Skip to content
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • Latest

ተሸላሚ ሚዲያዎች ለህዝብ ምኑ ናቸው?

<strong>IWPG Hosts 'the 5th International Loving Peace Art Competition' Exhibition at the African Union</strong> - IWPG Global Region 2 African high-ranking officials respond enthusiastically

  • AFRICA
  • Latest
  • News
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES

በወርቅ ታሪክ ዙሪያ ያለው ምሥጢር

Ayele Addis July 19, 2024July 19, 2024

Compiled by : Ayele Addis Ambelu

ወርቅ—እምብዛም ጥንካሬ የሌለውና ደመቅ ያለ ቢጫ ቀለም ያለው ብረት ነው። ይህ ብረት ልዩ ባሕርያት ያሉት በመሆኑ ከጥንት ጀምሮ ተፈላጊ ሆኖ ኖሯል። ቀለሙ፣ መብለጭለጩ፣ በተፈለገው ቅርጽ ሊስተካከል የሚችል መሆኑና ዝገትን መቋቋም መቻሉ ከሌሎች የብረት ዓይነቶች ልዩ ያደርገዋል። በፈላጊዎቹ ዘንድ የተሰጠው ከፍተኛ ግምት ከሌሎች ብረቶች ለየት ያለ ታሪክ እንዲኖረው አድርጎታል።

“ወርቅ! እርግጠኛ ነኝ፤ ወርቅ ነው! ወርቅ!” ሰዎች ወርቅ ሲያገኙ ልባቸው በደስታ ይፈነድቃል፤ ምቱ ይጨምራል፤ የሚይዙት የሚጨብጡት ይጠፋቸዋል። በየብስ ላይ፣ በወንዞችና ጅረቶች ውስጥ አልፎ ተርፎም ከምድር ገጽ በታች በሺህ የሚቆጠሩ ሜትሮች ቆፍረው ሲፈልጉት ኖረዋል።

ወርቅ ውድ ጌጥ እንደመሆኑ መጠን ነገሥታትና ንግሥቶች አጊጠውበታል። ዙፋናትና የቤተ መንግሥት ግድግዳዎች አሸብርቀውበታል። በዓሣ፣ በአእዋፍ፣ በእንስሳትና በሌሎችም ነገሮች ምስል የተቀረጹ የወርቅ ጣዖታት እንደ አማልክት ተቆጥረው ተመልከዋል። ሰዎች ወርቅ ለማግኘት ያደረጉት ተጋድሎ እጅግ ከፍተኛ ሲሆን ለሥልጣኔም ያበረከተው ድርሻ እንዲሁ የላቀ ነው።

ወርቅና ታሪክ

የጥንቷ ግብጽ ፈርዖኖች የግብጽ አማልክትና ፈርዖኖች ንብረት ተደርጎ የሚታየውን ወርቅ ፈልገው እንዲያመጡ ነጋዴዎቻቸውንና ሠራዊታቸውን ሩቅ ወደሆኑ አካባቢዎች ልከዋል። በ1922 የተገኘው የቱታንካሜን መቃብር እጅግ ከፍተኛ ዋጋ በሚያወጡ የወርቅ ዕቃዎች የተሞላ ነበር። የአስከሬን ሣጥኑ ሳይቀር ከወርቅ የተሠራ ነበር።

እንደ አንዳንድ ታሪክ ጸሐፊዎች አባባል ከሆነ ታላቁ እስክንድር “በመጀመሪያ ትኩረቱን ወደ እስያ እንዲያዞር ያደረገው ነገር በሰፊው ይነገርለት የነበረው የፋርሳውያኑ የወርቅ ሀብት ነው።” ሠራዊቱ ከፋርስ የዘረፈውን ወርቅ ወደ ግሪክ ለማሸሽ በሺህ የሚቆጠሩ የጭነት እንስሳትን ይጠቀም እንደነበር ሪፖርት ተደርጓል። ከዚህ የተነሣ ግሪክ በወርቅ የበለጸገች ሀገር ሆናለች።

አንድ ታሪክ ጸሐፊ ሪፖርት እንዳደረጉት ከሆነ የሮም “ንጉሠ ነገሥታት ወርቅን በጉርሻ መልክ በመስጠት ባለ ሥልጣኖቻቸው ለእነርሱ ታማኝ ሆነው እንዲኖሩ እንዲሁም በሌሎች አገሮች ባለ ሥልጣናት ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ይጠቀሙበት ነበር። ከወርቅ በተሠሩ ጌጦቻቸው በሚንጸባረቀው ከፍተኛ ሃብታቸው ሕዝባቸውን ያስደምሙና ብዙውን ጊዜም ያስፈራሩ ነበር።” ሮማውያን ስፔይንን ድል አድርገው በያዙና የስፔይንን የወርቅ ማዕድን ማውጫዎች ባገኙ ጊዜ ብዙ ወርቅ እንዳፈሱ አንድ ጽሑፍ ዘግቧል።

ይሁን እንጂ ታሪኩ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ ብዙ ደም መፋሰስ የታየበት ታሪክም አለው። ታሪኩ የወረራ፣ የጭካኔ፣ የባርነትና የሞት ታሪክ ነው።

በደም የተጨማለቀ ታሪክ

ሥልጣኔ እየተስፋፋ ሲሄድ ትላልቅና የበለጠ ኃይል ያላቸው መርከቦች አዳዲስ መሬቶችን ማሰስ፣ ነዋሪዎችን ማስፈርና ወርቅ መፈለጉን ተያያዙት። ግንባር ቀደም ባሕረተኛውን ክርስቶፈር ኮለምበስን (1451–1506) ጨምሮ ወርቅ ማግኘት የብዙ አሳሾች የቀን ሕልም ሆነ።

ኮለምበስ ወርቅ ለማግኘት በሚያደርገው ጥረት ለአገሬው ሰዎች ሕይወት ቅንጣት ታክል አዘኔታ አልነበረውም። ወጪዎቹን ይሸፍኑለት ለነበሩት የስፔይን ንጉሥና ንግሥት በአንድ ደሴት ላይ ስላጋጠመው ነገር ሲዘክር በውሎ ማስታወሻው ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ይህን አካባቢ ለመግዛት የሚያስፈልገው እዚህ ሰፍሮ በአገሬው ላይ ሥልጣን ማወጅ ብቻ ነው፤ የታዘዙትን ሁሉ የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው። . . . ሕንዳውያኑ . . . እርቃናቸውን የሚሄዱና ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ በመሆናቸው ትእዛዝ ተቀብለው በተግባር ለማዋል የተዘጋጁ ናቸው።” ኮለምበስ የአምላክን በረከት እንዳገኘ ይሰማው ነበር። የወርቅ ክምችቱ ስፔይን የምታደርጋቸውን ቅዱስ ጦርነቶች በገንዘብ ለመደገፍ የሚረዳ ነበር። በአንድ ወቅት የወርቅ ጭምብል በስጦታ ካገኘ በኋላ ‘አምላክ በምሕረቱ ወርቅ እንዳገኝ ይርዳኝ’ ብሏል።

የኮለምበስን ዱካ በመከተል የባሕር ጉዞ የጀመሩት የስፔይን ባለ ድሎች ከስፔይኑ ንጉሥ ፈርዲናንድ እንዲህ የሚል ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል:- “ወርቅ አምጡልኝ! የሚቻል ከሆነ በሰላም። እንዴትም ቢሆን ብቻ ወርቁን አምጡልኝ።” ምሕረት የለሾቹ አሳሾች በሜክሲኮ እንዲሁም በማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ ያገኟቸውን በሺህ የሚቆጠሩ የአገሬውን ተወላጆች ደም አፍስሰዋል። ወደ ስፔይን የተጫነው ወርቅ ደም የተነከረ ነበር ለማለት ይቻላል።

ከዚያም የየትኛውንም ብሔር ባንዲራ የማያውለበልቡ የባሕር ወንበዴዎች ብቅ አሉ። በጋራ የባሕር ክልሎች ላይ እየጠበቁ ወርቅና ሌሎች ውድ ንብረቶች የጫኑትን የስፔይን የንግድ መርከቦች ዘርፈዋል። ብዙውን ጊዜ እነዚህ የንግድ መርከቦች ራሳቸውን ለመከላከል የነበራቸው የጦር መሣሪያም ሆነ የሰው ኃይል በሚገባ ከታጠቁት የባሕር ወንበዴዎች ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ነበር። በ17ኛውና በ18ኛው መቶ ዘመን የባሕር ላይ ውንብድና በተለይ በዌስት ኢንዲስና በአሜሪካ ድንበር አካባቢ የባሕር ላይ መቅሰፍት ሆኖ ነበር።

የ19ኛው መቶ ዘመን የወርቅ ሽሚያ

በ1848 በካሊፎርኒያ ሳክራሜንቶ ሸለቆ ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ ተገኝቶ ነበር። ወሬው ወዲያው ስለተሰማ ድርሻቸውን ለማግኘት የፈለጉ ብዙ ሰዎች ወደዚያው ይነጉዱ ጀመር። በሚቀጥለው ዓመት ካሊፎርኒያ “ፎርቲ ናይነርስ” በሚባሉ ከዓለም ዙሪያ በመጡ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሀብት ፈላጊዎች ተጥለቀለቀች። በ1848 ሃያ ስድስት ሺህ ገደማ የነበረው የካሊፎርኒያ ነዋሪዎች ቁጥር በ1860 ወደ 380,000 ደርሶ ነበር። በወርቅ እንጀራቸውን ለማውጣት ሲሉ ገበሬዎች መሬታቸውን ትተው ሄደዋል፣ መርከበኞች ሥራቸውን ትተዋል፣ ወታደሮችም ሠራዊቱን ጥለው ወጥተዋል። አንዳንዶቹም “ደም የተጠሙ ወስላቶች” የሚል ስያሜ አትርፈዋል። ከተለያየ ሕብረተሰብ የተሰበሰቡ ሰዎች በሚገኙበት በዚህ ቦታ ወንጀልና ዓመፅ ተስፋፍቶ ነበር። ወርቁ ያማለላቸው፣ ግን ድካሙን የጠሉ ሰዎች ወርቅ ተጭነው የሚመጡ ጋሪዎችንና ባቡሮችን መዝረፍ ጀመሩ።

ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ በ1851 በአውስትራሊያ ከፍተኛ ክምችት ያለው ወርቅ ተገኘ። ሪፖርቱ እንደገለጸው “ምርቱ በእርግጥም ድንቅ ነበር።” ለአጭር ጊዜም ቢሆን አውስትራሊያ በዓለም ከፍተኛ የወርቅ አገር አምራች ሆና ነበር። ወደ ካሊፎርኒያ ከሄዱት መካከል አንዳንዶቹ ሻንጣቸውን ጭነው ወደ ታችኛዋ አገር አቅንተዋል። የአውስትራሊያ ነዋሪዎች ቁጥር በ1850 ከነበረበት ከ400,000 ተነስቶ በ1860 ወደ 1,100,000 ከፍ ብሏል። አብዛኛዎቹ ሰዎች የተረባረቡት ወርቅ በመዛቅ እንጀራቸውን ለማውጣት ስለ ነበር ግብርናውና ሌሎቹም ሥራዎች ዕድገታቸው ባለበት ተገትቶ ነበር።

በ19ኛው መቶ ዘመን መጨረሻ አካባቢ እነዚህ ወርቅ የማግኘት ምኞት ያሰከራቸው ሰዎች በዩኮንና አላስካ ወርቅ ሲገኝ ወደዚያም ተጉዘዋል። በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ በወርቅ በበለጸገ አገር በመኖር የድርሻቸውን ለመሰብሰብ ራቅ ወዳለው ሰሜናዊ ክፍል ማለትም ወደ ክሎንዳይክና አላስካ ሄደዋል።

ባሕር ውስጥ የሰጠመ ሀብት

በባሕር ውስጥ ጠልቆ የመዋኘት ችሎታ በዳበረበት በ20ኛው መቶ ዘመን ወርቅ ፈላጊዎች በባሕር ውስጥም ማሰስ ጀምረዋል። እንደ ወርቅ ያሉ ውድ ማዕድኖችንና ከብዙ መቶ ዘመናት በፊት የተሠሩ ሰው ሠራሽ ጌጦችን ፍለጋ የሰጠሙ መርከቦችን ማሰሱን ተያይዘውታል።

መስከረም 20, 1638 ኮንሴፕሲዮን የተባለችው የስፔይን የንግድ መርከብ በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ እየተገፋች ከአለቶች ጋር በመላተሟ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ከሳይፓን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ሰጥማ ነበር። የጫነቻቸው ወርቅና ሌሎች ውድ ነገሮች ዛሬ ባለው ተመን በአሥር ሚልዮኖች የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ ነበር። ተሳፍረው ከነበሩት 400 ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ሞተዋል። ጠላቂ ዋናተኞች እያንዳንዳቸው 1.5 ሜትር ርዝማኔ ያላቸውና ብዙ ኪሎ ግራም የሚመዝኑ 32 የወርቅ ሰንሰለቶችን ማውጣት ችለዋል። በአጠቃላይ ጠላቂ ዋናተኞቹ 1,300 የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦች ማለትም ሰንሰለቶች፣ መስቀሎች፣ አርማዎች፣ የደረት ጌጦች፣ ቀለበቶችና ዘለበቶች አግኝተዋል።

ሌሎች የሰጠሙ መርከቦችም ተገኝተዋል። በ1980 ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በፍሎሪዳ የባሕር ዳርቻ የሚገኙ ጠላቂ ዋናተኞች በ17ኛው መቶ ዘመን የሰጠመችውን ሳንታ ማርጋሪታ የተባለች የስፔይን የንግድ መርከብ አግኝተዋል። እስከሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ድረስ ጠላቂ ዋናተኞቹ ከ44 ኪሎ ግራም የሚበልጥ ጥፍጥፍ ወርቅና ሌሎችም ከወርቅ የተሠሩ ነገሮችን ማውጣት ችለዋል።

በጦርነት የተገኘ ወርቅ

የጀርመን መንግሥት በ1945 እጁን ከሰጠ በኋላ የሕብረ ብሔሩ ኃይል በጀርመን ቱሪንጂ ባለው በካይዜሮደ የጨው ማምረቻ አስገራሚ ነገር አግኝቷል። ዘ አትላንታ ጆርናል እንዳለው ከሆነ “በቁፋሮው ቦታ 2.1 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ ጥፍጥፍ ወርቅ፣ የጌጣጌጥ ሥራዎች፣ ጥሬ ገንዘብና የአክሲዮን ባለቤትነት ዋስትና” ተገኝተዋል። በተጨማሪም ናዚ ባካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ ካለቁት ሰዎች የተሰበሰቡ የወርቅና የብር የጥርስ ሥራዎች የተቀመጡባቸው ከረጢቶች ተገኝተዋል። ይህ የተደበቀ ወርቅ የናዚ የጦር አዛዦች ረጅም ጊዜ የፈጀውን ጦርነት በገንዘብ ለመደገፍ አስችሏቸዋል። ጆርናሉ ሪፖርት እንዳደረገው ከሆነ 2.5 ቢልዮን ዶላር እንደሚያወጣ የተገመተ ወርቅ በአንድ ወቅት በጀርመን ተይዘው ለነበሩት አሥር የሚያክሉ አገሮች ተመልሶላቸዋል። ናዚ የደበቀው ገና ያልተገኘ ወርቅ አለ የሚል እምነት ስላለ ፍለጋው ቀጥሏል።

