DPIJournalism #DPIFellows2025 For the CIPESA DPI Journalism Fellowship, Eastern Africa By Ayele Addis
የተገልጋዮችን እንግልት ለመቀነስም 800 አይነት የመንግስት አገልግሎቶች ወደ ዲጅታል መቀየራቸውን ገልፀዋል፡፡ዜጎች እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ድረስ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ ብሔራዊ ባንክ ከሰሞኑን ጥሪ ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡
ኢትዮጵያ ለእያንዳንዱ ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ እምነት የሚጣልበት እና ሁሉን አቀፍ የዲጂታል አገልግሎቶችን ማግኘት የሚያስችል ብሔራዊ መታወቂያ እየሰጠች ትገኛለች፡፡ለሁሉም አገልግሎቶች አስፈላጊ የሆነውን ብሔራዊ መታወቂያ እስካሁን ከ29 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ወስደዋል ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የብሔራዊ መታወቂያ አስተባባሪ አቶ ደጄኔ ገብሬ ጠቁመዋል፡፡አቶ ደጄኔ ከኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ቁጥር 90 ሚሊዮን ለማድረስ እየተሰራ ነው፡፡ይህን ለማሳካትም በሁሉም ክልሎች ባሉ ወረዳዎች እድሜያቸው ከአምስት ዓመት ጀምሮ ያሉ ዜጎች እንዲመዘገቡ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ፋይዳ የሚል ስያሜ ያለው የኢትዮጵያ ዲጅታል መታወቂያ ቴክኖሎጅውን በማስፋፋት ለዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚያግዝም አቶ ደጄኔ ተናግረዋል፡፡ዲጅታል ቴክኖሎጅው ደግሞ የመደመር መንግስት እሳቤ የሆኑትን መፍጠር፣ መፍጠን እና መዝለልን ከግብ ለማድረስ የሚረዳ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ በተለመደው አካሄድ ወደ ከፍታ መሻገር አይቻልም ያሉት አስተባባሪው ያሉን ነገሮች ላይ ፈጠራ በማከል በፈጣን ጉዞ ሀገራችንን ማሳደግ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ እንደ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያሉ ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀምም አላስፈላጊ ሂደቶችን በመዝለል፤ አለም የደረሰበት ደረጃ መድረስ እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚቻል አክለዋል፡፡ የአንድ መሶብ አገልግሎትን በሁሉም ክልሎች በማስፋፋት ከ40 በላይ ተቋማት በአንድ ቦታ አገልግሎቶችን መስጠት መጀመራቸውም ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያግዝ ነው ሲሉ ለአብነት አንስተዋል፡፡
“በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሰራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ለዚህ ቁርጠኝነታቸን አንዱ ማሳያ የሆነውን የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከልን ዛሬ መርቀናል።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ለመሆኑ መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ምንድን ነው? በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶችስ የትኞቹ ናቸው? ስለሚሉትና ፋይዳውን በተመለከተ በፅሁፉ ተዳሷል። መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር ምርጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው። የአሰራር ስርዓቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያስቀር መላ ነው፡፡ አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት 12 የፌደራል መንግስት ተቋማት የተቀላቀሉ ሲሆን 41 የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችንም አቅርበዋል፡፡
እነዚህም ፦
1. የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
2. የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
3. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሌት
4. የገቢዎች ሚኒስቴር
5. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
6. የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8. የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
9. የትምሀርት ምዘና እና ፍተናዎች አገልግሎት
10. የኢትዮ ፖስታ
11. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12. ኢትዮ ቴሌኮም ናቸው።
ሀሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡም ይገኛሉ።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያሥላሴ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ ማዕከሉ የመንግስት አገልግሎትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያቀላጥፍ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ማዕከሉ የተቀናጀ አገልግሎት ለተገልጋዩ መስጠት የሚያስችል ትልቅ ውጤታማ ስራ መሆኑንም ገልጸው፤ ማዕከሉን በማደራጀት ወደ ስራ መገባቱ በሀገሪቱ የታለመውን ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ማዕከሉ ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩ አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል በማስገባት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ትልቅ እርምጃ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ትልቅ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለብዙ ግዜ በመንግስት ተቋማት የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን እንደሚፈታ ተናግረዋል፡፡
ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ የያዘ ትልቅ ተቋም መሆኑን ገልጸው፥ ሥራዎች በአግባቡ ከተመሩ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያስመሰከረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መንግስት ለሰው ተኮር አገልግሎት የሰጠው ትኩረት የተግባር ማረጋገጫ ማዕከል እንደሆነ የጠቀሱት ሚኒስትሮቹ፤ ህብረተሰቡ ባልተንዛዛ ቢሮክራሲ እንዲሁም በተቀላጠፈ መንገድ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
በአጠቃላይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሀገሪቱ የአገልግሎት አሰጣጥ እንደ ታሪክ እጥፋት የሚቆጠር ትልቅ ስራ መሆኑን ማስታወቃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
አገልግሎትን ከማዘመን ባለፈ ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስለው ማዕከሉ፤ ለጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥም ተሞክሮ የሚወሰድበት እንደሆነም አብራርተዋል።
Amplifying Ethiopia’s Voices — From Grassroots to National Impact
EMMA NEWS – Ethiopian Mass Media Action is where Ethiopian stories come alive. We are a powerhouse of media development, content production, training, research, and consultancy, proudly working hand-in-hand with grassroots community radio stations and national media institutions across Ethiopia. What We Do Transform local stories into national conversations Train and empower journalists, producers, and […]