Skip to content
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • Latest

በኢትዮጵያ ሕጋዊ ነዋሪ ለሆኑ ሁሉ ይሰጣል የተባለው ዲጂታል መታወቂያ ምንድን ነው?

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መጪው የምርጫ ሂደት ሁሉን ያካተተ፣ ሕጋዊ፣ ግልጽ እና ተዓማኒ እንዲሆን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና እንዳላችው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።

  • AFRICA
  • Latest
  • Radio & TV
  • Technology

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስተኛውን እጅግ ፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ገንብቶ ሥራ አስጀመረ!

Ayele Addis November 29, 2025November 29, 2025

ዛሬ ሰሚት ፍየል ቤት አካባቢ ስራ የጀመረው ሦስተኛው ጣቢያ በአንድ ጊዜ 16 እጅግ በጣም ፈጣን መሙያዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም ያሉንን የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች የማስተናገድ አቅም በእጅጉ ከፍ ለማድረግ ያስችላል፡፡በመርሃግብሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ “ይህ ኢኒሼቲቭ፤ ሀገራችን በዲጂታል ጉዞ እያደረገች ያለውን ሁለገብ ለውጥ፣ በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር እና ዘላቂነት ያለው አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት በኩል ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላትን ተምሳሌትነት ያሳየንበት ነው“ ብለዋል፡፡

አክለውም “በሀገራችን የኤሌክትሪክ መኪኖች በሰፊው እየተለመዱ መምጣታቸውን ተከትሎ ስነ-ምህዳሩንም በአረንጓዴ መሰረተ ልማት መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ፣ እነዚህን የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች በአጭር ጊዜ ገንብተን ስራ ላይ እንዲውሉ አድርገናል” ብለዋል፡፡

ጣቢያው የአውሮፓ ስሪት የሆኑ መኪኖችን ጭምር ኃይል መሙላት የሚያስችል እጅግ ፈጣን አቅም ያለው ሲሆን፤ ኃይል ቆጣቢ፣ ከፍተኛ ፍጥነት ያለውና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰራ በመሆኑ፣ ባትሪዎች በሚችሉት ፍጥነት ዘላቂነት ባረጋገጠ መልክ ቻርጅ ያደርጋል፡፡ኩባንያችን ቀደም ሲል በአንድ ጊዜ 32 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችሉ ጣቢያዎችን ወደ ስራ ያስገባ ሲሆን፣ ከየካቲት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ165 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪኖች፣ 4,349,761.54 ኪሎዋት/ሰዓት ኃይል መሙላት ችሏል፡፡ይህም የአየር ብክለትን ከመከላከል አንጻር ሲታይ 6,081,447.62 ኪ.ግ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ ማድረግ የቻለ ሲሆን፣ ይህም ከ30,444 በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር ይነጻጸራል።ኩባንያችን አገልግሎቱን በስፋት ተደራሽ በማድረግ የሀገራችንን የዲጂታል ኢኮኖሚ በአረንጓዴ እና ታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂዎች በመደገፍ ለዘላቂ እድገት ቁልፍ ሚና መጫወቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ስማርት ቴክኖሎጂ

በጣቢያዎቹ የተገጠሙት 16 እጅግ ፈጣን (Super-Fast) የኃይል መሙያዎች፤ እያንዳንዳቸው እስከ 180 ኪሎዋት በሰዓት የሚደርስ የመሙላት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ ይህም ተሽከርካሪዎችን በከፍተኛ ፍጥነት ቻርጅ ለማድረግ ያስችላል፡፡

ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ በዘርፉ የመጨረሻው የልህቀት ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋና ባህሪያት አሉት፡-

  • ስማርት አገልግሎት፡ሲስተሙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በመታገዝ፤ የተሽከርካሪዎችን የባትሪ ዓይነት እና የደንበኛውን ትዕዛዝ አስቀድሞ በመተንተን (Charging after diagnosing/analyzing) ራሱን በማስተካከል አገልግሎት ይሰጣል፡፡
  • የባትሪ ደህንነት፡ምንም ዓይነት የኃይል ብክነት የሌለው (Zero energy loss)፣ ከፍተኛ ብቃት ያለው እና ከስህተት የጸዳ (Zero error) ሲሆን፤ ባትሪን የመንከባከብ (Battery maintaining/restoring) አቅም አለው፡፡
  • በቀላሉ የሚዘምን (Scalability):ጣቢያዎቹ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በፍጥነት አቅማቸውን ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ የተገነቡ በመሆናቸው፣ እንደ አስፈላጊነቱ በማንኛውም ጊዜ ማስፋፊያ ወይም ማሻሻያ ለማድረግ ያስችላል፡፡

ወጥና ተጣጥሞ የሚሄድ የዲጂታል ቻርጂንግ ተሞክሮ በቴሌብር

  • የቻርጅማድረጊያጣቢያው 24/7 አገልግሎትየሚሰጥሲሆን፣ሙሉበሙሉየሚሰራውበቴሌብርሱፐርአፕላይበሚገኝመተግበሪያነው፡፡
  • የአገልግሎትክፍያተገልጋዮችፈጣን፣ቀላል፣ምቹናአስተማማኝበሆነውቴሌብርመፈጸምይችላሉ፡፡
  • ያለማንምአጋዥነት (Self-service) አሽከርካሪዎችአገልግሎቱንበራሳቸውማግኘትእናክፍያቸውንምበቴሌብርሱፐርአፕመፈጸምይችላሉ።
  • የስማርትኦንላይንክትትልስርዓቱበቴሌብርሱፐርአፕአማካኝነትመረጃዎችንለማግኘትእናየመሙላትሂደቱንለማስተዳደርየሚያስችልሲሆን፣ሲስተሙከክላውድሰርቨሮችጋርበፋይበርኬብልእንዲሁምበ4ጂእና 5ጂኔትወርክየተገናኘበመሆኑእጅግአስተማማኝነው፡፡
  • ኤን. ኤፍ. ሲ (Near Field Communication – NFC) በእጅበመንካትቻርጅማድረግ (tap to charge) ወይምስማርትየማንነትማረጋገጫ (smart authentication) ያላቸውሲሆን፣ይህምበቀላሉቻርጅማድረግንለማስጀመርእናክፍያዎችንእንዲያጠናቅቁበማስቻልተጠቃሚዎችየላቀተሞክሮእንዲኖራቸውያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያን ዲጂታል እና አረንጓዴ ትራንስፎርሜሽን ማጠናከር

ሀገራችን ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የትራንስፖርት ሥርዓት (Green Mobility) እያደረገች ያለውን ሽግግር ለመደገፍ፤ ኩባንያችን አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ዘመን ተሻጋሪ (Future-ready) መሠረተ ልማቶችን በመገንባት ረገድ ፈርቀዳጅ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለት ያስጀመርነው ይህ ሦስተኛው እጅግ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ ጣቢያም፤ ኩባንያችን በቴክኖሎጂ እና በዲጂታል መፍትሔዎች የኢትዮጵያን የትራንስፖርት ገጽታ ለመለወጥ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ነው፡፡

የቤት አውቶሞቢል የኤለክትሪክ ካልሆነ ወደ ሀገር እንዳይገባ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ ካሳለፈ ወራት ተቆጥረዋል። ያም ሆኖ የመኪናዎቹ ውድ መሆን፣ የኤለክትሪክ አቅርቦት ፣ የባትሪ መሙያ ጣቢያዎች ፣ የመለዋወጫ እና የጥገና ማዕከላት እጥረት ተግዳሮቶች መሆናቸው ይነገራል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በነዳጅ የሚሠሩ የቤት አውቶሞቢሎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ከወሰነ ከግማሽ ዓመት በላይ ሆኖታል። መንግስት በምትኩ በኤለክትሪክ የሚሰሩ የቤት መኪናዎችን ከውጭ ማስመጣትን ወይም በሀገር ውስጥ መገጣጠምን ያበረታታል።የውሳኔው መነሻ የአየር  ብክለትን እና የነዳጅ ወጭን ለመቆጠብ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ዶክተር ዓለሙ ስሜ በወቅቱ ገልፀው  ነበር።ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሠሩ መኪኖችን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለመተካት ዝግጁ ነች?
ሚኪ አወቀ በሚል ስም በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ መረጃ በመስጠት የሚታወቀው፤ የአውቶሞቲቭ ባለሙያው እና የትራንስፖርት አማካሪው አቶ ብሩክ አወቀ የመንግስትን የውሳኔ መነሻ ይጋራል።

ያም ሆኖ ብሩክ  በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ምቹ ሁኔታ አለ ብሎ አፉን ሞልቶ አይናገርም።ምክንያቱም መንግስት ህብረተሰቡ የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እንዲጠቀም በሚያበረታታው ልክ ለዚህ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን ቀድሞ በማሟላት ረገድ የተሰራ ስራ የለም ባይ ነው።እስካሁን ባለው ሁኔታ የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎችን  ሀይል መሙላት / ቻርጅ ማድረግ/ የሚቻለው በመኖሪያ ቤቶች ብቻ ሲሆን፤ይህም በኤለክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሂድ  የሀይል እጥረት ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት አለው።

በመኖሪያ ቤት ባትሪ ለሙሙላትም ቢሆን፤ በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለሚኖሩ ተጠቃሚዎች  ምቹ አለመሆኑ ሌላው ፈተና መሆኑን ገልጿል።

በዓለም ላይ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን፤በቅርቡ የተደረገ የሸማቾች  ዳሰሳ ጥናት እንዳመለከተው ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት አሜሪካውያን አዲስ መኪና ለመግዛት ከፈለጉ በእርግጠኝነት የሚያስቡት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ለመግዛት ነው። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መግዛት ከሚፈልጉ ሰዎች መካከል 77 በመቶ የሚሆኑት የነዳጅ ወጭ መቆጠብን እንደ ዋና ምክንያት ይጠቅሳሉ። ነገር ግን ባትሪ ለመሙላት  በቂ ቦታ ከማግኘት ጋር ተያይዞ  60 በመቶ የሚሆኑት  የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ያመነታሉ።

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና የሚያሽከረክሩ ሰዎች ደግሞ የሀይል መሙያ ቦታዎች እጥረት ብቻ ሳይሆን፤ በቂ የኤለክትሪክ ሀይል ፣ የጥገና ማዕከላት እና የመለዋወጫ ዕቃዎች አለመኖርም  ተጨማሪ ችግሮቻቸው ናቸው።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ አብዛኞቹ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙት ሊቲየም የሚባለውን ባትሪ ሲሆን፤ እንደ ብሩክ ገለፃ ይህ ባትሪ የሚሰጠው ዋስትና ደግሞ፣ እስከ 10 ዓመት ድረስ ነው።ነገር ግን ዋስትናውን በተመለከተ ሀገር ውስጥ ወኪል ባለመኖሩ ችግር ሲያግጥም ዋስትናውን ለመጠቀም አስቸጋሪ መሆኑም ተጨማሪ ተግዳሮት ነው።

እንደ ዓለም አቀፉ ኢነርጂ ኤጀንሲ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች በጎርጎሪያኑ 2023  ዓ/ም ከአጠቃላይ የመኪና ገበያ አንድ አምስተኛውን ይይዛል። በጎርጎሪያኑ 2022 ዓ/ም በዓለም ላይ ከ10 ሚሊዮን በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች የተሸጡ ሲሆን ይህ አሃዝ በ2023 መገባደጃ  14 በመቶ አድጓል።በተያዘው የጎርጎሪያኑ 2024 ዓ/ም ሽያጩ 17 ሚሊዮን እንደሚጠጋ መረጃው ያሳያል።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወረት እንዳያልፍባቸው ለማድረግ እና  ከነዳጅ ይልቅ በኤለክትሪክ የመጠቀም ሀሳብ የበለጠ ምቹ እንዲሆን ዋጋቸውን የበለጠ ተመጣጣኝ የማድረግ አዝማሚያዎች አሉ። በትራንስፖርት ዘርፍ የ10 ዓመት ዕቅድ ውስጥ ለታዳሽ ኃይል ቅድሚያ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግስትም፤ የኤክትሪክ መኪና ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚጣለውን ግብር ዝቅ አድርጓል። ያም ሆኖ አሁን ባለው ገበያ አንድ አነስተኛ የኤለክትሪክ መኪና ለመግዛት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ብሮችን ማውጣት ይጠይቃል። ይህም ለአብዛኛው ህብረተሰብ የሚቻል አይደለም።
በሌላ በኩል መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ አፈፃጸም በተመለከተ  እስካሁን መመሪያ ይፋ ባለማድረጉ ወደ ሀገር ለሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግልጽ የሆነ የባትሪ መስፈረት አለመኖርም ሌላው ችግር  ነው።“የእርጅና ቅናሽ” ሲቀር የመኪና ዋጋ ጨመረ
ብሩክ እንደሚገልፀው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንደ ባትሪ መጠናቸው የሚጓዙት ርቀት ይለያያል።እንደ ቮልስ ቫገን እና ቶዮታ ያሉ የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎች አንዴ በተሞላ ባትሪ እስከ ከ500 እስከ 600 የሚደርስ ኪሎሜትር ሊጓዙ ይችላሉ። አነስተኛ በሚባሉት የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ከ300 እስከ 400 ኪሜ ይጓዛሉ።ከዚህ አንፃር ከተማ ውስጥ ለሚንቀሳቀስ አንድ አሽከርካሪ ባትሪው በአማካኝ  እስከ ሶስት ቀን ሊያቆየው እንደሚችል ያስረዳል። ነገር ግን በአሽከርካሪዎቹ  ዘንድ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች አሉ። 

ብሩክ እንደሚለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ባለ8፣16 እና በ32 አምፔር የኃይል መሙያ ያላቸው ሲሆን፤ 8 አምፔር የኃይል መሙያ ያለው ተሽከርካሪ ቤት ውስጥ በሚገኝ መደበኛ  7 ኪሎዋት የኤለክትሪክ አቅም፤ ባትሪ ለመሙላት ከ12 ስዓት በላይ ፤32 አምፔር ላለው ተሽከርካሪ ደግሞ  እስከ 8 ሰዓት ሊፈጅ ይችላል።ይህም ቤት ውስጥ በኤለክትሪክ የሚሰሩ ስራዎችን በሙሉ ያስተጓጉላል።ከዚህ አኳያ በሀገሪቱ ፈጣን የባትሪ መሙያዎችን ተደራሽ ማድረግም ሌላው ወሳኝ ነገር ነው።ከዚህ ባሻገር በነዳጅ እና ኤለክትሪክ የሚሰሩ «ሃይብሪድ» የሚባሉትን ተሽከርካሪዎች መጠቀም ሌላው መፍትሄ መሆኑን ብሩክ ይገልፃል።መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መኪኖችን ዕድሜ ሊገድብ ነው

ከዓለም አቀፉ የካርቦን ልቀት 0.3 ድርሻ ያላት ኢትዮጵያ፤ ወደ 40 በመቶ የሚሆነው የአየር ብክለት በነዳጅ ከሚሰሩ በ1.2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎቿ የሚመጣ ነው። ስለሆነም የአካባቢ ብክለትን ለመከላለክል እና ከውሃ ሀይል  የሚገኝን ርካሽ የኤለክትሪክ ሀይል በመጠቀም በውጭ ምንዛሬ የሚገባ የነዳጅ ወጭን ለማስቀረት የኤለክትሪክ መኪና በኢትዮጵያ ጠቃሚ ነው። ነገር ግን ለእነዚህ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ ግብዓቶችን እና የባትሪ መሙያ ቦታዎችን ማመቻቸትን የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶችን ማሟላት እጅግ አስፈላጊ እና ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ባለሙያው አመልክቷል።ዋስትና የሚሰጡ ወኪሎች በሀገር ውስጥ እንዲኖሩ አስገዳጅ መመሪያ ማውጣትም በመንግስት በኩል ሌላው መሰራት ያለበት ስራ ነው።
የኤሌክትሪክ መኪናዎች አይነት በገበያ ላይ እየጨመረ ሲሆን፤ ቴስላ ግንባር ቀደም ከሆኑት የኤለክትሪክ መኪናዎች ውስጥ አንዱ ነው። ከቴስላ በተጨማሪ ሌሎች የመኪና አምራቾችም  በየአመቱ አዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪና አማራጮችን ወደ ገበያው እያስገቡ ነው።
በጎርጎሪያኑ እስከ 2025  ደግሞ እንደ አልፋ ሮሚዮ ፣ ቤንትሌይ እና አፕል /የቴክኖሎጂ ኩባንያው/ ያሉ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዝርዝር ገበያ ላይ እንደሚውል ይጠበቃል።
አብዛኛው የኤለክትሪክ መኪናዎች ሽያጭ በቻይና፣ አውሮፓ እና ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ገበያዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ  በሽያጭ 60 በመቶውን በመያዝ በቀዳሚነት ትመራለች።

Next Post
  • Election & Democracy
  • Latest
  • Magazine
  • News
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መጪው የምርጫ ሂደት ሁሉን ያካተተ፣ ሕጋዊ፣ ግልጽ እና ተዓማኒ እንዲሆን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና እንዳላችው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።

Ayele Addis December 11, 2025

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መጪው የምርጫ ሂደት ሁሉን ያካተተ፣ ሕጋዊ፣ ግልጽ እና ተዓማኒ እንዲሆን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ። የዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ በግንቦት/ሰኔ ወር ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። 7ኛው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ እየተቃረበ በመምጣቱ፣ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዝግጅት፣ ዝግጁነት፣ ማነቆዎች እና ዕድሎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች […]

Related Post

  • AFRICA
  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • Education
  • Election & Democracy
  • Journalism and Communication
  • Latest
  • Magazine
  • Media Litracy
  • News
  • Public Relation

The Hidden Cost of False Information: Who Controls the Data Behind Digital Deception?

Ayele Addis September 30, 2025October 15, 2026

Volume 101, 2025, EMMA NEWS By Meseret Abebe Abay Fighting disinformation through fact-checking, data protection, and accountable digital governance In Ethiopia’s rapidly evolving digital environment, information travels across social media platforms, messaging applications, websites, and online news outlets at extraordinary speed. These technologies create opportunities for public participation, education, and access to information. Yet they […]

  • AFRICA
  • Health
  • Radio & TV

ከደም ስር መጥበብ እስከ ጋንግሪን፡ ምልክቶች፣ አደጋዎችና የቅድመ ጥንቃቄ መንገዶች

Ayele Addis May 29, 2026May 29, 2026

አዲስ አበባ — በደም ስር መጥበብና መዘጋት ምክንያት የሰውነት ክፍሎች የደም ዝውውር ሲያጡ ወደ “ጋንግሪን” የሚባል ከባድ የጤና ችግር ሊያመሩ እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች አስጠነቀቁ። በተለይ በእጅና እግር ላይ የሚከሰተው ይህ ችግር በጊዜ ካልታወቀ ወደ አካል መቆረጥ ሊያደርስ ይችላል ተብሏል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መምህርና የቀዶ ጥገና ሐኪም ፕሮፌሰር ነብዩ […]

  • AFRICA
  • FEATURED
  • General
  • Latest
  • Magazine
  • News
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ከትላንት ታሪኩ እስከ ዛሬ መንገዱ…

Ayele Addis December 3, 2023February 3, 2024

በታደለ አምበሉ የካፒታል ገበያ እና አክሲዮን ገበያ ጥንስስ በኢትዮጲያ ተጀመረ የሚባለው በአፄ ሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1960ዎቹ አካባቢ እንደነበር ድርሳናት ያስረዳሉ ፡፡ በ1963 አ፣ም የተመሠረተው የአዲስ አበባ የአክሲዮን ንግድ ማኅበር፣ ከግብጽ ቀጥሎ በአፍሪካ ሁለተኛው እንደነበርም ይገነገርለታል፡፡ ያኔ በብሔራዊ ባንክ አደራጅነት የተመሠረተው ‹‹የአዲስ አበባ ሼር ዲሊንግ ግሩፕ›› በወቅቱ አገር በቀል የነበሩ የአክሲዮን ኩባንያዎች የአክሲዮን ይዞታቸውን በስፋት […]

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • ዜና
  • ልዩ ዕትም
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress