Skip to content
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • FEATURED

Media Education in Ethiopia: Addressing Training Needs for Journalists

<strong>በወርቅ ታሪክ ዙሪያ ያለው ምሥጢር</strong>

  • AFRICA
  • FEATURED
  • General
  • Human Rights
  • Investigative Reports
  • Latest
  • Magazine
  • News
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES
  • TOP VIDEOS

ተሸላሚ ሚዲያዎች ለህዝብ ምኑ ናቸው?

Ayele Addis July 12, 2024

Silenced Voices: How Politics Chokes Ethiopian Media?

ተሸለሙ የተባሉት ሚዲያዎች ከሚሰሯቸው ዜናዎች እና ፕሮግራሞች የህዝብ ድምፅ የሌላቸው፣ ሳቢነት፣ ማራኪነት፣ ችግር ፈችነት፣ የሁሉንም ድምፅ ማሰማት የጎደላቸው ናቸው፡፡ በፍጥነትና በጥራት ተዘጋጅተው የሚቀርቡ አይደሉም። ሳቢነት ይጎድላቸዋል። ጥልቀት ያንሳቸዋል። ዜናዎቹ ተከታታይነት የላቸውም። በዳራ የበለፀጉም አይደሉም። ተሸላሚ ተቋማት የሚያቀርቧቸው ዜና ሀተታ፣ ፊቸርና ዜና ትንታኔዎች በጅምር ያሉና ሙያው በሚፈልገው መጠን ያልበሰሉ ናቸው። እያዋዙ የሚያስተምሩ ፣ ዝርዘር መረጃ የማይሰጡ ፣ የማያሳውቁና የማያዝናኑ ናቸው።

እንደአንድ የሚዲያ መምህር ዘርፈ ብዙ ጥቃት በተነጣጠረበት ሁኔታ ውስጥ ሁነን የመንግስትን ብረት ለበስ እጆች ፈርተን ዝም ማለት አንችልም፡፡ ሙያውን ቢያንስ ማራከሱ መቆም አለበት፡፡ እነዚህ ሁሉ ሚዲያዎች ለኢትዮጱያ ህዝብ ምኑ ናቸው? አንዳቸውም ለመሸለም ፣ የቀረቡት የሚዲያ መሪዎች መሪውን ስለሚፈርቱ እንጅ በስራቸው ኮርተው እንደማይሆን እርግጠኛ ሁኖ መናገር ይቻላል፡፡ እውነትን እየሸፈኑ ፤ ሐቅን እያዳፈኑ፣ ሙያዊ ክህደት እየፈፀሙ ራሱን ያመመውን እግርህን ነው ብለው እንደሚከራከሩ ያላዋቂ ባለሙያ መፍትሄ የጠፋቸው የፅህፈት ሚንስትሮች ተሸለምን ቢሉ ፣ የተሸለሙት ለህዝብ በሰጡት አገልግሎት ሳይሆን ለመንግስት አሸርጋጅነታቸው ብቻ እንደሆነ ሀቅ ነው፡፡  

እስኪ የትኛውም ስራችሁም እንደማያሸልም የማህበራዊ ሚዲያ የአሰተያየት መስጫ ሳጥናችሁን ከፍታችሁ አንብቡ፡፡ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ከዚህ ሽልማት መንግስት የህዝብ የሆኑ ሚዲያዎችን ወደባላቤቱ መመለስ እንደማይፈልግ ነው፡፡ በዴሞክራሲ እጦት የታፈነን ፣ ሰበዓዊ መብቱ የተገፈፈን ፣ በኢኮኖሚ አዘቅት ውስጥ የወደቀን፣ በግጨት አፈሙዝ የተከፈተባት ሀገርን የመረጃ ስርዓት እየመሩል ፣ ሀሳብን እየሸመገሉ ሳይሆን እየሸነገሉ የሚጓዙ ሚዲያዎችን መሸለም ለመረጃ መዛባት ፣ ለመረጃ መሳሳት፣ ለመረጃ መበከል እውቅና እንደመስጠት ነው፤፤

