረበት አዲስ አበባ ሃያ ሁለት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች
ተይዞ መወሰዱ፣ ተወስዶ ከተሰወረ ከቀናት በኋላ በፀጥታ ኃይሎች ታጅቦ ቢሮው መበርበሩንና የተያዘውም በፀጥታ ኃይሎች
መሆኑን የመረጃ ምንጮች መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡
የሪፖርተር ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ከሚኖርበት ኦሮሚያ ክልል ሸገር ክፍለ ከተማ ኮዬ ፈጬ አካባቢ ነሐሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም.
አመሻሽ ላይ ጭምብል ባጠለቁና የጦር መሣሪያ በታጠቁ ሰዎች ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ እንደተወሰደ በአካባቢው የነበሩ የዓይን
እማኞች ገልጸዋል። በአቅራቢያው የሚኖሩ ግለሰቦች የነበረውን ድርጊት በስልካቸው ካሜራ እንዳይቀርፁ ተብሎ ስልካቸው
ተወስዶ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
የሳሎን ቲዩብ ባለቤት እንደሆነ የተነገረለት ሐሰን ሰይድም ሐሙስ ነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ታፍኖ መወሰዱን የቅርብ
መረጃዎች ያመላክታሉ።
የጋዜጠኞችን መሰወርና ከዕይታ መጥፋት ተከትሎ ከአዲስ አበባ ፖሊስና ከፌዴራል ፖለሲ ስለጉዳዩ ለማጣራት ቢሞከርም፣
እዚህ ናቸው የሚል ምላሽ ካለመገኘቱም በላይ ያሉበትን ለማወቅ አልተቻለም፡፡
በጋዜጠኝነት ሙያ መሥራት ከሕግ ተጠያቂነት የማያድን ቢሆንም እንኳ፣ በ2013 ዓ.ም. ተሻሽሎ በወጣው የመገናኛ ብዙኃን
አዋጅ አንቀጽ 86፣ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ፣ ክሱ በቀጥታ በዓቃቤ ሕግ
አማካይነት ለፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተደንግጓል።
ይህ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 3 የተደገገውን የፕሬስና የመገናኛ ብዙኃን መብት ከመጣስ ባለፈ

የደኅንነታቸውን ሁኔታ አደጋ ውስጥ በሚጥል መንገድ ታፍነው የተወሰዱ ጋዜጠኞችን በተመለከተ፣ የሰወራቸውን አካልና
ያሉበት ቦታ እንዲታወቅ የተለያዩ አካላት ለመንግሥት ውትወታ ቢያደርጉም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።
‹ቅዳሜ ገበያ› የተሰኘው ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነው ሰለንዳ ኤቨንትስና ኮሙኒኬሽን ጋዜጠኛ አብዱልሰመድን በተመለከተ
በሰጠው መግለጫ፣ ‹‹የጓደኛችንን በሕይወት መኖርና የት እንደሚገኝ ለማወቅ ቤተሰቡ በሚያደርገው ጥረት የራሳችንን ድጋፍ
ያደረግን ሲሆን፣ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ግን እስካሁን የተጨበጠ መረጃ ማግኘት አልተቻለም፤›› ብሏል፡፡ ‹‹ማንም
ሰው ከሕግ በላይ መሆን እንደማይችል እንደምንረዳው ሁሉ፣ የአንድ ግለሰብ ተራ የሚባሉ ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱ
መመልከት ደግሞ እጅጉን የሚያሳዝነን ነው፤›› ሲልም አክሏል፡፡
ጋዜጠኛ ዮናስ ለቀናት በሥራ ላይ ባለመገኘቱና ታፍኖ መወሰዱ በመሰማቱ በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ ሴንተር አማካይነት
እየታተመ የሚወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው መግለጫ፣ ጋዜጠኛ ዮናስ ማንነታቸው ባልታወቁና ጭምብል ባደረጉ ሰዎች
መወሰዱን አስታውቋል፡፡
ጋዜጠኛው ከነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ባለመግባቱ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደወልለትም ሆነ ከቤተሰቦቹ ለማጣራት
ቢሞከርም ማግኘት አለመቻሉን፣ በሥራ ላይ እያለ የገባበት በመጥፋቱ የሥራ ባልደረቦቹና የቅርብ ጓደኞቹ በእጅ ስልኩ ላይ
ቢደውሉም ማግኘት አልቻሉም የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ ሪፖርተር በመኖሪያ ቤቱ በመሄድ ባደረገው ማጣራት፣
ጋዜጠኛው ረዕቡ ነሐሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ላይ ፊታቸውን በጭምብል በሸፈኑ ሰዎች የተወሰደ መሆኑን በአካባቢው
ከነበሩ የጥበቃ ሠራተኞች ለማወቅ መቻሉን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ጋዜጠኞቹን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ ባለፉት
ዓመታት ዜጎች የፀጥታ አካል ነን በሚሉ ግለሰቦች አንዳንዴም በማን እንደታፈኑና የት እንደታሰሩ የማይታወቅበት ሁኔታ
በተደጋጋሚ እያጋጠመ ነው ብሏል፡፡
በመንግሥት በተደጋጋሚ ያላግባብ ያሰርኩት ጋዜጠኛም ሆነ ዜጋ የለም የሚል ምላሽ እንደሚሰጥና ጉዳዩ መቀጠሉን
በመግለጽ፣ የመንግሥት ምላሽ በሁለት ምክንያቶች አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡
‹‹አንድም መንግሥት ድርጊቱን እየፈጸመ ነገር ግን እየደበቀው ከሆነ መንግሥት ሕገወጥ ተግባራትን ሆነ ብሎ እየፈጸመ ነው
የሚያስብል መሆኑን፣ ወይም እነዚህ ተግባራት የሚፈጸሙት ከመንግሥት ዕውቅና ውጪ በሌሎች በተደራጁ አካላት ከሆነ
መንግሥት በቅጡ የአገሪቱን ፀጥታና የዜጎችን ደኅንነት እያስጠበቀ አይደለም የሚል ሥጋት ዜጎች ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል፤››
በማለት ነው ኢዜማ ያስረዳው፡፡
በእነዚህ ሁነቶች ምክንያትም ዜጎች ጠባቂ የለኝም በሚል ሥጋት ደኅንነታቸውን በገዛ እጃቸው ለማስከበር እንዲሞክሩና የዜጎችን
የዕለት ተዕለት ሕይወት የሚፈታተኑ ሕገወጦች እንዲበራከቱ በማድረግ፣ የአገሪቱ የፀጥታ ሁኔታና የዜጎች ደኅንነት ከፍተኛ አደጋ
ውስጥ የሚከት አስፈሪ ሁነት ነው በማለት ኢዜማ ገልጾታል፡፡
ገዥው ፓርቲ ብልፅግና በቅርቡ ባወጣው መግለጫ እፈታቸዋለሁ ካላቸው ችግሮች ውስጥ በየደረጃው በሕዝቡ የሚነሱ
የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች አሉበት፡፡ በኢትዮጵያ አቅም በየደረጃው ጥያቄዎቹን ለመመለስ
ተገቢውንና እውነተኛውን መረጃ ለሕዝብ በየጊዜው ለመስጠትና ሐሰተኛ መረጃዎችን ማጋለጥ ነው ቢልም፣ በማግሥቱ እንዲህ
ዓይነት ድርጊት መፈጸሙ የተገባው ቃል ከልብ አለመሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው በማለት ኢዜማ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
ኢዜማ መንግሥት አገሪቱ አሁን ካለችበት ወደ ሌላ የከፋ ችግር ውስጥ ከመግባቷ በፊት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲያርም
አሳስቦ፣ ታፍነው የተሰወሩ ጋዜጠኞች ያሉበትን ሁኔታ በግልጽ እንዲያሳውቅም ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ጋዜጠኛ አብዱልሰመድና
ጋዜጠኛ ዮናስ ‹ከሕግ አግባብ ውጪ መሰወራቸውን› በመግለጽ ያሉበትን ሁኔታ መንግሥት በግልጽ እንዲያሳውቅ ጥያቄ
አቅርቧል፡፡
ጋዜጠኞቹ በወንጀል ተጠርጥረው ቢሆን እንኳን በሕግ አግባብ ተይዘው በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸው
ያለው ማኅበሩ፣ ‹‹ተይዘው የተወሰዱበት አለመታወቁ በእጅጉ ያሳስበኛል፤›› ብሏል፡፡
ማኅበሩ ከሕግ አግባብ ወጪ ጋዜጠኞችን መሰወርና ፍርድ ቤት አለማቅረብ በምንም አግባብ ተቀባይነት የሌለው አደገኛ

ይህ ሕግን ባልተከተለ አካሄድ የሚፈጸም ድርጊት ማኅበረሰቡ እየለመደው፣ ከጊዜ ወደ ጊዜም የበለጠ እየተላመደው
በመምጣቱ እንጂ በጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆን በፖለቲከኞች፣ በመብት ተሟጋቾች ጭምር ላይ ሲፈጸም የሚስተዋል
መንግሥታዊ ልማድ ነው ይላሉ፡፡
መንግሥት የተሰወሩትን ጋዜጠኞች የት እንዳሉ አላውቅም ማለት ሳይሆን አፈላልጎ የማምጣት ኃላፊነት አለበት የሚሉት አቶ
በፍቃዱ፣ የተፈጸመው በመንግሥት አካላት ከሆነ ደግሞ የአገሪቱን ሕግ በጠበቀ መንገድ ለፍትሕ የማቅረብ ግዴታ ያለበት አካል
እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት መጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት በመሆኑ ከአቅሙ በላይ እንኳ ቢሆን ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ
የማስታወቅ ግዴታ አለበት የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ከዚህ በተቃራኒ ሲሆን ግን ሕግን ያልጠበቀና ከአምባገነናዊነት ሥርዓተ
መንግሥት የሚመነጭ ተጠያቂነት የሌለው ባህሪ ነው ይላሉ፡፡
በታጣቂ ኃይሎች ለገንዘብ ወይም ለሌላ ዓላማ የሚፈጸሙ ዕገታዎች ወይም በመንግሥት ኃይሎች የሚፈጸሙ የአስገድዶ
መሰወር ድርጊቶችን የመከላከል፣ የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የመጠበቅ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ የመንግሥት ነው ሲሉም
ያሰምሩበታል፡፡

Don’t miss out! Grab your copy today.
Prefer to read online? Find the digital edition here: www.thereporterethiopia.com
Next Post
  • AFRICA
  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • Education
  • Job Vacancy
  • Journalism and Communication
  • Magazine
  • Media Litracy
  • Public Relation
  • Radio & TV
  • Scholarship
  • Scholarship and Opportunities
  • Special Edition
  • TOP STORIES
  • Training and Internships

<strong>“Striving for Community Change” – More than a Motto, A Movement</strong>

Ayele Addis August 28, 2025

When Amhara Media Corporation (AMC) was born in the late 1980s as a small bureau under the Amhara National Regional State’s Culture and Tourism office, few imagined it would grow into one of Ethiopia’s most influential regional media houses. From a staff of just 13 journalists armed with rudimentary tools, AMC has evolved into a […]

Related Post

  • Election & Democracy

የመራጮች ትምህርት ሚዲያ ካምፔን እና የምሽት ሬዲዮ ፕሮግራም ▶︎ •၊၊||၊|။|||| | “ልዩነት ግጭት አይደለም! የሀሳብ ብዝሃነት የዴሞክራሲ ውበት ነው!”

Ayele Addis May 18, 2026May 18, 2026

ወርሃ ግንቦት አስር ቀን ፣ ዕለተ ሰኞ 2018 ዓ.ምሰላማዊ ምርጫ = የተረጋጋ ሀገር!ድምፅዎ ሀገርን ይገነባል!የአማራ ክልል ሚዲያ እና ኪነ-ጥበባት ማህበር (ARMACA)Amhara Region Media and Art Associationየመራጮች ትምህርት ሚዲያ ካምፔን እና የምሽት ሬዲዮ ፕሮግራምየቀኑ መልዕክት“ሰላም የዴሞክራሲ መሠረት ነው!”“ልዩነት ግጭት አይደለም! የሀሳብ ብዝሃነት የዴሞክራሲ ውበት ነው!”ምርጫ በጥላቻ አይሸነፍም፤በሰላም፣ በክብር እና በህግ ይጠናከራል!⚠️ የጥላቻ ንግግር ሀገርን ያቃጥላል!የሰላም ቃል […]

  • Election & Democracy
  • News
  • Politics
  • Training and Internships

60 ጋዜጠኞች በምርጫ ስነ-ምግባር ስልጠና ተሳትፈው አጠናቀቁ

Ayele Addis March 2, 2026March 2, 2026

በአማራ ክልል ሚዲያ እና ኪነ ጥበባት ማህበርከየካቲት 21 እና 22 ቀናት 2018 ዓ.ም (2026) በባህር ዳር ከተማ ያዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር የምርጫ ዘገባ ስልጠና ለ60 የማህበረሰብና ዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች በመስጠት ተጠናቋል። በተለመደው የዜና ስልጠና አቀራረብ አይደለም፤ ይህ የዴሞክራሲ መከላከያ ስልጠና ነው ተብሎ ተገልጿል። “ዝምታ ሀገርን ያጠፋል” ማህበሩ ካካሄደው ቅድመ-ጥናት በኋላ ያቀረበው መልዕክት “ዝምታ ሀገርን ያጠፋል” የሚል […]

  • News

Hate Speech and Fake News In Ethiopia

Ayele Addis October 28, 2021October 28, 2021

ገጽ 1 የአውሮፓ የሰላም ተቋም | የውሸት ዜና የተሳሳተ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ፡ የተጋላጭነት ግምገማ 1የውሸት ዜና የተሳሳተ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ: የተጋላጭነት ግምገማ ኤፕሪል 12 ቀን 2021 ገጽ 2 የአውሮፓ የሰላም ተቋም | የውሸት ዜና የተሳሳተ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ፡ የተጋላጭነት ግምገማ 2ይዘቶችዋንኛው ማጠቃለያ ………………………………………… …………………………………………. ………………………………….. 3መግቢያ …………………………………………. …………………………………………. …………………………………………. […]

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • ዜና
  • ልዩ ዕትም
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress