የኢትዮጵያ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አውደጥናትን በሐገር አቀፍ ደረጃ ባህር ዳር ታስተናግዳለች።
የኢትዮጲያ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ብሔራዊ ኮንፈረንስ ሚያዚያ 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ርዕስ ከተማ በባሀር ዳር ይካሄዳል፡፡ ጉባኤው በኢትዮጵያ ሚዲያ በሚታዩ ለውጦች፣ ተግዳሮቶች እና ቀጣይነት ያለው የሚዲያ ማሻሻያ ላይ ያተኩራል። በዚህ ረገድ ጉባኤው በመድረኩ የሚዳሰሰው አበይት መሪ ሃሳቦች የኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪካዊ እድገት፣ በኢትዮጵያ የሚዲያ ፖሊሲ ውስጥ ያሉ ወቅታዊ ለውጦች፣ በቅርብ ጊዜ የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ላይ የተሰሩ ስራዎች፣ የኦንላየን ሚዲያ እና የጥላቻ ንግግር፣ አክቲቪዝም እና ጋዜጠኝነት፣ የመገናኛ ብዙሃን ቁጥጥር እና ተቆጣጣሪ አካላት፣ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የሚዲያ ሳንሱር፣ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እና ሚዲያ፣ ርዕዮተ ዓለም እና ሚዲያ ግንኙነት፣ የሚዲያ ትምህርት፣ ሚዲያ እና ስርዓተ ጾታ፣ የክልል ሚዲያ አስተዳደር እና አመራር፣ መረጃ የማግኘት መብት እና አተገባበሩ፣ እውነታን ማጣራት፣ የመገናኛ ብዙሃን እና ብዝሃነት እና አካታችነት፣ የመገናኛ ብዙሃን ማህበር እና የሲቪል ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙሃን ድጋፍ ሰጭ ቡድኖች ሚና፣ የሚዲያ ሥራ ፈጣሪነት እና በመንግስት ኮሙኒኬሽን ላይ የሚዲደረጉ ማሻሻያዎችን እና ሌሎችንም የተመለከቱ ከ17 በላይ የጥናት ወረቀቶች ይቀርባሉ።
በዝግጅቱ ላይ 100 የሚጠጉ ተሳታፊዎች እና ታዋቂ ተናጋሪዎች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የመንግስት እና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ሚዲያዎች፣ አካዳሚዎች እና የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ይገኙበታል። የሚዲያ ባለድርሻ አካላት መሪ ተወናይ በመሆኑነበት በዚህ ኮንፈረንስ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን፣ የሚዲያ ስራ አስኪያጆች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የሲቪል ማህበራት፣ የሚዲያ ድጋፍ ሰጪ ቡድኖች፣ የቁጥጥር አካላት፣ አክቲቪስቶች፣ የሚዲያ አካላትን ጨምሮ ወደ 20 የሚጠጉ ተመራማሪዎች እና ዋና ዋና ተናጋሪዎች፣ የሰባት መገናኛ ብዙሃን ተወካዮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። 10 የሚዲያ ድጋፍ ሰጭ ቡድኖች፣ 11 የጋዜጠኞች ማህበራት፣ አስር የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል ከዩኒቨርሲቲዎች፣ 12 የክልል መገናኛ ብዙሃን፣ አስር የፌዴራል እና የግል ሚዲያዎች ከአዲስ አበባ፣ እና ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ 100 ተሳታፊዎች በኢትዮጲያ የሚዲያ ጉዞ ላይ ለሁለት ቀናት በባሀር ዳር ይመክራሉ።

History of Ethiopian Magazines Dawit Alemu eliasww@gmail.com
uploaded and edited by Ayeleradio@ayele-addis Introduction Ethiopian magazines had a shortage history, because of not established printing enterprises like Birhanena Selam huge printing press and also lately introduce other publishing technology. Under this title, we are trying to overview the recent three regimes, which are the Imperial, The Derg, and the EPRDF regimes respectively. From […]