የሀገራችን ሚዲያዎች የዜናዎችን አሠራር፣ አደረጃጀትና አቀራረብ በትንሹ እንኳን ብናይ ተሸላሚ ሚዲያዎቻችን በአሰልችነታቸው፣ የህዝብ ድምፅ የሌላቸው፣ ጥበብ እና የእውቀት መረጃ ቀረፃ የተሳናቸው ዜናዎቻ እና ፕሮግራሞች ምን ያሸልማል? የተለያዩ ድምፃችን የማንሰማበት ፣ ጉዳያችንን ቢቢሲ፣  አልጀዚራ እና ሲኤን ኤን እስኪዘግበው ምንጠብቅበት፣ የተቀራኖ ድምፆች የማይሰሙበት፣ የሀሳብ ልዩነት የማይሰተናገድበት አይደሉም እንዴ? የሰለቹ የዜና መዋዕል (የውሎ ዜና) ዘገባዎች እና የህዝብ ግንኙነት ስራ ባህሪ የተዋረሳቸው፣ ጋዜጠኞች ቢናገሩ የልብ አያደርሱም ተብለው መሪዎች ጋዜጠኛ የሆኑበት ፕሮግራም ብቻ ናቸው። ምን? የት? መቼ? እንዴት? እና ማን? የሚሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ የማይመልሱ፣ አውዱን ፍራቻ፣ እውነትን ሽሽት፣ ከታመመው ይልቅ ለጤናማው መጨነቅ፣ ከጎደለበት ይልቅ ለሞላለት ማለቅለቅ አይደለም እንዴ ሰራችሁ?

እናንተ ሰትሸለሙ፣ መሪዎች በአፍሪካ ተሸለሙ እያለ የሚቀልድብንን የናይጀሪያ ጋዜጠኛ ነበር ያስታወስኩት፣ በዜና እና ፕሮግራሞቻችሁ አንድም የተቃርኖ ድምፆች የማንስማበት፣ ፍትሃዊነት፣ እና  ሚዛናዊነት የነጠፈበት ዘገባ ካሸለመ እንኳንም እያፈረን ተሸለማችሁ።

የመንግስት አክቲቪስት ሲሸለም እኛም የሰበዓዊ መብት ተሟጋቾችን መሸለም ግዴታ ይሆንብናል፡፡ ምክንያቱም እንባችን የሚገዳቸው፣ ሞታችን የሚያማቸው የማህበረሰብ አንቂዎች፣ የእውት አርበኞች እስር ቤትም ሆነው የህዝብ ድምፅ ናቸው፡፡

እነዚህ ከአንድ ግለሰብ የማህበረሰብ አንቂ ታማኝነት ያነሰ አቅም ያላቸው ሚዲያዎች በሽዎች ሰራተኛ ይዘው፣ በሳንሱር ተሸብበው፣ እውቀታቸውን ለመጠቀም የታፈኑት በነዚህ ሸላሚዎች ነው፡፡ እንቁ ብቁዎች አፃፃፋቸው ውበትም፣ እውነትም ያጣው መንግስትን ስለሚፈሩ ነው። በግል አስተያየት የታጀቡና የፖለቲካ ጉንፋን ያጠቃቸውና ሳይንሳዊ እሳቤ የራቃቸው ሙያዊ አሰተያየት የተለያቸው ዘጋቢ ሚዲያዎች ናቸው።

 የእነዚህ ችግሮች መነሻ ራሱ አፈናውን ያበረታው መንግስት ለነፃ ሚዲያ መስራት እና የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ባህሎ የሞተ በመሆኑ ነው። ጋዜጠኞችን ነፃ ቢያደርጋቸው በዜና አመራረጥ፣ አፃፃፍና አቀራረባችው ላይ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ።

ለዚህ ሃሳብ ማሳደጊያ ያነጋገርኳቸው ጋዜጤኞች ‹‹መንግስትን በመፍራት የማይናገረውን የማያስጠይቀውን የልማት ስራ ብቻ የመዘገብ ተልዕኮ የወሰዱት መንግስት በመፍራት ነው፡፡›› ስለዚህ ‹‹የህዝብ ግንኙነት ዜና›› ዘጋቢ ሁነናል የሚለው የጠቅላይ ሚንስትሩ ተሸላሚ የሚዲያ ተቋም ጋዜጠኛ፣ በሚዲያ ኩረጃ ፣ ዜና ግልበጣ ውስጥ ወድቀናል በማለት እጁ እና ህሊናው እንደታሰረ ይናገራል።

አሁን የመንግስት ስብሰባ፣ የስልጠና፣ የወርክሾፕ ዜናዎች ላይ ነን የምትለው ዘጋቢ እንደ ወረደ ዜና መስራት የወቅቱ መሻሪያ መስመር ነው በማለት ታረጋግጣለች። በነዚህ ቦታዎች ላይ የምንሠራቸው ዜናዎች በአጀንዳው ላይ የተነሱ ቁልፍ ጉዳዮችና አከራካሪ ነጥቦች በመለየት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የስብሰባ ተሳታፊዎች /የስብጥሩን ሚዛናዊነት በመጠበቅ/ እዛው (on the spot) በዕረፍት ሰአት ልዩ (excultive) ቃለ መጠይቅ በመስራት ማቅረብ፤ /የዕለቱ ክብር እንግዳ የሚያስተላልፈው መልዕክት እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም/ እና ለትርጉም የሚጋለጡ ሀሳቦችን ዘግተናል በማለት ትናገራለች፡፡

የጋዜጣዊ መግለጫዎች ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው ሌላ የተሸላሚ ሚዲያ ባለሙያ- ከጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከአፈጉባኤ፣ ከፕሬዝዳንቱና በተለየ መልክ ከሚሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ውጪ ያሉ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን አንዘግብም፡፡ ስለዚህ እኛ የጋዜጣዊ መግለጫ ጋዜጠኛ ነን፡፡ የምርመራ ዘገባ ስልቶች የሉም፡፡ ሲል ይጠቅሳል፡፡

እኛ የዜና ተቀባይ ሳጥን ጋዜጠኛ እንጅ ተጓዥ መንገደኛ አይደለንም፡፡ የሚለው ሌላው አሰተያየት ሰጭ – በተለምዶ ዜናዎቹ ናቸው ወደኛ እየመጡ ያሉት እኛ ወደዜናዎች ሂደን አናውቅም። ዜናዎች ወደኛ የሚመጡት ደግሞ በመጡበት አግባብ መስተናገድ ስለሚፈልጉ ነው። ይህን አቅጣጫ የሰጠን መንግስት ነው ይላል።

እያንዳንዱ ጋዜጠኛ /ከዋና – አዘጋጁ እስከ ሪፖርተሩ/ የራሱ የወሬ ምንጮች፣ /ቲፕ የሚሰጠንና መረጃ የሚያቀብሉ/ ሊኖሩት ይገባል። ከሚኒስትሩ እስከ በር ጥበቃው ድረስ /በተለምዶ በጋዜጠኝነት ት/ቤቶች እንደሚባለው ወዳጆቹ ሆነው የጥቆማና “ይህቺንስ ሰምተሃታል?” ብለው የሚያዋሩት ሰዎች ግንኙነት መመስረት በፍርሃት መመስረት አልቻለም። ስለዚህም ዜናን ቁጭ ብሎ ከመጠበቅ ዜናውን ማደን፣ መቆፈርና አሽትቶ ወደ መፈለግ አልተሻገረም። ተቋማዊ ህልውና ወይም መለያ የሚመሠረተው ተቋሙ ትርጉም ያላቸው ትኩስ፣ ሚዛናዊ፣ እውነታና የሚጣፍጡ ዜናዎች ማቅረብ ሲችል ብቻ ነው። የማይጣፍጥ ዜና ማንም አይቀምሰውም። ጣፋጩን ዜና ለማምረት “ዜናን የማደን” ወይም “የማሽተት” ተግባር የሁሉም ጋዜጠኛ መለኪያ፣ መገምገሚያ ይሆናል። ወደ ዜና መሄድ የዜናዎቻችንም የአቀራረብ ድምፀት ይለውጠዋል።

የዜናችን አፃፃፍ መለወጥ፦ ዜናችን በችኮ ቃላት፣ በፖለቲካ ጃርገን፣ በ”ብለዋል” ፣ በ”አሳውቀዋል”፣ በ”ገልፀዋል”  እና “አመልክተዋል” ገለፃዎች የተሞሉ ናቸው። አፃፃፉ አይስብም። የሚሰማው የአንድ ወገን /የአንድ ተቋም ወይም ዘርፍ/ ድምፅ ነው። ይህ ድምፅ ደግሞ ያው “የተለምዶ” ነው በሚል ተመልካች – አድማጭ አይይዝም።

የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር የሽለመው  ማንነው ካልን ሚዲያዎችን ሳይሆን  ራሱን ነው፡፡ ብለን እንደመድማለን፡፡

Next Post
  • AFRICA
  • Latest
  • News
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES

<strong>በወርቅ ታሪክ ዙሪያ ያለው ምሥጢር</strong>

Ayele Addis July 19, 2024

Compiled by : Ayele Addis Ambelu ወርቅ—እምብዛም ጥንካሬ የሌለውና ደመቅ ያለ ቢጫ ቀለም ያለው ብረት ነው። ይህ ብረት ልዩ ባሕርያት ያሉት በመሆኑ ከጥንት ጀምሮ ተፈላጊ ሆኖ ኖሯል። ቀለሙ፣ መብለጭለጩ፣ በተፈለገው ቅርጽ ሊስተካከል የሚችል መሆኑና ዝገትን መቋቋም መቻሉ ከሌሎች የብረት ዓይነቶች ልዩ ያደርገዋል። በፈላጊዎቹ ዘንድ የተሰጠው ከፍተኛ ግምት ከሌሎች ብረቶች ለየት ያለ ታሪክ እንዲኖረው አድርጎታል። “ወርቅ! […]

Related Post

  • News

Addis Ababa City Government Mass Media Agency Establishment Proclamation

Ayele Addis June 29, 2021April 24, 2025

ADDIS NEGARI GAZETA Addis Ababa City Government Mass Media Agency Establishment  Proclamation  Sixth year No. 42 ADDIS ABABA, 5th July, 2014   OF THE CITY GOVERNMENT OF ADDIS  ABABA The Addis Ababa City Government Mass Media Agency  Proclamation Proclamation  No. 42/2014 A proclamation to Provide for the Amendment of the Addis Ababa City Government Mass […]

  • AFRICA
  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • Education
  • Entertainment
  • FEATURED
  • Job Vacancy
  • Journalism and Communication
  • Latest
  • Magazine
  • Media Litracy
  • News
  • Public Relation
  • Radio & TV
  • Scholarship
  • Scholarship and Opportunities
  • Training and Internships

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከህንዱ ቻንዲጋርህ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ስራዎች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡

Ayele Addis August 21, 2025August 21, 2025

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከህንዱ ቻንዲጋርህ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ስራዎች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡ Mekdela Amba University has signed a Memorandum of Understanding (MoU) with Chandigarh University in India to collaborate on mutually beneficial academic and research activities.The two institutions have agreed to collaborate in the following areas of mutual interest:*To explore opportunities […]

  • News

ስለ ፋና

Ayele Addis January 13, 2024January 13, 2024

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ ተቋማችን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በ1987 ዓመተ ምህረት ሲቋቋም በኃላ ቀር መሳሪያዎችና በጥቂት የሰው ሃይል በሀገራችን የብሮድካስት ሚዲያ አዲስ አቀራረብ ይዞ ወደ ስራ ገባ። በሂደትም አደረጃጀቱንና የፕሮግራም ይዘቱን እያሻሻለና ችግሮቹን እየቀረፈ ገስጋሴዉን ቀጠለ። ህብረተሰብ ተኮር ፕሮግራሞች ላይ በማጠንጠን የሚታወቀውና ለህዝባችን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ኑሮ መሻሻልና መዳበር የሚተጋው የሚዲያ ተቋማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ […]

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • ዜና
  • ልዩ ዕትም
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress