በአብክመ የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስተባባሪነት ከተለያዩ አካባቢዎች ለመጡ የሚድያ ባለሙያዎች ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
ሪፖርተር ፦ በእውቀቱ ይደግ
በመድረኩ የአብክመ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ሞገስ፣ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ማሩ ቸኮል የተረማ ለሚዲያ ባለሙያዎች ግንዛቤ የሚያስጨብጥ “ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ የሚድያ ባለሙያዎች ሚና” በሚል ለአማራ ሚድያ አሶሴሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበት ስልጠና እና የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል።
በአብክመ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ሞገስ በመክፈቻ ንግግራቸው ትውልድን በስነ ምግባር ኮትኩቶ ከማሳደግ አንፃር ሰፊ ስራዎችን እንተደሰራ እና ወደፊትም በዚህ ረገድ ትልቅ ስራዎችን እንደሚሰሩ ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪ ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንደ ተቋም ትውልድን በስነምግባር ኮትኩቶ ከማሳደግም በላይ የሙስና መከላከል አሰራር ስርዓት ግንባታን ለማህበረሰቡ ታች ድረስ ወርዶ እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል። ሌላው አቶ ዘላለም በመድረኩ ሲናገሩ አስቸኳይ ሙስና መከላከል በእኛ ተቋም በሰፊው የሚሰራ ስራ ነው ያሉ ሲሆን ይህ ማለት ግዥ ፣ ጨረታ፣ ገቢ እና ወጭን የተመለከቱ ሂደቶች ሲፈፀሙ በአስቸኳይ ከሙስና እና ብልሹ አሰራሮች ምን ያክል የፀዱ ናቸው የሚለውን ይከታተላል ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነር አቶ ማሩ ቸኮል አክለውም ኮሚሽኑ ሀብት መመዝገብና ማጣራትም የሚሰራቸው አንኳር ጉዳዮች እንደሆኑ ጠቅሰው በተለይ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች የሀብት ምንጫቸው በተገቢው ሁኔታ ሳይታወቅ ከሚያገኙት ገቢ ጋር ያልተጣጣመ ሀብት ሲያከማቹ ይስተዋላል ይህ ደግሞ በአግባቡ የሀብት ምዝገባና ቁጥጥር ካለመስፋፋቱ ጋር የመጣ ችግር ነው ብለው ወደፊት ከሚድያ ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን የማጣራት ስራ እናከናውናለን ብለዋል።
የሚድያ ባለሙያዎች የስራ ስነምግባርን በጠበቀ መልኩ ቢሰሩ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከመታገል አንፃር አሰፈላጊ ነው ያሉት ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ሞገስ ፤ በተለይ በጋዜጠኞች እና በሚድያ አሰራር ውስጥ 5 ወርቃማ የስራ ስነምግባሮች እንዳሉ አስታውሰዋል። ከነዚህ ውስጥ እውነተኝነት እና ሀቀኝነት የመጀመሪያው እና መሰረታዊ መርህ መሆኑን አንስተዋል ። ለአብነት ታዋቂው ጋዜጠኛ ፑልቲዘር በእያንዳንዱ የጋዜጠኝነት ስራዎች ውስጥ ስለእውነተኝነት ደጋግሞ እንደፃፈ ገልፀዋል። የዲጅታል ሚዲያው አለም አሁን ከተቋም በላይ ህዝቡን በቀላል የምናገኝበት እና ለስነ ምግባር ግንባታ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ልንጠቀምበት የሚገባ መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡

በእያንዳንዱ የጋዜጠኝነት ስራዎች ውስጥ ከእውነተኝነትና ሀቀኝነት እኩል ሚዛናዊ ዘገባን ማካተት ተገቢ እንደሆነም አፅንኦት ሰጠው ተናግረዋል። ሚዛናዊ ዘገባ ማለት በአንድ ዜና ወይም ፅሁፍ ውስጥ ለሁለት ጉዳዮች እኩል የሆነ ሽፋን መስጠት ነው። ከዚህ በተጨማሪ በጋዜጠኝነት ስራ ውስጥ ሰብአዊነት በጉልህ ሊከበር እንደሚገባ ተናግረዋል። ከሰብዓዊ ማንነትና መገለጫዎች ያፈነገጡ ዜናዎችን በተቻለ መጠን ላለመስራት ሞክሩ ሲሉም ወጣት ጋዜጠኞችን ትምህርት ሰጠዋል።
አቶ ዘላለም በመድረኩ ትምህርት ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል የሙስና እና ብልሹ አሰራር መንስኤዎች ያሏቸውን ለተሳታፊዎች ገልፀዋል። ከነዚህ ውስጥ በዋናነት የስነምግባር ጥሰት፣ የማህበረሰቡ ስነምግባር እና ግብረገብ ትውፊቶች መሸርሸር፣ የአስተምህሮ ተቋማት መላላት ፣ ለሙስና መከላከል ትኩረት አለመስጠትና የሚድያ መርሆች አለመከበር አንኳር የሆኑ መንስኤዎች ናቸው ብለዋል።
ለሙስና መከላከል ትኩረት አለመስጠት ለብልሹ አሰራሮች መስፋፋት ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ የገለፁት አቶ ዘላለም ፤ ይህ ማለት የሙስና እና ብልሹ አሰራርን ጉዳይ ለአንድ ተቋም ወይም ለፀጥታ አካላት ብቻ የመስጠት አዝማሚያ ይስተዋላል ። ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ሲዘረፉ ዝም ማለት፣ አድሎአዊ አሰራር ሲከሰት በእኔ ምን አገባኝነት ችላ ብሎ ማለፍ እና እኔን የሚመለከት አይደለም ማለት ለችግሩ መባባስ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።
ስለ ችግሩና መንስኤዎች ከማውራት በዘለለ ምን አማራጭ መፍትሄዎች አሉ የሚሉትንም የገለፁት አቶ ዘላለም ፦ በዋናነት ራስን ለሙስና እና ብልሹ አሰራሮች ተባባሪ ከመሆን መቆጠብ ብሎም ሁነቱን ማጋለጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ በአስተሳሰብ ራስን መለወጥና በሌሎች ውስጥ ለማስረፅ መሞከር ፣ ሚድያዎች ከስነምግባር እና ግብረገብ ትምህርቶች ጋር አጣምሮ መስራት እንዲሁም በተናጠል ከመስራት በቡድን መስራትን መምረጥ የተሻሉ የመፍትሔ ሀሳብ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተለያዩ ጥያቄዎችንና ማሳሰቢያዎችን ያነሱ ሲሆን ለአብነት ዶ/ር ነገሰ በላይ ይህንን የመሰለ የውይይትና የመማማሪያ መድረኮች መዘጋጀታቸው መልካም ናቸው ያሉ ሲሆን በዋናነት የሚድያ ባለሙያዎች መጥፎ ስራዎችን የሚሰሩ ሰዎችን ከማጉላት በተሻለ በጎ ስራዎችን የሚሰሩ ሰዎችን ለማህበረሰቡ ማሳወቅና ተምሳሌት እንዲሆኑ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል።
አቶ አዝዛቸው ወንዴ በበኩላቸው መድረኩ ትልቅ ተሞክሮዎች የቀረቡበትና ለበርካታ የዲጂታል ዘመን ጋዜጠኞች ትምህርት የሚያስጨብጥ መሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ኮሚሽኑ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፣ ከሚድያዎች ጋር በጋራ በመሆን ሙስናና ብልሹ አሰራርን መዋጋት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም የአብክመ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ማሩ ቸኮል በተነሱ ሀሳቦች ዙሪያ የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጠዋል። አቶ ማሩ በማጠቃለያ ንግግራቸው በተለይ ኮሚሽኑ በቀጣይ በማህበረሰቡ ላይ ስለተንሰራፋው የሙስናና ብልሹ አሰራሮች ዙሪያ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ የሚድያ ባለሙያዎች ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከመዋጋት ረገድ እስካሁን እዚህ ግባ የሚባል ስራዎች እንዳልሰሩ የተናገሩ ሲሆን ወደፊት አብረን መስራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

የአማራ ሚድያ እና አርት አሶሴሽን ይህ መድረክ እንደ ትልቅ አጋጣሚ ሊታይ የሚችልና በርካታ ተሞክሮዎችን፣ ትምህርቶችንና መሰል ገለፃዎችን ያገኘንበት ነው በተለይ ደግሞ ወጣት ጋዜጠኞች ወደፊት በሚኖራቸው ስራ ሙስናን ከመዋጋት አንፃር እንደ ትልቅ የማንቂያ ደወል የሚሆን መድረክ ነው ብለዋል። እንደነዚህ አይነት መድረኮች በቀጣይም በስፋት ቢሰሩ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከብልሹ አሰራር ማዳን እንደሚቻልም ተናግረዋል።
በአብክመ የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስተባባሪነት በዲጅታል ሚዲያ መጠቀም የስነ ምግባር ግንባታን ለማጠናከር እና የፀረ ሙስና ትግልን ለማስፋት ያለመ የግንዛቤ መድረክ ተካሄደ። መድረኩ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰበሰቡ የሚዲያ ባለሙያዎችን በአንድ ላይ በማቀላጠፍ ሙስናና ብልሹ አሰራር ላይ የሚዲያው ሚና ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ በትልቅ አፅንኦት ያቀረበ ነበር።
የመድረኩ ዋና ዓላማዎች
- ዲጅታል ሚዲያን በመጠቀም የስነ ምግባር ትምህርትን ለህብረተሰቡ በስፋት ማድረስ
- የፀረ ሙስና ትግል ውስጥ የሚዲያ ባለሙያዎች አጋርነትን ማጠናከር
- በጋዜጠኝነት ስራ ውስጥ ስነ ምግባርና ሙያዊነትን ማበረታታት
- በሙስና መከላከል ሂደት የህብረተሰቡን ንቁ ተሳትፎ ማበረታታት
የኮሚሽኑ መልዕክት
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ሀብታሙ ሞገስ በክፍት ንግግራቸው ትውልድን በስነ ምግባር ኮትኩቶ ማሳደግ የተቋሙ ቀዳሚ ተልዕኮ መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ በላይ ዘላቂ የሙስና መከላከል አሰራር ስርዓት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በተለይም በግዥ፣ ጨረታ፣ ገቢና ወጪ ሂደቶች ውስጥ አስቸኳይ ክትትል በማድረግ ሂደቶቹ ከሙስና ነፃ እንዲሆኑ እንደሚሰራ ተጠቅመዋል።
ምክትል ኮሚሽነር አቶ ማሩ ቸኮል በበኩላቸው የሀብት ምዝገባና ማጣራት ኮሚሽኑ ከሚሰራቸው አንኳር ተግባራት መካከል መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ከተገኘ ገቢ ጋር ያልተጣጣመ የሀብት ክምችት በህብረተሰቡ ውስጥ እየታየ መሆኑን ገልጸዋል። ይህን ችግር ለመቅረፍ ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በጋራ የማጣራት ስራ ለመስራት ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
የሚዲያ ሚና እና 5 ወርቃማ መርሆች
ኮሚሽነር አቶ ሀብታሙ ሞገስ በጋዜጠኝነት ስራ ውስጥ የሚጠበቁ አምስት ወርቃማ የስነ ምግባር መርሆችን አስታውሰዋል፤
- እውነተኝነትና ሀቀኝነት – መሰረታዊ መርህ
- ሚዛናዊነት – በዜና ውስጥ ሁለቱንም ወገኖች እኩል ማቅረብ
- ተጠያቂነት – ለህዝብ ታማኝ መሆን
- ሰብአዊነት – የሰው ክብርና መብት ማክበር
- ሙያዊ ነፃነት – ከፖለቲካና ከግል ጥቅም ግፍ መርቀቅ
እንደ ምሳሌ ታዋቂው ጋዜጠኛ Joseph Pulitzer በስራው ውስጥ እውነተኝነትን እንደ ከፍተኛ መርህ ማድረጉ ተጠቅሷል። ይህ አስተምህሮ ዛሬ በዲጅታል ሚዲያ ዘመን ይበልጥ አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።

የሙስና መንስኤዎች
በመድረኩ የተጠቀሱ ዋና ዋና መንስኤዎች፦
- የስነ ምግባር ጥሰት
- የማህበረሰብ ግብረገብ መሸርሸር
- የትምህርት ተቋማት ድክመት
- የሙስና ጉዳይን ለአንድ ተቋም ብቻ መተው
- የሚዲያ መርሆች አለመከበር
የተጠቀሱ መፍትሄዎች
- ራስን ከሙስና ተባባሪነት መጠበቅ
- ብልሹ አሰራርን ማጋለጥ
- በአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት
- ሚዲያን ከስነ ምግባር ትምህርት ጋር ማጣመር
- በተናጠል ከመስራት በቡድን መስራት

የተሳታፊዎች አስተያየት
ተሳታፊዎች መድረኩን እንደ ጠቃሚ የመማማሪያ እና የልምድ ልውውጥ አጋጣሚ ገልጸው፣ በተለይ ወጣት ጋዜጠኞች ሙስናን በመታገል ረገድ ንቁ ሚና እንዲወስዱ እንደ “ማንቂያ ደወል” እንደሚያገለግል ጠቅሰዋል። እንዲሁም የአማራ ሚድያ እና አርት አሶሴሽን ይህን መድረክ እንደ ትልቅ ዕድል በመቁጠር ተመሳሳይ ፕሮግራሞች በቀጣይ እንዲስፋፉ ጠይቋል።
መደምደሚያ
መድረኩ የሚዲያ ተቋማትን ከፀረ ሙስና ተቋማት ጋር በማቀናጀት ዲጅታል መሣሪያዎችን በስነ ምግባር ግንባታ እና በሙስና መከላከል ሂደት ውስጥ በተወሰነ ደረጃ ለመጠቀም ግንዛቤ የፈጠረ ነው። ኮሚሽኑ ከሚዲያ፣ ከሲቪል ማህበረሰብ እና ከትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ በቀጣይ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

RIGHT WATER FACTORY Pure • Safe • Trusted Commercial Advertisement for Customers
Are you looking for clean, safe, and refreshing drinking water for your family, office, or business? Right Water Factory proudly provides high-quality purified bottled water produced under strict hygiene and quality control standards. Every drop is carefully treated, filtered, and packaged to ensure purity, freshness, and safety. ✔️ Crystal clear✔️ Hygienically processed✔️ Safe for all […]