የዚህ ግጭት አገናዛቢ አዘጋገብ የመጀመሪያ ረቂቅ የታተመው በዩኔስኮ በሚደገፈው የደቡብ አፍሪካው ሮድስ ዩኒቨርሲቲ የግጭት አገናዛቢ ጋዜጠኝነት ፕሮጀክት እ.ኤ.አ. በ2010 ነበር።
የፕሮጀክቱ ዓላማ የግጭት አገናዛቢ አዘጋገብ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ለመቅረፅ እና ስርዓተ ትምህርቱን የተለያዩ ግጭት ባለባቸው አገራት ውስጥ ባሉ ዘጋቢዎች ለመሞከር ነበር። ይህ ማጣቀሻ ሲዘጋጅ ኮርሱን የሚወስዱት ሰዎች በትምህርቱ ምን እንደተሰጠ መከለስ እና በጥልቀት መመርመር እንዲችሉ ይዘውት የሚሔዱት ሰነድ ተደርጎ ነበር። አዲሱ የትምህርት ስርዓት ከዚህ ማጣቀሻ ጋር ተደማምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሞከረው በሲሲኤስአር እና በኢንተርኒውስ-ኬንያ ትብብር ናይሮቢ ውስጥ እ.ኤ.አ. በ2010 ነበር። ዎርክሾፑ ከደቡብ ሱዳን፣ ሰሜን ዩጋንዳ እና ከኬንያ ስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የመጡ ተሳታፊዎችን አካቷል፤ ሁሉም አካባቢዎች በቅርቡ ከፍተኛ ግጭት አስተናግደዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኮርሱ ከሌሎች የግጭት አካባቢዎች ለመጡ ተሳታፊዎች የተሰጠ ሲሆን፣ በሁሉም ሁኔታዎች በጥሩ ሁኔታ ተቀብለውታል። በነዚህ ዎርክሾፖች ወቅት ጋዜጠኞቹ ዎርክሾፑ ውስጥ ላልተገኙት ባልደረቦቻቸው እያጋሩ የነበሩ ሲሆን፣ ብዙዎቹ ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኙት ግልጽ ነበር። ይህም ማጣቀሻውን የበለጠ አሳድገ ራሱን የቻለ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎች ለሚሠሩ ጋዜጠኞች መመሪያ እንዲሆን የማድረጉን ውሳኔ አስከትሏል።
ይህንን ማጣቀሻ በማዘጋጀት ሥራ ውስጥ ሲሲኤስአር በተለያየ ሰፊ የዐውድ ማዕቀፍ፣ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎች ውስጥ የመሥራት ልምድ ያላቸው አምስት የታወቁ ጋዜጠኞችን ተሞክሮ በመዋስ የተገለጹት ሐሳቦችን ፋይዳ እና የተጠቆሙት ስልቶችን ለግጭት አገናዛቢ አዘጋገብ ያላቸውን ጠቃሚነት አጢኗል። ጋዜጠኞቹ እና ደራሲው ገንቢ ትችቶችን በመጀመሪያው ማጣቀሻ ላይ ሲያደርጉ አንድ ቅዳሜና እሁድ አብረው ያሳለፉ ሲሆን፥ ጥቂት ተጨማሪ መካተት ያለባቸው ጠቃሚ የግጭት አዘጋገብ ጥቆማዎችም አድርገዋል። በአምስቱ ጋዜጠኞች የተሰጡት አስተያየቶች እና ጥቆማዎች ማጣቀሻውን በእጅጉ ያበለፀጉት ሲሆን፥ በዎርክሾፑ ላይ የተነሱት ብዙ ጉርሻዎች እና ስለቶች በማጣቀሻው ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል። በዚህም ጋዜጠኞቹ እንደ አርታኢዎች ቦርድ እና አጋር ደራሲ ድርብ ሚና ተጫውተዋል።
ህግን የተፃረረ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት Gov't interference in the media
የተካሄደው መላመልና አሻሻም ሂደት እንዲስተካከል እንጠይቃለን ; የሚመለከታችሁ አካላትም ይህ ህግን የተፃረረ አካሄድ እንዳይደገምና ልምድ ሆኖ በመንግስት ስርዓት ውስጥ እንዳይቀጥል ድምጻችሁን እንድታሰሙ እንጠይቃለን፡ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት ያጸደቀው ፖርላማው ከዓመት በፊት ያወጣውን የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2ዐ13 በተፃረረ መሆኑን ተመልክተናል፤ በመጀመሪያ ደረጃ አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጁ ከረቂቁ ጀምሮ […]