የመረጃ ነፃነት፣ መረጃ የማግኘት መብት፣ ስርጭት እና ተደራሽነት By Ayele Addis Ameblu ayeleradio@gmail.com
መረጃ የማግኘት መብት ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አካል ቢሆንም መረጃ መግኘት የጋዜጠኞች እና የሚዲዎች ትልቁ ፈተና ሁኖ ለብሄራዊ መግባባት እንቅፋት እየሆነ ነው:: ማንኛውም ሰው መረጃን የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት መብት አለው፡፡(ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 19) መረጃ የማግኘት መብት ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አካል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ–መንግሥት፣ አንቀጽ 29 ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡
ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዐይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል፡፡
የመረጃ ተደራሽነት፡- በሕዝብ መረጃ ተደራሽነት ላይ ገደቦች፣ የመረጃ ክልከላ የኢንተርኔት መዘጋት እና የአስተዳደር ግልጽነት እጦት በመኖሩ ህዝብ የሚፈለገውን መረጃ በትክክለኛ ስዓት እና ቦታ አያገኝም፡፡ በዚህም ምክንያት ለሀሰተኛ መረጃ እና ለጥላቻ ንግግር በር ከፍቶ ለህዝቦች ግንኙነት እንቅፋት እየሆነ ይገኛል፡፡ በሀገሪቱ ለሚታየው ተጠያቂነት መጉደል፣ ኃላፊነትን መወጣት እንቅፋት በመሆኑ በሐገራዊ ምክክሩ ሂደት ከህግ ማዕቀፍ ስሪት እስከፖለቲካ ቁርጠኛ የውሳኔ ለውጥ ወይይት ቢደረግበት ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት አሻራ ይኖረዋል።ስንል በአጀንዳነት አቅርበነዋል፡፡
የአጀንዳው ማብራሪያ፡- መረጃ ማግኘት የሚዲያዎች ፈተና ሁኗል፡፡ በዚህም ምክንያት ለዘመናት አብሮ በኖረው ህዝብ መሀል አንድነትን የሚሸረሽር፤እርስ በእርስ በጥርጣሬ እንዲተያይ የሚያደርግ ከፋፋይ የሆኑ ንግግሮች፤ መግለጫዎችና ሀሳቦች በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት በስፋት ሲሰራጭ ተመልክቷል፡፡ አንዳንዶቹ አሉታዊ ይዘት ያላቸው ንግሮችና መግለጫዎች በመንግስት ባለስልጣናት፤በፖለቲካ ፖርቲ አመራሮች፤ በሀይማኖት ሰባኪያንና በምሑራን መደረጉን ስንመለከት መገናኛ ብዙኃን በሕጉ አግባብ ሙያዊ ነፃነታቸውን ተጠቅመው ስራቸውን ከፍ ባለ የኃላፊነት ደረጃ ለማከናወን የመረጃ አቅርቦት ፍትሃዊ አለመሆን አጀንዳ እንዲሆን ያስገድዳል፡፡
መገናኛ ብዙኃን በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 29 ሆነ ሀገሪቱ ፈርማ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮሎች መሠረት የሕዝብን አንድነት የሚንዱ፣ ጥላቻንና ግጭትን የሚያባብሱ ንግግሮችና ድርጊቶችን ማሰራጨት የለባቸውም፡፡ ንግግሮቹ በማንም ይነገሩ በማን ያለፉ ቁስሎችን ከሚቀሰቅሱ፣ ጥላቻን ከሚያነግሡ፣ ሕዝብ በጥርጣሬ እንዲተያይ የሚያደርጉና፣ የሀገርን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ መልዕክቶችን ከማሰራጨታቸው በፊት አስፈላጊውን የአርትኦት ስራ ሊሰሩባቸው እንደሚገባ ይደነግጋል፡፡
የኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰት መረጃ መከላከል አዋጅ ቁጥር 1185/2020 እንደተቀመጠው መገናኛ ብዙኃን በዘገባዎቻቸው ማናቸውንም የህብረተሰብ ክፍል በዘር፣ በብሔር፣ በፆታ፣ በሃይማኖት ወይም በፖለቲካዊ አስተሳሰብን መሠረት በማድረግ የሚሰጥ/የሚነገር/ ጥላቻን የሚያበረታታ፤ ሰብአዊ ክብርን የሚያዋርዱ የአደባባይ መግለጫዎችን ፤ ንቀትን ወይም መገለልን ሊፈጥር የሚችል ቋንቋን የሚጠቀሙ እንግዶችን ከመጋበዝ እና ከፋፋይ መግለጫዎችንም በማህበራዊ ሚዲያ ጭምር ከማሰራጨት የሚቆጠቡት አንድም ለሙያው ሰነ ምግባር ተገዥ መሆናቸው የሚረጋገጠው በቂ የመረጃ አቅርቦት እና አሰገዳጅ አሰራር ሲኖር ነው፡፡ ችግሮች በዝርዝር
- የመረጃ ገደቦች፡- ጋዜጠኞች በቢሮክራሲያዊ አሰራር ክልከላዎች እና ገዳቢ ህጎች ምክንያት የህዝብ መረጃን ለማግኘት እና ለህዝብ ለማድረስ ከፍተኛ እንቅፋት ይገጥማቸዋል።የኢትዮጵያ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ ከሽብር ጋር የተያያዘው ስለ ሽብር የሚያወራው የኢትዮጵያ ህግ የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አዋጅን በመንተራስ የጸረ-ሽብርተኝነት ህግን በተደጋጋሚ መረጃን ለመደበቅ መጠቀሙ ግልጽነት የጎደለው መሆኑን ያሳያል። በዚህ ወቅት ለፕሬሶች የሥነ ምግባር መርህን የያዘ መረጃ ለኅብረተሰቡ በአግባቡ ባለመሰጠቱ ሕዝቡ በትክክለኛው መንገድ ለአገር ግንባታ፣ ለሰላም፣ ለልማት ከመሳተፍ ይልቅ ሚዲያው በሚሰጠው የተሳሳተ መረጃ ወደ ግጭት፣ መራራቅ፣ ይህንንም ተከትሎ ወደ ሰላም ዕጦት ውስጥ እንዲገባ የራሳቸው አስዋፅኦ አድርገዋል፡፡
በዚሀም ብሄራዊ ምክክሩ በአጀንዳነት አዲስ የመረጃ ነፃነት አዋጅ እስከማፀደቅ የሚደርስ እና አሰገዳጅ መረጃ የማግኘት መብትን እና የህዝብን ጥቅም የሚያስጠብቅ እና በአሁኑ ወቅት ያለውን የመረጃ ብክለት እና ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል አይነተኛ መሳሪያ ሁኖ የሚያገለግል በመሆኑ ያለመንም ቅድመ ሁኔታ መፅደቅ እና መረጃን በማፈን ፣ ተጠያቂነትን የሚያፍኑ እና የህዝብን ጥቅም የሚጎዱ አካላትን በመከላከል ብሄራዊ መግባባትን ማምጣት ያስችላል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29(3)(ለ) መረጃ የማግኘት መብትን በግልጽ የተረጋገጠውን ድንጋጌ እንዲጠበቅ እና በዋናነት ችግር ሁኖ የቀጠለው የኢትዮጵያ መንግሥት የአስተዳደር ባህል በአብዛኛው ሚስጥራዊ በመሆኑ ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀምንና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ማስከተሉን በመረዳት፣ እንዲሁም የሕዝብ ጥቅምን የሚመለከቱ ጉዳዮች ግልጽ እንዲደረጉና ውይይት እንዲደረግባቸው ግልጽ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት አስፈላጊ ነው፡፡
የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 ዓ. ም ላይ እንደሰፈረው ዜጎች መረጃ የማግኘት ሕገ-መንግስታዊ መብት እንዳላቸውና የመረጃ ባለቤቶች መሆናቸውን ይደነግጋል። የመረጃ ነፃነት ይዞት ከተነሳው ዓላማ አንፃር በአግባቡ ቢተገበር በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉትም ተመልክቷል። ከጠቀሜታዎቹ መካከልም ግልፅነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፤ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል፤ ፍትህን ማስፈን እንዲሁም የዜጎች መብትና ጥቅሞችን ማስከበር ይጠቀሳሉ።
የመንግሥትና የግል አካላት ለግለሰቦችና ለመገናኛ ብዙኃን መረጃን ተደራሽ እንዲያደርጉ የሕግ ግዴታ ለመጣል፣ የሕዝብ ተሳትፎንና የሥልጣን ባለቤትነትን የማረጋገጥ፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ውጤታማነት የሰፈነበት የመንግሥት አሠራርንና መልካም አስተዳደርን ለማጠናከር በመወሰንና የመረጃ ነፃነትን ማረጋገጥ አለበት፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት አዲስ የመረጃ ነፃነት እና የማግኘት መብት አዋጅ ፀድቆ ወደ ስራ እንዲገባ መደረግ አለበት፡፡ በተመሳሳይም፡፡ ይህንን የሚከታተል ገለልተኛ የዴሞክራሲ መረጃን አሰተዳደር ተቋም ሊኖር ይገባል፡፡
2. የኢንተርኔት መዘጋት፡- በፖለቲካ አለመረጋጋት ወቅት የኢንተርኔት መዘጋት የመረጃ ፍሰትን የሚገድብ እና ዲጂታል ጋዜጠኝነትን የሚያዳክም መደበኛ መለኪያ ሆኗል። በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ግጭትን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ (2020-2024) ዘገባዎችን እና ሰብአዊ ጥረቶችን በከፍተኛ ሁኔታ አግዶታል።
3. ግልጽነት ማጣት፡- የመንግስት ባለስልጣናት ብዙ ጊዜ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተጠያቂነትን ያዳክማል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ጋዜጠኞች በሕዝብ ወጪ እና አስተዳደር ላይ ወሳኝ መረጃዎችን በተደጋጋሚ እንዳያገኙ ይከለከላሉ።
ተጽዕኖ
• የምርመራ ጋዜጠኝነት እንዳይሰፋፋ እንቅፋት መሆን።
• ሙስናን ያስፋፋል
ተጠያቂነት እንዳይኖር ያደርጋል።
የመረጃ ሰርጭትን ይገድባል፡፡
• የተሳሳተ መረጃ እና የህዝብ አለመተማመን አሰፍኗል። የነዚህ ቁልፍ ችግር መፍትሄ በብሄራዊ የምክክር አጀንዳ ቢሸፈን አውንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
ምክሮች
1. የመረጃ ተደራሽነት ህጎችን ማውጣት፡ የመረጃ ነፃነት እና የመረጃ ተደራሽነት ሞዴል ህግ በማውጣት የህዝብን ተደራሽነት ለማረጋገጥ ጠንካራ የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት። የመረጃ አሰተዳደርን የሚመራ ገለልተኛ ዴሞክራሲያዊ ተቋም እንዲኖር መታሰብ አለበት፡፡ 2. የኢንተርኔት መዝጋትን መከልከል፡ ብሄራዊ ፖሊሲዎችን ከሰላማዊ ተቃዋሚዎች አንፃር የሰብአዊ መብቶችን ማስተዋወቅ እና ከመሳሰሉ አለም አቀፍ ደረጃዎች ጋር ማጣጣም። በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው የበይነ መረብ ጋዜጠኞችና ፈቃድ ያለው ማንኛውም የሚዲያ ተቋም ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት እስካገኘ ድረስ በመደበኛው መገናኛ ብዙሃን እና በበይነ መረብ የሚተገበሩ የአገልግሎት መድረክ ወይም ፎርማት (ድረ ገፅ፤ዩ ቲዩብ፤ ፌስ ቡክ፤ቲውተር፤ኢንታግራም፤ሊንክዲን ወዘተ)ሁሉንም ሙያዊ ስነ-ምግባር እና የጋዜጠኝነት ዋና እሴቶችን እስካከበሩ ድረስ ገደብ ሊጣልባቸው አይገባም፡፡
3. ተደራሽ የመረጃ አቅርቦትን ማሳደግ፡ የመንግስት ባለስልጣናትን በግልፅነት አሰራር ላይ ማሰልጠን እና መረጃን በወቅቱ ለማሰራጨት መድረኮችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

ማንኛውም ሰው መረጃን የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት መብት አለው፡፡(ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 19)
መረጃ የማግኘት መብት ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አካል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 29
ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡
ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዐይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል፡፡
ሲሳይ ሳህሉ ከሪፖርተር የመረጃ ነፃነትና መረጃ የማግኘት ፈተናዎች ሲል እንደዘገበው
በኢትዮጵያ መረጃን የማግኘት መብት አሁን በሥራ ላይ ባለው የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 ክፍል ሦስት ላይ፣ ዜጎች መረጃ የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳላቸውና የመረጃ ባለቤቶች ስለመሆናቸው በግልጽ ሠፍሯል፡፡
መረጃን የማግኘት መብት ሲባል ከማንኛውም መንግሥታዊ አካል ዜጎች መረጃን ለመጠየቅ፣ ለማግኘትና ለማስተላለፍ ያላቸውን መብት እንዲረጋገጥ፣ መረጃ ፈላጊዎች በተቻለ መጠን በፍጥነትና በዝቅተኛ ወጪ ሳይደክሙ የሚያገኙበት አሠራርና ሥነ ሥርዓት በመመሥረት፣ መብቱ ተፈጻሚ እንዲሆን የሚፈቅድና የሕዝብ ተሳትፎና የሥልጣን ባለቤትነትን የማረጋገጥና የአሠራር ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ውጤታማነት የሰፈነበት የመንግሥት አሠራርና መልካም አስተዳደር የማጠናከርን ዓላማ የያዘ መሆኑ በአዋጁ ተብራርቷል፡፡
የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ በሚል ስያሜ በ2000 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ሥራ ከጀመረ 14 ዓመታት ገደማ የሆነው ይህ አዋጅ፣ በ2013 ዓ.ም. የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ተሻሽሎና ራሱን ችሎ እንደገና መውጣቱ ይታወሳል፡፡ የመረጃ ነፃነት አዋጅም እንደገና ተሻሽሎና ረሱን ችሎ እንዲወጣ ረቂቁን በዝግጅት ላይ ቢሆንም፣ እስካሁን ፀድቆ ወደ ሥራ ሊገባ አልቻለም፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የሕግ ማሻሻያ ሪፎርሞች አካል የሆነው ረቂቅ የመረጃ ነፃነት አዋጅ ፀድቆ፣ የመንግሥት አካላት በአምስት ቀናት ውስጥ ለሚዲያዎች ምላሽ እንዲሰጡ የሚል ድንጋጌ ይዟል፡፡ በተጨማሪም የመንግሥት አካላትን የሐሳብ ልውውጥ ሊያሰናክል የሚልችል መረጃ የሚከለክል ሲሆን፣ አዋጁ የመረጃ ነፃነት ኮሚሽን እንደሚቋቋም ይደነግጋል፡፡
አሁን በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ክፍተቶች እንዳሉበትና በግልጽ በተደነገጉት አንቀጾች በቀላሉ መሥራት እንደሚቻል፣ በዚህም ሳቢያ ሕዝቡ በቀጥታም ሆነ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት መረጃ የማግኘት መብቱ የተነፈገ መሆኑን በተለያየ መንገድ ይነገራል፡፡
በቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) አገዛዝ ቁጥጥር ሥር አስቸጋሪ ይባል የነበረው የመረጃ ነፃነት ጉዳይ፣ በ2010 ዓ.ም. ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ሥልጣን ተረክበው መንግሥታዊ ለውጥና ሪፎርም ሲያደርጉ በሚዲያ ኢንዱስትሪው ከኢትዮጵያ አልፎ ዓለምን
ጭምር ያስደሰተ እንቅስቃሴ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ ብዘዎችን ዕፎይታ ሰጥቶ የነበረው ተስፋ እንደ ጠዋት ጤዛ ታይቶ ወደ ነበረበት የመንግሥት ቁጥጥር ሥር ለመመለስ ጊዜ እንዳልፈጀበት ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
ለዚህ ማሳያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመገናኛ ብዙኃን ከመንግሥት ተቋማት መረጃ ማግኘት ፈታኝ እየሆነባቸው መምጣቱን፣ የተቋማትን ኃላፊዎችን የማያስደስት መረጃ በሚዲያ ሲነገር አኩራፊዎች መብዛታቸውን ጋዜጠኞች በተለያዩ መድረኮች ሲያነሱት መስማት የተለመደ ነው፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ከተቋማት መረጃ ማግኘት ፈታኝ እንደሆነባቸው ሌላው ማሳያ፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. የመገናኛ ብዙኃንን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማው ሲያቀርቡ ያሰሙት ቅሬታ ነው፡፡
የመንግሥት ተቋማት ስለሚያከናውኑት ሥራ ተገቢውን መረጃ የመስጠት ኃላፊነት ቢኖርባቸውም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን፣ ጉዳዩ አዳጋች በመሆኑ ለሚዲያዎች መረጃ በማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነት የሚረጋገጥበት ሥርዓት እንዲዘረጋና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትኩረት እንዲሠራበት ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀው ነበር፡፡
በተመሳሳይ ከጥቂት ወራ በፊት የፌዴራል ዋና ዕንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ (ዶ/ር) ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የመረጃ ነፃነት አዋጁ በግልጽ እንዳስቀመጠው አስፈጻሚ አካላት ከሕዝብ በሚሰበሰብ ግብር የሚተዳደሩ ቢሆኑም፣ ለሕዝቡ የሚጠበቅባቸውን መረጃ እያደረሱ አለመሆናቸውን መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
የመንግሥት ተቋማት ከሕዝብ በሚሰበሰብ ሀብት የሚተዳደሩ ከሆነ ስለሠራተኞቻቸው፣ ስለመዋቅራዊ አደረጃጀታቸው፣ ስለፖሊሲያቸውና በአጠቃላይ ስለሚሰጡት አገልግሎት ለኅብረተሰቡ በየወቅቱ መረጃ ይፋ ማድረግ ቢኖርባቸውም፣ የአስፈጻሚ አካላቱ የመረጃ አሰጣጥ ግን የተቋማቸውን ገጽታ ይጠብቁልኛል የሚሏቸውን መረጃዎች እየመረጡ መስጠት ላይ ብቻ እንደሚያተኩር ዋና ዕንባ ጠባቂው አስረድተው ነበር፡፡
ለዚህም የመረጃ አሰጣጥ ክፍተት በአስፈጻሚው አካል ያሉ ኃላፊዎች መረጃ ለመስጠት ያላቸው የፈቃደኝነት ችግር፣ እንዲሁም በየተቋሙ ያሉ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በሚጠበቅባቸው ልክ ራሳቸውን አለማዘጋጀታቸው ምክንያት እንደሆነ መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡
የመረጃ ነፃነትን ተግባራዊነት የሚከታተለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ የመረጃ ነፃነት ሕግን በተሻለ መንገድ ለማስተግበር ያግዛል ያለውን የምክክር መድረክ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም. አዘጋጅቶ ነበር፡፡
በውይይቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የክልል ምክር ቤቶች ተወካዮች፣ የሕግ፣ የፍትሕና የዴሞክራሲ ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ የክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮዎች፣ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የውይይቱ ታዳሚ ነበሩ፡፡
በውይይቱ ንግግር ያደረጉት ዋና ዕንባ ጠባቂው እንዳለ (ዶ/ር)፣ በየዘመኑ ወደ ሥልጣን የሚመጡ መንግሥታት ሥልጣን በተረከቡ ማግሥት ፈጥነው ለውጥ ወይም ሪፎርም ከሚያደርጉባቸው መስኮች መካከል የሐሳብና የአመለካከት ነፃነት፣ የመገናኛ ብዙኃንና የፕሬስ ወጤቶችን ያለገደብ ተግባራዊ ማድረግና የመሳሰሉ ቢሆኑም፣ በሚከናወነው ለውጥ ኅብረተሰቡ መሸከም በሚችለው አቅም ልክ እያመዛዘኑ ተግባራዊ ያለማድረግ ችግር እንደሚስተዋልባቸው ጠቁመዋል፡፡
በዚህ ገድብ የለሽ ነፃነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረግ ግብግብ የሕግ የበላይነት፣ የዜጎች ሰላምና ደኅንነት በቀላሉ አደጋ ውስጥ እንደሚወድቅና በዚህ ሳቢያ የነበረውን ጥሩ ጅማሮ ወደ ሌላኛው ያልተገባ ጫፍ በአንድ ጊዜ በመቀየር፣ የዜጎች የሐሳብና የአመለካከት ነፃነት ላይ ልክ የሌለው ገደብ እንደሚጣል አስረድተዋል፡፡
በእነዚህ መሰል ውጣ ውረዶች ኅብረተሰቡ የፕሬስ ነፃነትን በውል ሳይረዳው ወጥነት ባለው መንገድ እንዲለማመድ ከማስቻል ይልቅ ግራ ሲጋባ እንደሚታይ የገለጹት እንዳለ (ዶ/ር)፣ በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከዚህ የራቀ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የመረጃ ነፃነት ዳይሬክተር አቶ ማናዬ ዓለሙ፣ ለውይይቱ ያቀረቡት የመነሻ ጽሑፍ ይህንኑ የመረጃ አሰጣጥ ችግር በግልጽ ያንፀባረቀ ነበር፡፡ ምንም እንኳ በአዋጁ ላይ ስለመረጃ ተደራሽነት በግልጽ የተቀመጠ አቅጣጫ ቢኖርም፣ ተቋማት ሁልጊዜም የሕዝብን ጥቅም የሚመለከቱና በእጅ ላይ ያለን መረጃ አትሞ የማሠራጨት ግዴታ ቢኖርባቸውም፣ አሁን የሚታየው መረጃን አትሞ የማውጣት ሥራ የሚፈራበትና ኩነኔ የመሰለ አሠራር መስፈኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ለሕዝብ አገልግሎት ተብለው የሚታተሙ ጽሑፎች በፎቶ የታጨቁ፣ አልበም የሚመስሉና በቂ መረጃ የሌላቸው መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በድረ ገጾችና በሌሎች የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸው የሚለቋቸው መረጃዎችም ቢሆኑ የተቋማት ኃላፊዎች ጉብኝት አደረጉ ወይም ለስብሰባ ተቀመጡ ከማለት ውጪ ለሕዝብ ፋይዳ የሌላቸው፣ የተቋማቱን በጀትና ዕቅድ አፈጻጸም ጥንካሬና ድክመት ነቅሰው የማያሳዩ እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡
ብዙዎቹ ተቋማት የመረጃ ማዕከልና ቋት የሌላቸው ከመሆናቸውም በላይ፣ በመገናኛ ብዙኃንና በሕዝብ ግንኙነት መካከል ጣት መቀሳሰር እንጂ ለአንድ አገራዊ ዓላማ የቆሙ አለመምሰልና በጎሪጥ የመተያየት ዝንባሌ መኖሩን በመጥቀስ፣ የመረጃ ነፃነት የሚባለው ጉዳይ ተግራዊ አለመሆን በስፋት መስተዋሉን ተናግረዋል፡፡
አሁን በሥራ ላይ ላለው የመረጃ ነፃነት አዋጅ ክፍተት እንደ ምክንያት የተጠቀሰው ለዜጎች መብት መከበር የመንግሥት ኃላፊዎች ያላቸው ግንዛቤና ቁርጠኝነት አናሳ መሆን፣ የሕዝብ ግንኙነት መዋቅር ደካማና ሙያዊ ሥነ ምግባር የጎደለው መሆኑ፣ የተቋምን መልካም ገጽታ ለመገንባትና ከፍ ከፍ ለማድረግ እንጂ ክፍተት ከተቋሙ ውጭ እንዳይነገር ለመሥራት የተቀመጡ የሚመስላቸው በመሆናቸው እንደሆነ አቶ ማናዬ አክለው አስረድተዋል፡፡
በሌላ በኩል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ሹመት ሙያን መሠረት ያላደረገ፣ የፖለቲካ ዝንባሌና ወገንተኝነት ላይ ያደላ፣ በአጠቃላይ በተቋማት ውስጥ ስለመረጃ ነፃነት ሲነሳ በተለያዩ ችግሮች የተተበተበ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
ለመረጃ ነፃነት አዋጅ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ ደንቦችና ሚስጥራዊ መረጃዎች ይፋ ስለሚደረጉበት አሠራር የሚወስን ደንብ አለመኖር፣ አዋጁ መረጃ በማይሰጡ አካላት ላይ ስለሚወሰደው ዕርምጃ በግልጽ አለመቀመጡ ለመረጃ ነፃነት ክፍተት ሌላው ምክንያት እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡
የመረጃ ነፃነት አዋጁ እንደ ማሟያ ሕግ ሆኖ ብቻ እያገለገለ መሆኑን በመጠቆም፣ መንግሥታዊ ሥርዓቱ የተዘረጋው ሕዝብን ለማገልገል ከሆነ አሠራሩን ማስተካከል ካልተቻለ አካሄዱ፣ ‹‹ውኃውን እያፈሰሱ ቧንቧውን እንደ መንከባከብ›› መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም እነዚህ ተቋማዊ የመዋቅርና የአሠራር ክፍተቶች መላ ካልተፈለገላቸው፣ የመረጃ ነፃነት የሚባለው ጉዳይ ሊሳካ የማይችል መሆኑን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ሆነ የክልል ምክር ቤቶች የተቋማተን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ሲገመግሙ፣ የመረጃ ነፃነትን እንደ አንድ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲገመገም ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል፡፡
የናሁ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብሩክ ኃይሉ (ፕሮፌሰር)፣ የመንግሥትና የግል ሚዲያ በሚል በፌደራል መንግሥቱ በኩል የሚታየው የግል ሚዲያን እንደ በጥባጭና እንደ የማይታመን አድርጎ የመፈረጅ፣ በተቃራኒው ደግሞ የመንግሥት ሚዲያን እንደ ታማኝ ተቋም በማየት መረጃን ለይቶ ለመንግሥት ሚዲያ ብቻ የመስጠት አዝማሚያ በስፋት ስለመኖሩ አስረድተዋል፡፡ ችግሩ የግል ሚዲያ ውስጥ አለ እንደሚባለው ሁሉ በመንግሥት ሚዲያ ወስጥም መኖሩን በመጠቆም፣ ‹‹በግል ሚዲያው ላይ ያለው ፍራቻና ጥርጣሬ ምንድነው? እኛም እኮ ለአገራችን እናስባለን፣ እንቆረቆራለን፤›› ብለዋል፡፡
አክለውም በኢትዮጵያ የማስፈጸም አቅም እንጂ የአዋጅ እጥረት ባለመኖሩ፣ ፓርላማው በአዋጁ አፈጻጸም ላይ ጠንካራ ክትትል እንዲያደርግ በመጠየቅ፣ የመንግሥትና የግል ሚዲያ እንደ ባላንጣ መተያየት የለባቸውም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የአሻም ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥበቡ ታደሰ ሕዝቡ የሚፈልገውንም ሆነ የሚያስፈልገውን መረጃ የማግኘት መብት ቢኖረውም፣ በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ እየደረሰው ያለው መረጃ የሚፈልገው ወይም የሚያስፈልገው ሳይሆን፣ መንግሥት የሚፈልገውን ብቻ እየመረጠ ነው ብለዋል፡፡
መንግሥት በአብዛኛው መረጃ ሰጪ አካል በሆነበት አገር መረጃ የሚያደርሱት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ወይም የተቋም አመራሮች፣ በየትኛውም መመዘኛና በየትኛውም አገር ሆኖ በማያውቅ ሁኔታ መንግሥትን ምሉዕ አድርገው የሚያቀርቡ ስለሆነ፣ መንግሥት የሚሰጠው መረጃ በራሱ ትልቅ ጥያቄ ያለበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም መንግሥት ራሱን ፍፁማዊ አድርጎ እኔ ብቻ ልሰማ በማለት እየሄደበት ያለው መንገድ፣ ከሚዲያ ተቋማት ጋር የሚያጋጭ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አንዳንድ የመንግሥት ተቋማት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የሚለቋቸው ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ መረጃዎችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በየመድረኩ እየወጡ ሕዝብን ከሕዝብ የሚለያዩ ንግግሮች በብዛት በሚደመጥበት አገር፣ በሚዲያ ተቋማት ላይ የሚደረገው ተጠያቂነት ዙሪያ ገባውንም የሚቃኝ መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በ2000 ዓ.ም. የወጣውና ለ14 ዓመታት በሥራ ላይ ለነበረ የመረጃ ነፃነት አዋጅ አሁን የመመርያ ክፍተት፣ የመንግሥት ቁርጠኝነት፣ የአተገባበር ድክመትና የመሳሰሉ ችግሮችን ከማንሳት ይልቅ ችግሮቹን ሊመጠን በሚችል አቅም መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ አዋጁ እንዲሁ እንዳለ ሆኖ ከእነ ክፍተቶቹ ለመሥራት ሙከራ ሳይደረግ፣ አስገዳጅ መመርያ ስለሌው የሚለው ዕሳቤ በራሱ ምክንያት ሊሆን አይገባውም ብለዋል፡፡ ለዚህም እንደ ማሳያነት የጠቀሱት የጠያቂና የተጠያቂነት ሥርዓት ባለመኖሩ ምክንያት በኢትዮጵያ በሚገባ የተዘጋጁ፣ ነገር ግን በርካታ አስገዳጅ የሆኑ መመርያዎች ያሏቸው አዋጆች ተግባራዊ እንደማይደረጉ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ እየወጡ ያሉ ሕጎች አስገዳጅ የመሆንና ያለ መሆን ችግር ሳይሆን፣ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ባለመኖሩ በተለይ አሁን ባለው ሁኔታ የፖለቲካ የበላይነት መግዘፉን ጠቁመው፣ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲበጅ አቶ ጥበቡ ጠይቀዋል፡፡
የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) መረጃ ለመንግሥት ሚዲያዎች ብቻ እንጂ ለግል ሚዲያ አይሰጥም የሚባለውን ቅሬታ በተመለከተ፣ በአሁኑ ጊዜ መረጃ እያገኙ ያሉት የግል ሚዲያዎች ናቸው በሚል ወቀሳ እየቀረበ ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም አንድ ጋዜጠኛ ሙያውን እስከጠበቀ ድረስ የመንግሥት ጉድ አይነገር የሚል አገርም ሆነ አመራር የለም ሲሉ አክለዋል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትሕና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዕፀገነት መንግሥቱ በበኩላቸው፣ የመረጃ ነፃነት ሲታሰብ የተቋም ግንባታ በሚል ምክንያት መረጃ በተገቢው ቦታና ሰዓት ለሚፈልገው አካል አለማድረስ ይዞት የሚመጣው ቀውስ ከባድ ከመሆኑም በላይ፣ እንደ ኋላቀርነት ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል፡፡
‹‹የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ማንኛውንም መረጃ የማይሰጥ የመንግሥት ተቋም ዘርዝሮ ያቅርብልን፤›› ሲሉም አሳስበዋል፡፡
The right to access to information is an integral part of the right to freedom of expression
Everyone has the right to seek, receive and impart information. (Article 19, Universal Declaration of Human Rights)
The right to access to information is an integral part of the right to freedom of expression.
Ethiopian Constitution, Article 29
Everyone has the right to freedom of expression without any interference.
This right shall include freedom to seek, receive and impart information and ideas of all kind regardless of frontiers, either orally, in writing or in print, in the form of art, or through any media of his choice.
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጠኞችን ልትመዘገብ ነው፡፡ "Ethiopia Begins Journalist Accreditation for the First Time in History"
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ለጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች ወጥነት ያለው የሙያ ማንነት መለያ ምዝገባ፣ የብቃት ማረጋገጫ እና መታወቂያ ዕውቅና አሰጣጥን ለመተገበር ያዘጋጀውን መመሪያ እና ደንብ በመገምገም ግብዓት እንድትሰጡን ስለመጠየቅ፣ ይህ በጋዜጠኞች፣ የህግ ባለሙያዎች፣ የሚዲያ ተመራማሪዎች ቅንጅት ሰፊ ምርምር ተደርጎበት የተዘጋጀ ሰነድ በመፈተሸ ለላቀ ዝግጅት አሰተያየትዎን በመሰጠት እንዲያግዙን እንጠይቃለን፡፡ በዚህም በሚዲያ ተቋማት ምዝገባ […]