Skip to content
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • Scholarship and Opportunities
  • Training and Internships

ጥቂት ስለኢትዮጵያ ሬዲዮው ዜና ፋይል

የአብክመ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን "የሌብነት ሰንሰለቶችን" ለመቁረጥ የፀረ ሙስና ፍልሚያ  እያካሄደ ነው፡፡

  • AFRICA
  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • Job Vacancy
  • Journalism and Communication
  • Media Litracy
  • Public Relation
  • Radio & TV
  • Scholarship
  • Special Edition
  • Training and Internships

‘የኢትዮጵያ ሬዲዮ’ ጣቢያ 90 ዓመታትን በትጋት ለኢትዮጵያ! በኢትዮጵያ የአሁኑን

Ayele Addis September 20, 2025September 20, 2025

‘የኢትዮጵያ ሬዲዮ’ ጣቢያ ለማቋቋም ስራ ሲጀመር ዘርፉ በአለም ላይ ገና ለጋ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ የሬዲዮ ስርጭት ስትጀምር አሁን ላይ ስመጥር የሆኑ፤ ያኔ ግን ገና ያልተመሰረቱ ሀገራት ነበሩ፡፡ ከኢትዮጵያ ዉጭ መላዉ አፍሪካ በቅኝ ግዛት እየማቀቀም ነበር፡፡ የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ለአለም ገና እንግዳ በነበረበት በዚያ ወቅት ታዲያ የኢትዮጵያ ሬዲዮ በአየሩ ላይ መናኘት ጀምሯል፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ስርጭት ሲጀምር እንዳሁኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጅ አልተስፋፋም ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ስራዉን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር ይነገራል፡፡

በጅማሮዉ ወቅት ድምፅ በመቅዳት ወይም ሪከርድ በማድረግ አቀናብሮ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ለሰዓት እወጃ ሳይቀር ደወል ስቱዲዮ ዉስጥ በተዘጋጀ ሰዉ በአካል ይደወላል፤ ዜና እና ሙዚቃ በቀጥታ ይቀርባል፡፡ በወቅቱ የሬዲዮ መቀበያ መሳሪያዉ በብዙ ሰዎች ዘንድ ባለመኖሩ በትላልቅ ከተሞች ስርጭቱን በድምጽ ማጉያ አማካኝነት ነዋሪዉ ሰብሰብ ብሎ እንዲሰማ ይደረግም ነበር፡፡ አዲስ አበባ ላይ የአድማጭ አስተያየት ከመንገድ ላይ ሰዉ ተጠርቶ በቀጥታ ከስቱዲዮ ይደመጣል፡፡ ምክንያቱም ያኔ እንዳሁኑ ስራዉን ሁሉ በቀላሉ ለማከናወን የሚያስችል ቁሳቁስ አልተሟላም፡፡ ይሁንና ሬዲዮ ጣቢያዉ ራሱን ቀስ በቀስ በቁሳቁስ እያደራጀ በኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ ሳይሆን በቀጠናዉ ሀገራትም ጭምር ስርጭቱ ናኝቷል፡፡

በአለም ዙሪያ የተሰሙ ወቅታዊ መረጃዎችን ‘ዜና ፋይልን’ ጨምሮ በተለያዩ የዜና እወጃ መርሃግብሮቹ አማካኝነት አሁንም ድረስ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ልብ ዉስጥ ታትመዉ በሚገኙ ጋዜጠኖች ለህዝቡ አድርሷል፡፡የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ ‘ቡና ቡና’ የሚለዉን መዝሙር በተከታታይ ከማስደመጥ ጀምሮ በርካታ ጥንቅሮችን እያዘጋጀ ለአድማጭ አድርሷል፡፡ ፖለቲካዊ ዉሳኔዎች እና የመንግስታት ለዉጥን የተመለከቱ ዘገባዎች ተላልፈዉበታል፡፡ ከዳሎል ዝቅታ እስከ ራስ ደጀን ከፍታ የኢትዮጵያን ታሪካዊ እና ሰዉ ሰራሽ ሃብቶች አስተዋዉቋል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮ የሀገሪቱ ‘የኪነ ጥበብ ዘርፍ’ አሁን ለደረሰበት ደረጃ አሻራዉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡ በሙዚቃዉ በኩል አበርክቶዉ ‘ከኢትዮጵያ ሬዲዮ ኦርኬስትራ’ ምስረታ ይጀምራል፡፡

በርካታ ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራዎቻቸዉን በኢትዮጵያ ሬዲዮ ስቱዲዮ ቀርፀዋል፡፡ በዚህም የትም የማይገኙ ሙዚቃዎች ጭምር አሁን ላይ በኢትዮጵያ ሬዲዮ የሙዚቃ ክምችት ክፍል ዉስጥ ይገኛሉ፡፡ ሬዲዮ ጣቢያዉ የድምፅ ክምጭት /አርካይቭ/ ሃብታም ነዉ፡፡ስነ – ፅሁፍን ከፍ አድርጎ የሰቀለዉ ‘ፍቅር እስከ መቃብርን’ ጨምሮ የተለያዩ መጽሃፍት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ተተርከዉ ለአድማጭ ደርሰዋል፡፡ በዚህም ሬዲዮ ጣቢያዉ ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ‘የክፍለ ዘመኑ ጀግና’ የሚል እዉቅና አግኝቷል፡፡ አድማጭን በስሜት ብድግ ቁጭ ያደረጉ የስፖርት መረጃዎች በኢትዮጵያ ሬዲዮ ተላልፈዋል፡፡ እሁድ እና ቅዳሜን የሚያስናፍቁ የመዝናኛ መሰናዶዎች ቀርበዉበታል፡፡ ሬዲዮ ጣቢያዉ ያልዳሰሰዉ ርእሰ ጉዳይ የለም፡፡ በኢትዮጵያ አሁን ላይ ቁጥራቸዉ ለበዙት የሬዲዮ ጣቢያዎች እና በሙያዉ ከፍ ያለ ስም ለያዙት ጋዜጠኞች መነሻቸዉ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ነዉ፡፡ ሬዲዮ ጣቢያዉ አሁንም የይዘት እና አቀራረብ ለዉጦችን እያደረገ ለኢትዮጵያዊያን የመረጃ ምንጭነቱ እንደቀጠለ ነዉ፡፡

ብዙ ከፍታ እና ዝቅታዎችን ያለፈዉ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ታዲያ ስርጭት ከጀመረ ዛሬ መስከረም 2/2018 ዓ.ም 90 አመት ሞልቶታል፡፡ ይህ አንጋፋ የሬዲዮ ጣቢያ ታሪኩ ረጅም ነዉ፡፡ አመጣጡን በአጭሩ እንንገራችሁ፡- ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጣቢያ ግንባታን የመሰረት ድንጋይ በ1923 ዓ.ም በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ በሚባለዉ አካባቢ አስቀመጡ፡፡በመሰረት ድንጋዩ ላይ የሰፈረዉ ፅሁፍም “ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ በነገሱ በሁለተኛዉ አመት ኢትዮጵያን ከአለም መንግስታት ጋር የሚያገናኝ ‘ያለ ሽቦ ቃል የሚያሳልፍ መኪና’ የሚቆምበት ቤት ሲመሰረት በሀምሌ 14 ቀን 1923 ዓ.ም የመጀመሪያዉን የማእዘን ድንጋይ አኖሩ” ይላል፡፡ ግንባታዉ በታህሳስ ወር 1927 ዓ.ም ተጠናቆ በቀጣይ አመት አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ይሄዉም መስከረም 2/1928 ዓ.ም ነበር፡፡ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ “ይህ የምትሰሙት ድምፅ የእኔ የንጉሳችሁ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ነዉ” በማለት የመጀመሪያዉን መልዕክት በሬዲዮ ጣቢያዉ አሰሙ፡፡

በአዲስ አበባ አሁን ላይ ንፋስ ስልክ የሚባለዉ አካባቢ ስያሜዉን ይዞ የቀረዉ የሬዲዮ ጣቢያዉ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ላይ ከሰፈረዉ “ያለ ሽቦ ቃል የሚያሳልፍ መኪና” ከሚለዉ ፅሁፍ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ይሁንና የነፋስ ስልክ ሬዲዮ ጣቢያ ብዙ ሳይቆይ በአመቱ አዲስ አበባን በተቆጣጠረዉ የፋሽስት ጣሊያን ወራሪ ሃይል አገልግሎቱ ተቋረጠ፡፡ ይኸዉ ሃይል የነፋስ ስልኩን ጣቢያ በማስቀረትና የራሱን ሬዲዮ ጣቢያ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ አካባቢ በማቋቋም ወረራዉን ለማሳካት በሚያስችለዉ መልኩ ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨቱን ቀጠለበት፡፡መጠሪያዉንም የኢጣሊያ የምስራቅ አፍሪካ ሬዲዮ ጣቢያ ብሎ ሰየመዉ፡፡

ፋሽስት ጣሊያን ከ5 አመታት በኋላ በ1933 ዓ.ም በሽንፈት ሀገር ለቆ ሲወጣ ታዲያ ይኸንኑ ሬዲዮ ጣቢያ አፈራርሶት ነበር፡፡ ይሁንና በ1934 ዓ.ም ጣቢያዉ ጥገና ተደርጎለት በአማርኛ፤ በሶማሊኛ፤ በእንግሊዝኛና በአረብኛ ቋንቋዎች ዜና፤ አስተያት እና ሙዚቃ እንደገና ማቅርብ ስለመጀመሩ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባሳተመዉ መጽሄት ላይ የተቀመጠዉ መረጃ ያመለክታል፡፡ በወቅቱ እነ ከበደ ሚካኤል፤ እነ አምደሚካኤል ደሳለኝና ሌሎችም በጋዜጠኝነት ስራዉ ተመድበዉ ዝግጅቶችን ያቀርቡ ነበር፡፡ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴም በወቅቱ ሬዲዮ ጣቢያዉ ከወራሪዉ የጣሊያን ሃይል እጅ መዉጣቱንና በአዲስ መልክ ወደ ስራ መግባቱን በማስመልከት “በግፍ የፋሽስቶች አፍ የነበረዉን ሬዲዮ እንደገና ለህዝባችን እናገለግልበት ዘንድ እንሆ የብርሃንና ሰላም ዘመን ሆኗል” የሚል መልዕክት አስተላልፈዉ ነበር፡፡ከጣሊያን ወረራ ማብቃት በኋላ እንደገና ወደ ስራ የገባዉ ሬዲዮ ጣቢያዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሬዲዮ ጣቢያ ተብሎ ተሰየመ፡፡

ንጉሰ ነገስቱን የሚያወድሱ፤ በ5 አመቱ የጣሊያን ወረራ ወቅት የነበረዉን የአርበኝነት ገድል የሚያወድሱና የሚያመሰግኑ፤ ፕሮግራሞችም በብዛት ተላለፉ፡፡ከዜና፤ ከትምህርታዊ ፕሮግራሞችና ከመዝናኛ ዝግጅቶች ባሻገር የንግድና የመንግስት ማስታወቂያዎችም የስርጭቱ አካል ሆኑ፡፡በ1942 ዓ.ም ማስታወቂያ ሚኒስቴር የጣቢያዉን ፕሮግራም በበላይነት እንዲቆጣጠር ሃላፊነት ተሰጠዉ፡፡ ይህ ከሆነ ከ5 አመታት በኋላ ደግሞ የተደራጀ ነበር የተባለለት የስቱዲዮ መሳሪያ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ግቢ ዉስጥ ተተከለ፡፡ ሌሎች መሳሪያዎችም በአስመራ በጎንደር፣ በበደሴ፣ በደብረማርቆስ፣ በድሬዳዋ፣ በሀረር፣ በጂማ፣ በነቀምት፣ በአሰላ፣ በይርጋለም እንዲሁም በመቀሌ እንዲተከሉ ተደረገ፡፡በጌጃ ዴራ የተቋቋመዉ ባለ 100 ኪሎዋት ማስተላለፊያ ጣቢያም በ1949 ዓ.ም ለሬዲዮ ጣቢያዉ አዲስ ጉልበት ሰጠዉ፡፡

በ1954 ዓ.ም ደግሞ አዲስ የድምፅ መቅረጫና ማሰራጫ መሳሪያዎችን በመጠቀም ለምእራብ አፍሪካና ለምእራብ አውሮፓ በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ፤ ለምስራቅና መካከለኛዉ እሰያ እንዲሁም ለሰሜን አፍሪካ በአረብኛ፤ ለመካከለኛዉና ምስራቅ አፍሪካ በስዋህሊ ቋንቋዎች ፕሮግራሞችን ማስተላለፍ ጀመረ፡፡ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ 35ኛ የዘዉድ በዓላቸዉን በጥቅምት ወር 1959 ዓ.ም ሲያከብሩ መርቀው የከፈቱት ከፍተኛ አቅም የነበረዉ የሚዲየም ዌቭ ማሰራጫ ጣቢያም የሬዲዮ የስርጭት አድማስን አሰፋዉ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የኢትጵያ ሬዲዮ ተብሎ እንደተጠራ ይነገራል፡፡

ጣቢያዉ እንዲህ አንዲያ እያለ ከ7 አመታት በኋላ ደግሞ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገባ፡፡ደርግ መንበረ ስልጣኑን ከቀዳማዊ ሃይለስላሴ ለመዉረስ ያዘጋጀዉን መግለጫ በተለያ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ቋንቋዎች አስተርጉሞ በመስከረም ወር 1967 ዓ.ም በኢትጵያ ሬዲዮ አንዲተላለፍ አደረገ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮም የሬዲዮ ጣቢያዉ ስያሜ ከኢትጵያ ሬዲዮ ወደ አብታዊት ኢትዮጵያ ድምጽ ተቀየረ፡፡ በወቅቱ ህዝቡን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመቀስቀስ፤ ለማንቃት፤ እና ለማደራጀት የሚያግዙ የዘመቻ የፉከራና የማርሽ ድምጾች በብዛት ይስተጋቡ ነበር ይባላል፡፡

ለ17 አመታት በዘለቀዉ የደርግ ስርተ መንግስት ወቅት የሬዲዮ ጣቢያዉን አብዛኛኘዉን የአየር ሰአት የሚሸፍኑት የአማርኛ መሰናዶዎች ሲሆኑ የእሁድ ፕሮግራም፤ እርስዎም ይሞክሩት፤ ግብርና፤ ኢኮኖሚ፤ ማህበራዊ ኑሮ፤ ኪነ ጥበባት፤ የመፅሃፍት አለም፤ ስፖርት፡ ጤና፤ ወጣቶች፤ ቅዳሜ መዝናኛ፤ ህግና ህብረተሰብ፡ ደብዳቤዎች፤ የልጆች አለም፤ የሳይንስ ማህበርና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ሬዲዮ ጣቢያዉ እንደ አሜሪካ ድምጽ ቪኦኤ እና የጀርመን ድምጽ ዶቸቨሌ ያሉ ጣቢያዎች ከዉጭ ለኢትዮጵያያን ብለዉ በአገር ቤት ቋንቋ ያስተላልፏቸዉ የነበሩ አፍራሽ የሚል ስም የተሰጣቸዉን መልእክቶች የሚመክት መረጃ የማቅረብ ሃላፊነት ተጥሎበትም ነበር፡፡

ከደርግ መንግስት መዉረድ በኋላ ሬዲዮ ጣቢያዉ እንደገና የኢትዮጵያ ሬዲዮ ተብሎ በተለይም በ1980ዎቹ እና 90ዎቹ መላ ሀገሪቱን በሚያዳርስ ስርጭት ዝግጅቶችን በተለያዩ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ቋንቋዎች ለአድማጭ አድርሷል፡፡ሬዲዮ ጣቢያዉ በኢህአዴግ ዘመን መጨረሻ ብሄራዊ ሬዲዮ በሚል እንዲጠራ ተደርጎ የነበረ ሲሆን በለዉጡ ሰሞን የኢትዮጵያ ሬዲዮ ወደሚለዉ ስያሜዉ እንዲመለስና ተቀይረዉ የነበሩ ተወዳጅ ፕሮግራሞችም እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡90 አመታትን ለተሻገረ ጊዜ ብዙ ከፍታና ዝቅታን ያሳለፈዉ የኢትዮጵያ ሬዲዮ አሁን ላይም ዘመኑ ባፈራዉ ቴክኖሎጅ በመጠቀም ኢትዮጵያን እያገለገለ ይገኛል፡፡ አማርኛ፤ ኦሮምኛ፤ ትግርኛ፤ አፋርኛ እና ሶሚሊኛ አሁን ላይ በጣቢያዉ እየተላለፉ የሚገኙ ቋንቋዎች ናቸዉ፡፡የኢትዮጵያ ሬዲዮ – ለኢትዮጵያ ልእልና! በብርሃኑ አለሙ

#ethiopianradio#EBC#radio#anniversary#ebcdotstream#Ethiopia#90th

Next Post
  • AFRICA
  • Election & Democracy
  • General
  • Human Rights
  • Investigative Reports
  • Latest
  • Magazine
  • News

የአብክመ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን "የሌብነት ሰንሰለቶችን" ለመቁረጥ የፀረ ሙስና ፍልሚያ  እያካሄደ ነው፡፡

Ayele Addis September 20, 2025

“በአማራ ብሄራዊ ክልል የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ ሙስናዎችን በመከላከል እና በመቆጣጠር ላይ ተፅእኖ የሚያደርጉ ጉዳዮች” በሚል መሪ ቃል በባህር ዳር ከተማ የተካሄደው አውደ ጥናት የኢትዮጵያን አስተዳደር እና ኢኮኖሚ እያሽመደመደ ያለውን ቀውስ ይፋ አድርጓል። በአማራ ብሔራዊ ክልል የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአማራ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ኃላፊዎችን፣ ተመራማሪዎችን፣ የሲቪክ ተወካዮችን እና ጥሪ የተደረገላቸውን […]

Related Post

  • AFRICA
  • Education
  • Election & Democracy
  • FEATURED
  • Human Rights
  • Latest
  • Magazine
  • News
  • Radio & TV
  • Scholarship and Opportunities
  • Special Edition
  • TOP STORIES

Beyond the Headlines: How Ethiopian Journalists Are Building Stronger, Sustainable Newsrooms Through Practical Media Training

Ayele Addis July 28, 2026July 28, 2026

A News Analysis on Journalism Capacity Building in Ethiopia By Dr. Ketema A, Addis Ababa, Ethiopia Across Ethiopia’s rapidly evolving media landscape, journalism is undergoing a profound transformation. The pressures of digital disruption, shrinking revenues, misinformation, artificial intelligence, audience fragmentation, and increasing demands for ethical, evidence-based reporting have reshaped what it means to be a […]

  • AFRICA
  • ART & Media school of Africa
  • FEATURED
  • Journalism and Communication
  • Latest
  • Magazine
  • Media Litracy
  • News
  • Radio & TV

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ፣ የፕሬስ ነፃነት ፣ የመረጃ የማግኘት መብት እና የሚዲያ ልማት ፋይናንስ ፈተና ሁነውብኛል ብሏል፡፡ 

Ayele Addis March 9, 2024March 9, 2024

ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት “የጋዜጠኞችን ደኅንነት በማስጠበቅ ሥራቸውን ከፍርሃት ነፃ ሆነው” የሚሠሩበት እድል እንዲፈጠር እሰራ ነው መሆኑን የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ ወ/ሮ ትዕግስት ይልማ ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ የፀጥታ መናጋት እና ቀውስ መቀጠሉን ፣ ጦርነት ብሎም የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ድንጋጌ ከመኖሩ ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ጋዜጠኞች ባለፈ፣ የማህበራዊ መገናኛ ዐውታሮችን […]

  • AFRICA
  • FEATURED
  • General
  • Latest
  • Magazine
  • News
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES

በሚዲያ ሕጉ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ አሳሳቢ ይዘት ላይ ከጋዜጠኞች የሙያ ማህበር እና  ከሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የተሰጠ መግለጫ  

Ayele Addis November 14, 2024

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 19/2017 በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ ይታወሳል። እኛ ሥማችን ከዚህ መግለጫ ግርጌ የተዘረዘረው ከጋዜጠኞች የሙያ ማህበር እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቾች የአዋጁ ማሻሻያ […]

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • ዜና
  • ልዩ ዕትም
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress