Skip to content
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • FEATURED

Ethiopian Digital & Media Literacy Training Program Main Trainer

የጋዜጠኝነት፣ የአክቲቪስትነትና የጦማሪነት ሁኔታ

  • AFRICA
  • ART & Media school of Africa
  • FEATURED
  • Journalism and Communication
  • Latest
  • Magazine
  • Media Litracy
  • News
  • Radio & TV

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ፣ የፕሬስ ነፃነት ፣ የመረጃ የማግኘት መብት እና የሚዲያ ልማት ፋይናንስ ፈተና ሁነውብኛል ብሏል፡፡ 

Ayele Addis March 9, 2024March 9, 2024

ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት “የጋዜጠኞችን ደኅንነት በማስጠበቅ ሥራቸውን ከፍርሃት ነፃ ሆነው” የሚሠሩበት እድል እንዲፈጠር እሰራ ነው መሆኑን የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ ወ/ሮ ትዕግስት ይልማ ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ የፀጥታ መናጋት እና ቀውስ መቀጠሉን ፣ ጦርነት ብሎም የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ድንጋጌ ከመኖሩ ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ጋዜጠኞች ባለፈ፣ የማህበራዊ መገናኛ ዐውታሮችን ተጠቅመው በመንግሥት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ፣ በመረጃ ትንተና የሚሳተፉ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ሲታፈኑ፣ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ተስተውሏል።

ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በአሁኑ ስዓትም 82 የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትንና ማህበራትን በአባልነት ማቀፉን ያስታወቀው   “የጋዜጠኞችን ደኅንነት በማስጠበቅ ሥራቸውን ከፍርሃት ነፃ ሆነው” የሚሠሩበት እድል እንዲኖር ከፌድራል ፖሊሲ እና ከፍትህ ተቋማት ጋር ከስራቸው ጋር በተገናኘ የሚደረግ ህገወጥ እስርን ለማስወገድ እየሰራ መሆኑ ተገልፆዋል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ የሚዲያ ባለሙያዎቭ እና የምክር ቤቱ አባላት  ጋዜጠኝነት አሁን ላይ ፈተና ላይ ስለመውደቁ ይታመናል። የምክር ቤቱ አባል ተቋማትም በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያለፉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

“የምክርቤታችን አባላት ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ውስጥ በመግባታቸው ፣ የኅትመት ዋጋ በመናሩ እና መገናኛ ብዙኃን እስከ መዘጋት የሚደርስ ችግር ውስጥ መውደቃቸው እንዲሁም የሳተላይት ክፍያ በመጨመሩ ሳቢያ አብዛኞቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ ይገኛሉ”።የጋዜጠኞች የመታሰር እና የመፈታት ሁኔታ በጎ የመሻሻል አዝማሚያ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም አሁን “እያሽቆለቆለ” እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ጋዜጠኞችና የሕትመት ውጤቶት በፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ መታገታቸው እንዳሳሰበው ከዚህ በፊት የጠየቀው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እርምት እንዲደረግ መጠየቁ ይታወሳል።

 በዚህ ወቅት ተጽዕኗቸው ጎልቶ የሚታየው የበይነ መረብ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ትንተናዎች እና ዘገባዎች ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችም ይሁን ድርጅቶች በደረሰባቸው ማስፈራራት፣ ቢሮ ተሰብሮ ዘረፋ ፣ ዛቻ እና መሰል ጉዳዮች ከሙያው የመራቅ፣ የመታሠር አልያም ሀገር ጥሎ ለመሰደድ ፈተና ተጋፍጠዋል።መሠል ችግሮችን ይፈታል ተብሎ እምነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የፈረመው የግልግል ዳኝነት ተግባራዊ አለመሆኑ አንዱ ችግር አባባሽ ጉዳይ መሆኑን አቶ አማረ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የመረጃ ነፃነት ዐዋጅ እንዲፀድቅ እንደሚሰራ እና ወደፊትም የሚዲያ ህጉ እንዲከበር የመግባቢያ ስምምነቶችን ለመፈራረም ከፌድል ፖሊሲ እና ከፍትህ ሚንስት ጋር መግባባት መድረሱን አስታውቋል። 

ኢትዮጵያ ውስጥ  ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር በተገናኘ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ፣ የማህበራዊ መገናኛ ዐውታሮችን ተጠቅመው በመንግሥት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ፣ በመረጃ ትንተና የሚሳተፉ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚሠሩ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ሲታፈኑ፣ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ታይቷል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ጋዜጠኞችና የህትመት ውጤቶት በፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ መታገታቸው ፣ መያዛቸው ፣ መለቀቃቸውና ዳግም መታሰራቸው ተደጋግሞ ታይቷል።

በቅርቡ በርካታ ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው መሰደዳቸውን አስታውቀው ነበር።

በአጠቃላይ፣ ሲፒጄ ህዳር 21፣ 2016 ባደረገው ቆጠራ  በዓለም ላይ 320 ጋዜጠኞች እስር ላይ እንደነበሩ ዘግቧል። ይህ ቁጥር በ1985  በሲፒጄ ቆጠራ ከተጀመረ ወዲህ ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር የሁለተኛነትን ደረጃን ይዟል። ይህ ደግሞ፣ ስር የሰደደ የአምባገነንነት እና  የመንግስታት  የነፃነት ድምፆችን አፋኝነት የሚያሳይ አሳሳቢ መመዘኛ ነው። አንዳንድ መንግስታት፣ ከራሳቸው ድንበር አልፈው አንድ እርምጃ ወደ ፊት በመሄድ፣ ጋዜጠኞችን ለማስፈራራት እና ለማዋከብ፣ የድንበር ዘለል የጭቆና ዘዴ ይጠቀማሉ። ሞስኮ የተጠቀመችባቸው የማስፈራሪያ ድርጊቶች በሌሎች ሀገሮች የሚኖሩ የሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ ተከታታይ የእስር ማዘዣዎችን ማውጣትን ያካትታሉ፤ ኢትዮጵያም በጎረቤቷ ጅቡቲ በስደት ይኖር የነበርን ጋዜጠኛ እንዲታሰር ካስደረገች በኋላ፣ በግድ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ የሽብርተኝነት ክስ እንዲመሰረትበት አድርጋለች።

በተጨማሪም፣ የሲፒጄ ጥናት እንደሚያሳየው በቆጠራው ውስጥ ከተዘረዘሩት ክሶች ውስጥ፣ ከ65% (209) በላይ የሚሆኑት ታሳሪ ጋዜጠኞች፣ መንግስትን የሚተቹ የዜና ሽፋን በማቅረባቸው፣ የሃሰት ዜና ማሰራጨትና የሽብርተኝነት የመሳሰሉ የፀረ-መንግስት ወንጀሎች፣ በበቀል መልክ፣ ክስ እንዲመሰረትባቸው ያደርጋል። ከ67 የክስ መዝገቦች ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች የተከሰሱበት ጉዳይ፣ እስካሁን አልተነገራቸውም። ብዙውን ጊዜ፣ ያለምክንያት ጭካኔ የተሞላባቸው ክስተቶች ያጋጥሟቸዋል፤ ብዙ ጊዜ የክስ ሂደቱን በማዛባት፣ ባለስልጣናት የቅድመ-ክስ እና የጋዜጠኞችን ቅድመ-ችሎት እስራት ሲያራዝሙ ይታያል፤  በጋዜጠኞች ጠበቆች ላይም በዓለም ዙሪያ የበቀል እርምጃ ሲወስድባቸው ይስተዋላል።  

በአገራችን በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን  ሕጋዊ ዕውቅና አግኝተው በሥራ ላይ ያሉ ሚዲያዎች  በህዝብ፣ በንግድና በማህበረሰብ ባለቤትነት የተያዙ ሲሆን ብዛታቸውም 168 ይደርሳል፡፡ እነርሱም 10 የህዝብ ሬዲዮና 12 የህዝብ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣15 የንግድ ሬዲዮና 26 የንግድ ቴሊቪዥን ጣቢያዎች፣ 54 የማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣ እንዲሁም 3 የትምህርት መገናኛ ሬዲዮ ሲሆኑ የህትመት መገናኛ ብዙኃንን በተመለከተም 13 ጋዜጦችና 10 መጽሔቶች በፌደራልና በክልል መንግሥታት ደረጃ ይታተማሉ፡፡ በተጨማሪም 13 ጋዜጦችና 12 መጽሔቶች በግሉ ሴክተር እየታተሙ  በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሀገሪቱ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የራስ በራስ ማስተዳደር እንዲችሉና ሕዝባዊ ተጠያቂነትና ግልፅነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ከማድረጉም በላይ የመገናኛ ብዙሃንን ነፃነትን ለመጠበቅና ለማስፋፋት ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡ መሆኑም ምክር ቤቱ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም የተመሠረተበትን ዓላማ ለማሳካት እንዲችል በአጭር ጊዜ ዕቅድ በማውጣት የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን ይገባዋል፡፡ ለዕቅዱም መነሻ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ የምክር ቤቱን ዓላማዎች በተሳለጠ መንገድ መተግበር ይቻላል፡፡ እነዚህ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎች በሥራ ላይ የዋሉት ደግሞ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ በሚባሉት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29 የፕሬስና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ በተመሠረተው የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ 590/ 2000 መሠረት ነው፡፡ ይህንን የሕግ ማእቀፍ መነሻ አድርገው የሚዲያ ድርጅቶችም ሆኑ ሙያተኞች በከፍተኛ ሙያዊ  ሥነ ምግባርና ብቃት ነፃ፣ ገለልተኛና ህብራዊ የመገናኛ ብዙኃን  እንዲሁም  የዲሞክራሲያዊ ሒደት ለማጠናከር ከፍተኛ  ሚና  ያላቸው የተለያዩ የሚዲያ ድርጅቶችና የጋዜጠኞች ማህበራት ተዋቅረዋል፡፡

ከዚያም አልፎ ወጥ በሆነ የሥነ ምግባር ደንብ የሚመራ፣ ጠንካራ አገር አቀፍ  ሚዲያ ካውንስል መመስርቱ አስፈላጊና ጠቃሚ ነበር፡፡ ከአድካሚ ውጣ ውረድ በኋላ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እውን ሊሆን የቻለውም በዚሁ መነሻ ነው፡፡ በመቀጠልም የመገናኛ ብዙኃን ካውንስሉ ራሱን ችሎ እንዲቋቋም የተለያዩ የጋዜጠኞች ማኅበራት፣ የአሳታሚዎችና የብሮድካስተሮች ማህበራት፣ እንዲሁም የሚዲያ ድርጅቶች በመሰብሰብ ከብዙ ውጣ ውረድና ክርክር በኋላ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤትን በ2008 ዓ.ም. ለመመሥረት ችለዋል፡፡ ሆኖም በወቅቱ የነበረው የሲቪክ ማህበራት ሕግ አካታች አንቀጽ የለውም በሚል ሰበብ ምክር ቤቱ ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ሊመዘገብ አልቻለም ነበር ፡፡ይህ ምክር ቤት ህጋዊ እውቅና አግኝቶ ወደ ሥራ ሲጋባ በአሁኑ ወቅት  የያዛቸው የሚዲያና የጋዜጠኞች ማህበራት ብዛት 52 ሲሆኑ፣ የአባላቱ ዝርዝርና የተሰማሩበት ዘርፍን በሚመለከት የቴሊቭዥንና የሬዲዮ ጣቢያ ያላቸው 10፣ ቴሊቪዥን ጣቢያ ብቻ ያላቸው 7፣ ሬዲዮ ጣቢያ ብቻ ያላቸው 7፣ ህትመት ላይ የተሰማሩ 18 ሲሆኑ የጋዜጠኞች ማህበራት፣ የብሮድካስተርና የአሳታሚዎች ማህበራት ደግሞ 4 ናቸው ፡፡ በየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ስር 16 የግልግል ዳኞች ይገኛሉ፡፡

ከለውጡ በኋላ ግን በ2011 ዓ.ም. በተሸሻለው የሲቪክ ማህበራት አዋጅ መሠረት ጉዳዩ በድጋሚ ታይቶ፣ ሰኔ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ምክር ቤቱ በሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ኤጄንሲ ሕጋዊ ፈቃድ አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ለፖለቲካዊ፣ ለማኅበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያደርግ፣ ጥራቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽ፣ በሃላፊነት ስሜት የሚንቀሳቀስ እና ነፃነቱ የተረጋገጠ አስተማማኝ የመገናኛ ብዙሃን እንዲስፋፋ የማድረግ፣ የሚዲያውን አቅም የመገንባት እና የመቆጣጠር አላማን ይዞ ልዩ ልዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ከነዚህ ስራዎች ውስጥ አንዱም መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን በራሳቸው የሚቆጣጠሩበትን ስልት መቀየስና መደገፍ ሲሆን በቅርቡም በአገራችን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ተቋቁሟል፡፡

Next Post
  • AFRICA
  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • General
  • Journalism and Communication
  • Latest
  • Magazine
  • Media Litracy
  • News
  • Public Relation
  • Radio & TV
  • Scholarship and Opportunities
  • Special Edition
  • TOP STORIES
  • TOP VIDEOS

የጋዜጠኝነት፣ የአክቲቪስትነትና የጦማሪነት ሁኔታ

Ayele Addis March 14, 2024

የጋዜጠኝነት መምህር እንደመሆንዎ በአሁን ወቅት ያለውን የጋዜጠኝነት፣ የአክቲቪስትነትና የጦማሪነት ሁኔታ እንዴት ያዩታል? ፕ/ር ዘነበ ክንፈ ይባላሉ፡፡ በሩሲያ የወዳጅነት ዩኒቨርሲቲ (Russian FriendShip University) የጋዜጠኝነት መምህር; ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መምጣቱን ተከትሎ፣ በጋዜጠኝነት ላይ የመጡ አዳዲስ ባህሪያት በራሳቸው አከራካሪ ናቸው፡፡ ጋዜጠኛ ማን ነው? አክቲቪስት ማን ነው? ጦማሪ ማን ነው? የሚለው አሁንም ድረስ በአለማቀፍ ደረጃ አከራካሪ ነው፡፡ የተለያዩ አገራት እነዚህን […]

Related Post

  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • Education
  • Female
  • General
  • Human Rights
  • Investigative Reports
  • Job Vacancy
  • Journalism and Communication
  • Media Litracy
  • Public Relation
  • Scholarship
  • Scholarship and Opportunities
  • Training and Internships

Internship Opportunity at the Ethiopian Media Women Association (EMWA)

Ayele Addis August 23, 2025August 23, 2025

Looking for opportunities in journalism and communication?EMWA is calling for fresh women graduates in journalism, communication and related fields.Send your motivation letter and CV to emwadirectress@gmail.com. Ethiopian Media Women Association EMWAEthiopian Media Women Association EMWA • 3rd+3rd+ professional Association at Ethiopia Media Women Assocaitionprofessional Association at Ethiopia Media Women Assocaition Ready to kickstart your media […]

  • News

African Leading BANK Summit; Ethiopia

Ayele Addis July 31, 2025July 31, 2025

@Firaol Abraham Tasisa @Nedi benti wakjira

  • AFRICA
  • General
  • Latest
  • Magazine
  • News
  • Politics
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES

India and Ethiopia Activate Mutual Visa Exemption for Diplomatic Passports

Ayele Addis January 16, 2026January 16, 2026

By Awot Haileslassie, 16th January 2026, Addis Ababa, Ethiopia India and Ethiopia have formally agreed to implement a mutual visa exemption for diplomatic passports effective as of 15th January 2026. This diplomatic visa exemption marks a major step forward for the diplomatic engagement between the two countries. Speaking at the signing ceremony, H.E. Ambassador Anil […]

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • ዜና
  • ልዩ ዕትም
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress