Timeline of government #Disinformation & #Misinformation about Amhara Innocent University Girls Kidnap in Oromia region
ህዳር 2012 መጨረሻ ንፁሀን የአማራ ክልል ተማሪዎች በብሄር በደረሰባቸው ጥቃት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ መንግ,ገድ ላይ እንዳሉ በታጠቁ ሃይሎች ታገቱ፡፡ የአካባቢው ኗሪም የልጆችን ጩህት እየሰማ ለመታደግ አልሞከረም፡፡
ታህሳስ 1/2012 ዓ.ም ድረስ መታገታቸውን የሰሙ ወላጆች ለመንግስት አቤቱታ አሰሙ ፤ የስልክ ግንኙነታቸው ተቋረጠ፡፡
ታህሳስ 26፣ 2012 የፌደራል ፖሊስ እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በጋራ መግለጫ ሰጡ
ታህሳስ 26፣ 2012 ጋዜጠኛ ጋሻው ፈንታ 7 ሰዎች ባልታወቁ ኃይሎች እንደታገቱና 11 ሰዎች አስገድዶ መድፈር እንደደረሰባቸው መረጃው እንዳለው ገልፆ ጥያቄ አቀረበ፡፡
ታህሳስ 26፣ 2012 ዓ.ም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ “እገታ የሚባለው ነገር… በእዚህ አካባቢ ይሄ ታገተ የሚል የደረሰን ሪፖርት የለም፡፡” አሉ፡፡
ታህሳስ 27፣ 2012 ዓ.ም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ስለታገቱ ተማሪዎች ለመከላከያና ለፌደራል የመንግስት አካላት መረጃ እንደሰጡና ከአባገዳዎች ጋር በተደረጉ ውይይቶች ከተለቀቁት ውጭ አራት ተማሪዎች በእገታ ላይ እንደሚገኙ በወቅቱ ገልፁ፡፡
ታህሳስ 27፣ 2012 ዓ.ም የፌድራልየፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ስለገታው አላውቅም ባለ ማግስት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያውቃል ሲሉ መሰከሩ፡፡
ከታህሳስ 25 ፣ 2012 ጀምሮ የታገቱ ተማሪዎች ምስልና ማንነት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ መንግስት እንዲያስለቅቃቸው የሚጠይቁ ድምፆች መበርከት ጀመሩ፡፡
ከታህሳስ 26 ፣ 2012 ዓ.ም የታገቱ ተማሪዎች ምስልና ማንነት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ መንግስት እንዲያስለቅቃቸው የሚጠይቁ ድምፆች መበርከት ጀመሩ፡፡
የሀገር ውስጥና የዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች የታጋች ቤተሰቦችን በማነጋገር የተለያዩ ዘገባዎችን ሰሩ፡፡
ጥር 2፣ 2012 ዓ.ም የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ቢቢሲ አማርኛ ስለጉዳዩ ጠይቋቸው በቁጣ “እኔ ምንም አልሰማሁም ነው የምልህ። ለምድን ነው የምትጠይቀኝ?” በማለት መለሱ።
ጥር 2፣ 2012 ዓ.ም የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዴሬሳ ተረፈ ለቢቢሲ ሚዲያ “ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም” በማለት ካዱ፡፡
ጥር 2፣ 2012 ዓ.ም ምሽት ላይ የጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢቲቪ በኩል 27 ተማሪዎች ታግተው እንደነበርና ከእነዚህም ውስጥ 21 ተለቀው፣ 6 እንደሚቀሩ አስታወቁ፡፡
ጥር 4፣ 2012 ዓ.ም ‹መረጃው የለኝም› ያሉት የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ፣ ለአንድ የውጪ ሀገር ሬዲዮ ጣቢያ ከእገታው የተለቀቁ ተማሪዎች በመንግስት እጅ እንደሚገኙና ሌሎችንም ለማስለቀቀ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ አስታወቁ፡፡
ጥር 5፣ 2012 ዓ.ም የታጋች ቤተሰቦችም ልጆቻቸውን ማግኘት ቀርቶ በስልክ እንዳላወሯቸው በእንባ እየታጀቡ ተናገሩ፡፡
ጥር 6 ቀን 2012 እስከ 20/2012 ዓ.ም የታጋች ቤተሰቦችን ጥያቄ እንዲመልሱ ጥያቄ የቀረበላቸው የመንግስት ባለስልጣናት ከሚዲያ ጠፉ፡፡
ጥር 11 ቀን
2012 ዓ.ም ጀምሮ ትዊተር በተሰኘው ማሕበራዊ መድረክ ላይ
#Bringourgirlsback #Bringourstudentsback #WhereAreTheStudents? #ተማሪዎችየትገቡ? የተሰኙ ዘመቻዎች በስፋት ተካሄዱ፡፡
ጥር 17፣ 2012 ዓ.ም የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ላቀ አያሌው የክልሉም ሆነ የፌድራል ተቋማት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም ሲሉ ለአማራ
ብዙሐን መገናኛ ድርጅት ተናገሩ፡፡
ጥር 18፣ 2012 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት ልዑክ የታገቱ ተማሪዎችን በተመለከተ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ከአንድ ቀን በፊት ማለትም እንደተሰበሰበ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘግቧል፡፡
ጥር 18፣ 2012 ዓ.ምበውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልና ከፍተኛ የመከላከያ እና የደኅንነት ኃላፊዎች በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ እየመከሩ ነው ተባለ፡
ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም. በአማራ ክልል በጎንደር፣ በደሴ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በዳንግላ፣ በወልዲያ፣ በደብረ ብርሃን፣ በባህር ዳርና በሌሎች በርካታ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ፡፡
ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በዚህ የጭንቀት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ዝም በማለታቸው ደግሞ ብዙዎች ግራ መጋባታቸውን እየገለጹ ነው፡፡
ማክሰኞ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም.የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አመራሮች ማየስድስት ወራት፣ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት፣ በምዕራብ ወለጋ የሚገኘው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መታገትን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከምክር ቤቱ በአባላቱ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር። በተቋሙ የተደራጁና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋ፣ የታገቱት ተማሪዎችን በተመለከተ ምርመራ መጀመሩንና ይህ ጉዳይ ተጣርቶ ዝርዝር ሁኔታው ቢገለጽ የተሻለ እንደሚሆን አመልክቱ።
ጥር 20፣ 2012 ዓ.ም የፌደራል ፖሊስ እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ “ተለቀቁ ብለን መግለጫ የሰጠነውም እውነት ነው፤ 21 የታገቱ ተማሪዎች ተለቅቀዋል፤ ቀሪዎቹን ለማስለቀቅ በትኩረት እየሠራን ነው” ሲሉ ከዚህ ቀደም የተናገሩትን ደግመውታል፡፡ ዘገባው የታጋቾችን ስምና ማንነት ባለስልጣኑ ስለመግለፃቸው ያለው ነገር የለም፡፡
ጥር 21 ቀን፣ 2012 ዓ.ም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ አጣሪ ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ጥር 21 ቀን ንፁሐን የአማራ ልጆች ከታገቱ በጫካ ውስጥ 60ቀናት አለፋቸው፡፡ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር፣ መከላከያ ሚንስትር ምንም ያሉት የለም፡፡ .����
Connect media Promotion, Program, and Advertising with us all over the region of Ethiopia, connecting 52 community radio stations in 54 languages.
Partner with us to amplify your media promotions, programs, and advertising across Ethiopia by leveraging our expansive network. We connect with 52 community radio stations broadcasting in 54 languages, ensuring your message reaches diverse audiences nationwide. Our network covers urban and rural regions, engaging listeners in their native languages for greater impact and resonance. This […]