
ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት “የጋዜጠኞችን ደኅንነት በማስጠበቅ ሥራቸውን ከፍርሃት ነፃ ሆነው” የሚሠሩበት እድል እንዲፈጠር እሰራ ነው መሆኑን የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ ወ/ሮ ትዕግስት ይልማ ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ የፀጥታ መናጋት እና ቀውስ መቀጠሉን ፣ ጦርነት ብሎም የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ድንጋጌ ከመኖሩ ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ጋዜጠኞች ባለፈ፣ የማህበራዊ መገናኛ ዐውታሮችን ተጠቅመው በመንግሥት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ፣ በመረጃ ትንተና የሚሳተፉ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ሲታፈኑ፣ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ተስተውሏል።

ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በአሁኑ ስዓትም 82 የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትንና ማህበራትን በአባልነት ማቀፉን ያስታወቀው “የጋዜጠኞችን ደኅንነት በማስጠበቅ ሥራቸውን ከፍርሃት ነፃ ሆነው” የሚሠሩበት እድል እንዲኖር ከፌድራል ፖሊሲ እና ከፍትህ ተቋማት ጋር ከስራቸው ጋር በተገናኘ የሚደረግ ህገወጥ እስርን ለማስወገድ እየሰራ መሆኑ ተገልፆዋል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ የሚዲያ ባለሙያዎቭ እና የምክር ቤቱ አባላት ጋዜጠኝነት አሁን ላይ ፈተና ላይ ስለመውደቁ ይታመናል። የምክር ቤቱ አባል ተቋማትም በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያለፉ መሆናቸውን ገልፀዋል።
“የምክርቤታችን አባላት ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ውስጥ በመግባታቸው ፣ የኅትመት ዋጋ በመናሩ እና መገናኛ ብዙኃን እስከ መዘጋት የሚደርስ ችግር ውስጥ መውደቃቸው እንዲሁም የሳተላይት ክፍያ በመጨመሩ ሳቢያ አብዛኞቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ ይገኛሉ”።የጋዜጠኞች የመታሰር እና የመፈታት ሁኔታ በጎ የመሻሻል አዝማሚያ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም አሁን “እያሽቆለቆለ” እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ጋዜጠኞችና የሕትመት ውጤቶት በፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ መታገታቸው እንዳሳሰበው ከዚህ በፊት የጠየቀው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እርምት እንዲደረግ መጠየቁ ይታወሳል።
በዚህ ወቅት ተጽዕኗቸው ጎልቶ የሚታየው የበይነ መረብ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ትንተናዎች እና ዘገባዎች ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችም ይሁን ድርጅቶች በደረሰባቸው ማስፈራራት፣ ቢሮ ተሰብሮ ዘረፋ ፣ ዛቻ እና መሰል ጉዳዮች ከሙያው የመራቅ፣ የመታሠር አልያም ሀገር ጥሎ ለመሰደድ ፈተና ተጋፍጠዋል።መሠል ችግሮችን ይፈታል ተብሎ እምነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የፈረመው የግልግል ዳኝነት ተግባራዊ አለመሆኑ አንዱ ችግር አባባሽ ጉዳይ መሆኑን አቶ አማረ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የመረጃ ነፃነት ዐዋጅ እንዲፀድቅ እንደሚሰራ እና ወደፊትም የሚዲያ ህጉ እንዲከበር የመግባቢያ ስምምነቶችን ለመፈራረም ከፌድል ፖሊሲ እና ከፍትህ ሚንስት ጋር መግባባት መድረሱን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር በተገናኘ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ፣ የማህበራዊ መገናኛ ዐውታሮችን ተጠቅመው በመንግሥት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ፣ በመረጃ ትንተና የሚሳተፉ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚሠሩ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ሲታፈኑ፣ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ታይቷል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ጋዜጠኞችና የህትመት ውጤቶት በፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ መታገታቸው ፣ መያዛቸው ፣ መለቀቃቸውና ዳግም መታሰራቸው ተደጋግሞ ታይቷል።
በቅርቡ በርካታ ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው መሰደዳቸውን አስታውቀው ነበር።
በአጠቃላይ፣ ሲፒጄ ህዳር 21፣ 2016 ባደረገው ቆጠራ በዓለም ላይ 320 ጋዜጠኞች እስር ላይ እንደነበሩ ዘግቧል። ይህ ቁጥር በ1985 በሲፒጄ ቆጠራ ከተጀመረ ወዲህ ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር የሁለተኛነትን ደረጃን ይዟል። ይህ ደግሞ፣ ስር የሰደደ የአምባገነንነት እና የመንግስታት የነፃነት ድምፆችን አፋኝነት የሚያሳይ አሳሳቢ መመዘኛ ነው። አንዳንድ መንግስታት፣ ከራሳቸው ድንበር አልፈው አንድ እርምጃ ወደ ፊት በመሄድ፣ ጋዜጠኞችን ለማስፈራራት እና ለማዋከብ፣ የድንበር ዘለል የጭቆና ዘዴ ይጠቀማሉ። ሞስኮ የተጠቀመችባቸው የማስፈራሪያ ድርጊቶች በሌሎች ሀገሮች የሚኖሩ የሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ ተከታታይ የእስር ማዘዣዎችን ማውጣትን ያካትታሉ፤ ኢትዮጵያም በጎረቤቷ ጅቡቲ በስደት ይኖር የነበርን ጋዜጠኛ እንዲታሰር ካስደረገች በኋላ፣ በግድ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ የሽብርተኝነት ክስ እንዲመሰረትበት አድርጋለች።
በተጨማሪም፣ የሲፒጄ ጥናት እንደሚያሳየው በቆጠራው ውስጥ ከተዘረዘሩት ክሶች ውስጥ፣ ከ65% (209) በላይ የሚሆኑት ታሳሪ ጋዜጠኞች፣ መንግስትን የሚተቹ የዜና ሽፋን በማቅረባቸው፣ የሃሰት ዜና ማሰራጨትና የሽብርተኝነት የመሳሰሉ የፀረ-መንግስት ወንጀሎች፣ በበቀል መልክ፣ ክስ እንዲመሰረትባቸው ያደርጋል። ከ67 የክስ መዝገቦች ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች የተከሰሱበት ጉዳይ፣ እስካሁን አልተነገራቸውም። ብዙውን ጊዜ፣ ያለምክንያት ጭካኔ የተሞላባቸው ክስተቶች ያጋጥሟቸዋል፤ ብዙ ጊዜ የክስ ሂደቱን በማዛባት፣ ባለስልጣናት የቅድመ-ክስ እና የጋዜጠኞችን ቅድመ-ችሎት እስራት ሲያራዝሙ ይታያል፤ በጋዜጠኞች ጠበቆች ላይም በዓለም ዙሪያ የበቀል እርምጃ ሲወስድባቸው ይስተዋላል።
በአገራችን በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ሕጋዊ ዕውቅና አግኝተው በሥራ ላይ ያሉ ሚዲያዎች በህዝብ፣ በንግድና በማህበረሰብ ባለቤትነት የተያዙ ሲሆን ብዛታቸውም 168 ይደርሳል፡፡ እነርሱም 10 የህዝብ ሬዲዮና 12 የህዝብ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣15 የንግድ ሬዲዮና 26 የንግድ ቴሊቪዥን ጣቢያዎች፣ 54 የማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣ እንዲሁም 3 የትምህርት መገናኛ ሬዲዮ ሲሆኑ የህትመት መገናኛ ብዙኃንን በተመለከተም 13 ጋዜጦችና 10 መጽሔቶች በፌደራልና በክልል መንግሥታት ደረጃ ይታተማሉ፡፡ በተጨማሪም 13 ጋዜጦችና 12 መጽሔቶች በግሉ ሴክተር እየታተሙ በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሀገሪቱ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የራስ በራስ ማስተዳደር እንዲችሉና ሕዝባዊ ተጠያቂነትና ግልፅነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ከማድረጉም በላይ የመገናኛ ብዙሃንን ነፃነትን ለመጠበቅና ለማስፋፋት ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡ መሆኑም ምክር ቤቱ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም የተመሠረተበትን ዓላማ ለማሳካት እንዲችል በአጭር ጊዜ ዕቅድ በማውጣት የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን ይገባዋል፡፡ ለዕቅዱም መነሻ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ የምክር ቤቱን ዓላማዎች በተሳለጠ መንገድ መተግበር ይቻላል፡፡ እነዚህ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎች በሥራ ላይ የዋሉት ደግሞ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ በሚባሉት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29 የፕሬስና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ በተመሠረተው የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ 590/ 2000 መሠረት ነው፡፡ ይህንን የሕግ ማእቀፍ መነሻ አድርገው የሚዲያ ድርጅቶችም ሆኑ ሙያተኞች በከፍተኛ ሙያዊ ሥነ ምግባርና ብቃት ነፃ፣ ገለልተኛና ህብራዊ የመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ሒደት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ያላቸው የተለያዩ የሚዲያ ድርጅቶችና የጋዜጠኞች ማህበራት ተዋቅረዋል፡፡
ከዚያም አልፎ ወጥ በሆነ የሥነ ምግባር ደንብ የሚመራ፣ ጠንካራ አገር አቀፍ ሚዲያ ካውንስል መመስርቱ አስፈላጊና ጠቃሚ ነበር፡፡ ከአድካሚ ውጣ ውረድ በኋላ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እውን ሊሆን የቻለውም በዚሁ መነሻ ነው፡፡ በመቀጠልም የመገናኛ ብዙኃን ካውንስሉ ራሱን ችሎ እንዲቋቋም የተለያዩ የጋዜጠኞች ማኅበራት፣ የአሳታሚዎችና የብሮድካስተሮች ማህበራት፣ እንዲሁም የሚዲያ ድርጅቶች በመሰብሰብ ከብዙ ውጣ ውረድና ክርክር በኋላ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤትን በ2008 ዓ.ም. ለመመሥረት ችለዋል፡፡ ሆኖም በወቅቱ የነበረው የሲቪክ ማህበራት ሕግ አካታች አንቀጽ የለውም በሚል ሰበብ ምክር ቤቱ ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ሊመዘገብ አልቻለም ነበር ፡፡ይህ ምክር ቤት ህጋዊ እውቅና አግኝቶ ወደ ሥራ ሲጋባ በአሁኑ ወቅት የያዛቸው የሚዲያና የጋዜጠኞች ማህበራት ብዛት 52 ሲሆኑ፣ የአባላቱ ዝርዝርና የተሰማሩበት ዘርፍን በሚመለከት የቴሊቭዥንና የሬዲዮ ጣቢያ ያላቸው 10፣ ቴሊቪዥን ጣቢያ ብቻ ያላቸው 7፣ ሬዲዮ ጣቢያ ብቻ ያላቸው 7፣ ህትመት ላይ የተሰማሩ 18 ሲሆኑ የጋዜጠኞች ማህበራት፣ የብሮድካስተርና የአሳታሚዎች ማህበራት ደግሞ 4 ናቸው ፡፡ በየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ስር 16 የግልግል ዳኞች ይገኛሉ፡፡
ከለውጡ በኋላ ግን በ2011 ዓ.ም. በተሸሻለው የሲቪክ ማህበራት አዋጅ መሠረት ጉዳዩ በድጋሚ ታይቶ፣ ሰኔ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ምክር ቤቱ በሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ኤጄንሲ ሕጋዊ ፈቃድ አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ለፖለቲካዊ፣ ለማኅበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያደርግ፣ ጥራቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽ፣ በሃላፊነት ስሜት የሚንቀሳቀስ እና ነፃነቱ የተረጋገጠ አስተማማኝ የመገናኛ ብዙሃን እንዲስፋፋ የማድረግ፣ የሚዲያውን አቅም የመገንባት እና የመቆጣጠር አላማን ይዞ ልዩ ልዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ከነዚህ ስራዎች ውስጥ አንዱም መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን በራሳቸው የሚቆጣጠሩበትን ስልት መቀየስና መደገፍ ሲሆን በቅርቡም በአገራችን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ተቋቁሟል፡፡
የጋዜጠኝነት፣ የአክቲቪስትነትና የጦማሪነት ሁኔታ
የጋዜጠኝነት መምህር እንደመሆንዎ በአሁን ወቅት ያለውን የጋዜጠኝነት፣ የአክቲቪስትነትና የጦማሪነት ሁኔታ እንዴት ያዩታል? ፕ/ር ዘነበ ክንፈ ይባላሉ፡፡ በሩሲያ የወዳጅነት ዩኒቨርሲቲ (Russian FriendShip University) የጋዜጠኝነት መምህር; ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መምጣቱን ተከትሎ፣ በጋዜጠኝነት ላይ የመጡ አዳዲስ ባህሪያት በራሳቸው አከራካሪ ናቸው፡፡ ጋዜጠኛ ማን ነው? አክቲቪስት ማን ነው? ጦማሪ ማን ነው? የሚለው አሁንም ድረስ በአለማቀፍ ደረጃ አከራካሪ ነው፡፡ የተለያዩ አገራት እነዚህን […]