ወርቅ ከፍ ያለ ዋጋ እንዳለው ምንም ጥርጥር የለውም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ወርቅ እንደ ሌሎቹ ቁሳዊ ንብረቶች ሁሉ ለሚጓጉለት ሰዎች ሕይወትን ሊሰጥ እንደማይችል ይናገራል። (መዝሙር 49:6–8፤ ሶፎንያስ 1:18) አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ “ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል” ይላል። (ምሳሌ 16:16) የእውነተኛ ጥበብ ምንጭ ይሖዋ አምላክ ሲሆን ይህ ጥበብ የሚገኘው በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። እንዲህ ያለውን ጥበብ የሚፈልጉ ሰዎች የአምላክን ቃል በማጥናት የአምላክን ሕግጋት፣ መሠረታዊ ሥርዓቶችና ምክር ሊማሩና በሕይወታቸው ውስጥ ተግባራዊ ሊያደርጓቸው ይችላሉ። በዚህ መንገድ የሚገኘው ጥበብ የሰው ልጅ እስከዛሬ ድረስ ቆፍሮ ያወጣውን ወርቅ ሁሉ የሚያስንቅ ነው። ይህ ዓይነቱ ጥበብ ዛሬ የተሻለ ሕይወት ወደፊት ደግሞ የዘላለም ሕይወት ሊያስገኝልን ይችላል።—ምሳሌ 3:13–18

ስለ ወርቅ ጥቂት ለማለት ያህል

• ወርቅ ከማንኛውም ብረት ይበልጥ በቀላሉ የተፈለገው ቅርጽ ሊሰጠው ይችላል። ወርቅን 0.1 ማይክሮሜትር እስከሚያክል ድረስ ማሳሳት ይቻላል። 28 ግራም የሚመዝነውን ወርቅ በመጠፍጠፍ 17 ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሸፍን ማድረግ ይቻላል። 28 ግራም ወርቅ በቀጭኑ እየተጎተተ 70 ኪሎ ሜትር ድረስ ሊረዝም ይችላል።

• ንጹሕ ወርቅ ጥንካሬ ስለሚጎድለው ከሌሎች የብረት ዓይነቶች ጋር ተቀላቅሎ እንዲጠነክር ይደረግና ጌጣጌጦችና ሌሎች ነገሮች ይሠሩበታል። የወርቁ መጠን የሚገለጸው በአንድ 24ኛ መለኪያ ሲሆን ይህም ካራት ይባላል። በመሆኑም 12 ካራት ወርቅ ማለት 50 በመቶ ወርቅ ነው ማለት ነው። 18 ካራት ደግሞ 75 በመቶው ወርቅ ነው። 24 ካራት ከሆነ ንጹህ ወርቅ ነው ማለት ነው።

• ግንባር ቀደም የወርቅ አምራች አገሮች ደቡብ አፍሪካና ዩናይትድ ስቴትስ ናቸው። መረጃው የጄደብሊው ነው፡፡

ኦዶ ሻኪሶ-ወርቅ ‘መርዝ’ የሆነባት ምድር

የቢቢሲ አማርኛ ሙሉ መረጃ ምንጭ በመጥቀስ የኢትጲያን የወርቅ ታሪክ እንመልከት

የሚድሮክ ኩባንያ

ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል።

ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት አድርጎባቸዋል።

የእሳቸውን እና የልጆቻቸውን ጤንነት ይከታተሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእሳቸው አጥንት ህመምም ሆነ የልጃቸው እግር አጥንት መልፈስፈስ ምክንያቱ ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሑቴ የሚኖሩበት ዲባ በቴ ቀበሌ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ የሚገኝበት ነው።

“ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ። ጭንቅላታቸው መጠኑ በጣም ያነሰ ነው። እጅና አይናቸውም ተጎድቶ ይወለዳሉ። ሰው ታሞ ወደ ሐኪም ቤት ሲሄድ ከ ‘ነርቭ’ ጋር የተያያዘ ችግር ነው ይባላል።” በማለት የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ ዱቤ ጋሸራ ሚጁ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በዚሁ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት እኚህ አዛውንት “ድሮ ይህንን የሚመስል ችግር አልነበረም”ይላሉ። https://www.bbc.com/ws/av-embeds/cps/amharic/news-42266025/p05qgzyx/am የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, “መንግሥት የወጣቱን ቅሬታ ከመስማት ውጭ ምንም የለወጠው ነገር የለም።”

ዓይናቸው ከማምረቻው ውስጥ በሚወጣ ኬሚካል መጎዳቱን እንዲሁም በአግባቡ ቆመው መሄድ እንደሚያቅታቸው ነግረውናል። በተጨማሪም ከዚሁ ችግር የተነሳ በከብቶች እና በዱር እንስሳት እየደረሰ ያለው እልቂት ለትልቅ ችግር አጋልጦናል ይላሉ።

‘ሳናይድ’ እና የአካል ጉዳተኝነት

የሚድሮክ ለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ ወርቅና ነሐስ በሚያመርትበት ወቅት ወርቁን ለማፅዳት የሚጠቀምበት ኬሚካል ‘ሳናይድ’ ይባላል።

ይህ ኬሚካል ራስ ምታት፣የልብ፣ የአእምሮ እና የነርቭ ህመሞች እንደሚያስከትል የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጦና ዋሬ ነግረውናል።

ከዚህም ባሻገር የሰው አጥንት ለማጠንከር የሚረዱ እንደ ብረት(አይረን) ያሉ ንጥረ ነገሮች ከሰው እና ከእንስሳት አካል ውስጥ መጠኑን ይቀንሳል።

ይህም ለአጥንት መሳሳት እና መሰባበር እንደሚያጋልጥ አቶ ጦና ዋሬ ያስረዳሉ።

የወርቅ ማምረቻው የሚገኝበት ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥም የአካል ጉዳተኝነት ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው።

የቢቢሲ ሪፖርተር በአካል በቀበሌው ተገኝቶ አንድ ኪሎ ሜትር ባልሞላ መንደር ውስጥ ሶስት የአካል ጉዳት ያለባቸው ህፃናትን አይቷል።

በህፃናት ላይ የሚደርሰው የአካል ጉዳት በቀበሌው ውስጥ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ነዋሪዎች ወልደው ለመሳም እየተሳቀቁ እንደሆነ ይናገራሉ።

ወ/ሮ ደምበሊ ሔጦ የአካል ጉዳት ያለባት ህፃን አላቸው፤ “ልጆቼ በታመሙ ቁጥር ስጋት ያድርብኛል። ሌላ ተጨማሪ ልጅ ለመውለድ እንደዚሁ ልጅ ይሆንብኝ ይሆን ስል እሰጋለሁ” ይላሉ።

በተጨማሪም ነፍሰጡር ሴቶች ልጃቸውን ወልደው ከአካል ጉዳት ነፃ መሆኑን እስኪያረጋግጡ ድረስ ማርገዛቸውን እንደሚደብቁ፣ የአካል ጉዳት ያለበትን ህፃን የወለዱ እናቶችም ከሰው አይን ከልለው በቤት ውስጥ ደብቀው እንደሚያሳድጓቸውም የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በተጨማሪም የሳይናይድ ኬሚካል የተቀላቀለበት ወራጅ ውሃ የሚጠጡ እንስሳት ወዲያውኑ እንደሚሞቱ፣ የተበከለ አየር ውስጥ የሚቆዩት ደግሞ ከወደቁ በኋላ መነሳት እንደማይችሉ፣ አጥንታቸውም በቀላሉ እንደሚሰበር የአካባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ። https://www.bbc.com/ws/av-embeds/cps/amharic/news-42266025/p05qh0hd/amየተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, “ድጋሚ ተመሳሳይ ችግር ይደርስብኝ ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።”

የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች

የፋብሪካው የጥበቃ ሰራተኞች በህብረተሰቡ ላይ ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደሚያደርሱ ቅሬታዎች ይሰማሉ። ይህንን ቅሬታ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የወረዳው አስተዳደር ሰራተኞችም ይጋሩታል።

ለፋብሪካው ከሚደረገው ከፍተኛ ጥበቃ የተነሳ መንግስት በሰጣቸው ኃላፊነት ተጠቅመው በፋብሪካው ውስጥ ገብተው የቁጥጥር እና ክትትል ስራ ማድረግ እንዳልቻሉ የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ቦሬ ጦና ይናገራሉ።

ሰራተኞችንም በሚቀጥሩበት ወቅት ህጉ በሚያዘው መሰረት እንደማያሳትፏቸወው ከድርጅቱ የሚያገኙት ምላሽም “እኛ በእናንተ ሳእሆን በፌደራል መንግስት ነው የምንመራው” የሚል እንደሆነም ይናገራሉ።

የስራ እድል ማግኘትን ጨምሮ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ የማእድን አምራች ድርጅቶች ጥቅም እያገኘን አይደለም፤ ከዚህም አልፎ ችግር እየደረሰብን ነው በማለት የወረዳው ነዋሪዎች በተለያየ ጊዜ ሰልፍ ወጥተዋል።

ምላሽ

የአካባቢውን ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ቅሬታ መልስ ለማግኘት ወደ ማእድን ማምረቻው በሄድንበት ወቅት የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት መልስ የሚሰጡን የስራ ኃላፊዎች እንደሌሉ ነግረውናል።

ነገር ግን ይህ ፅሁፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣ በኋላ ሚድሮክ ለቢቢሲ በፃፈው ደብዳቤ ጉዳቱን አላደረስኩም ብሏል።

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር የለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ሳናይድ የተባለው ኬሚካል በሕዝብና በአካባቢ ላይ ጉዳት አለማድረሱን በደብዳቤው ገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን አዶ ሻኪሶ ወርቅ በማምረት የተሰማራው ይህ ኩባንያ አካባቢውን በጠበቀና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እየሰሩ መሆኑንም ጭምር ገልፀዋል።

“በአካባቢ ላይም ሆነ በሰዎች ላይ ከኬሚካል ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ችግር የለም” ብሏል።

ሚድሮክ በአካባቢው የተባሉት ችግሮች ተከስተው ቢሆን ኖሮ የሚያውቅበትም ዕድል እንደነበር ገልፆ የአካባቢን ጉዳዮች ለመከታተል ራሱን የቻለ ክፍል እንዳቋቋሙ ጠቁሟል።

ከዚህም በተጨማሪ በአዶ ሻኪሶ አካባቢ በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ የተሰማራው ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ኩባንያዎች በአካባቢው በመኖራቸው ከኬሚካል ጋር ተያይዞ ደረሰ የተባለው ጉዳት በእርግጥ ከሚድሮክ ጋር ብቻ የተያያዘ ስለመሆኑ ማረጋጋጫ የለም ብለዋል።

ሚድሮክ በአካባቢው ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ገልጾ፤ ትምህርትቤቶች፣የጤና ኬላዎች፣ የመንገድ ግንባታ ላይ በመሳተፍ ለብዙ ሰዎችም የስራ ዕድል እንደፈጠሩ አስታውቋል።

በማእድን ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የአካባቢ እና የማህበረሰብ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት ወ/ሮ እናት ፋንታ ግን “እስከ መጋቢት 2009 ዓ.ም ባደረግነው ክትትልና ቁጥጥር መሰረት በኬሚካል የደረሰ ጉዳት አላየንም፤ ከማህበረሰቡም ሆነ ከመንግስት አካል የደረሰንም ቅሬታ የለም” በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የሻኪሶ ከተማ

የማዕድን፣ነዳጅ እና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ግን በሚድሮክ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችችን ለመፍታት ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር መስራት አለበት።

ኬሚካል እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ እየደረሰ ያለው ጉዳትም በ አስቸኳይ በገለልተኛ አካል መጣራት አለበት እንዳሉ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ይሁን እንጂ ጥያቄው የወርቅ ምርቱ ተጠቃሚነት ሳይሆን በህይወት የመቆየት ስጋት የሆነባቸው የዲባ ባቴ ነዋሪዎች “ከመንግስት በኩል መፍትሄ እንፈልጋለን” እያሉ ነው።

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር በ1989 ዓ.ም የለገደንቢን የወርቅ ማእድን ከመንግስት እጅ በ172 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለ20 ዓመታት በሊዝ ነበር የተረከበው።

ድርጅቱ በ2014 እኤአ በአለም ባንክ በተዘጋጀው ፎረም ላይ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የሚድሮክ ለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ እኤአ ከ 1997-2014 ድረስ ባሉት 16 አመታት 52 0444.71 ኪሎ ግራም ወርቅ እንዲሁም 14 670.6 የብር ማእድን አምርቶ 17.24 ቢሊዮን ብር እንደሸጠ ያሳያል።

ድርጅቱ ለ20 ዓመታት የተፈራረመው ውል አሁን በያዝነው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ የሚጠናቀቅ ሲሆን ስምምነቱ እንዲታደስለት አመልክቷል።

Next Post
  • News

<strong>IWPG Hosts 'the 5th International Loving Peace Art Competition' Exhibition at the African Union</strong> - IWPG Global Region 2 African high-ranking officials respond enthusiastically

Ayele Addis July 20, 2024

The International Women’s Peace Group (IWPG) Global Region 2 (Regional Director Seo-Yeon Lee) held an exhibition of the winning works from the ‘5th International Loving Peace Art Competition’ on the 4th and 5th of this month at the African Union (AU) headquarters in Addis Ababa, Ethiopia. The exhibition took place in the main corridor of […]

Related Post

  • News

The First Ethiopian Community Radio Station FM 92.3 Kore Community Radio,

Ayele Addis January 10, 2024January 10, 2024

FM 92.3The Kore community radio, FM 92.3 went on air transmitting its programme in Korrettie, the language of the Kore community. Review by Ayele Addis Ameblu Kore Community Radio The Kore community lives in Amaro Special Woreda in the Southern Nations Nationalities and Peoples Regional State (SNNPR).The Woreda has a total land area of 1710 […]

  • AFRICA
  • Election & Democracy
  • FEATURED
  • General
  • Latest
  • Magazine
  • News
  • Politics
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

Ayele Addis November 19, 2026November 19, 2026

የሀገሪቱ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ የታሪካዊ በደሎችን ለመፍታትና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት ተስፋ ቢሰጥም፣ የሂደቱ ተዓማኒነት በተግባራዊ አፈጻጸም፣ በተጎጂዎች ተሳትፎና በነጻ ጋዜጠኝነት ላይ ይወሰናል። አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ | ህዳር 10፣ 2019 by Meseret Abebe Abay ኢትዮጵያ ከታሪካዊ በደሎች፣ ከተደጋጋሚ ግጭቶችና ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የተነሳ የተከማቹ ችግሮችን ለመፍታት የሽግግር ፍትህን እንደ ብሔራዊ መፍትሔ ስትወስድ ቆይታለች። ይሁን እንጂ አንድ […]

  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • Education
  • FEATURED
  • General
  • Journalism and Communication
  • Latest
  • Magazine
  • Media Litracy
  • News
  • Special Edition

Ethiopian Journalists Face Increasing Threats: A Comprehensive Analysis on Safety and Security

Ayele Addis September 25, 2024April 21, 2025

The graphic illustration representing the challenges faced by Ethiopian journalists. The image visualizes the dual threats from state and non-state actors, legal complexities, and digital dangers. It captures the perilous environment for journalism in Ethiopia while highlighting both physical and digital threats.

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • ዜና
  • ልዩ ዕትም
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress