በየካቲት 1966 ዓ.ም የኢትዮጵያ አብዮት ፈነዳ፤ ህዝቡ ከዳር እስከዳር የሃይለስላሴን ዘውዳዊ አገዛዝ በመቃወም ተነሳ፡፡- በወቅቱ የነበረውን የነዳጅ ዋጋ መናርና የኑሮ ውድነትን መነሻ በማድረግ ታክሲ ነጂዎች፣ መምህራን፣ ጦርሰራዊት…. የሸቀጦች ዋጋ እንዲቀነስ፣ ደመወዝ እንዲሻሻል… በመጠየቅ አደባባይ ወጡ- የወሎ ርሃብና ያስከተለው ጉዳት በመንግስቱ ላይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ፣ ህዝብ ሲያልቅ ደንታ የማይሰማው ፊውዳልላዊ መንግስት ይውረድ የሚሉ መፈክሮችን ያነገቡ ወገኖች በተለያዩ የአገራችን ከተሞች ለሰላማዊ ሰልፍ ወጡ፤- የሃይማኖት እኩልነት፣ የብሔሮች መብት፣ የሴቶች እኩልነት እንዲከበር የሚጠይቁ፣ በስርአቱ ላይ የሚታየው የፍትህ መጓደል፣ የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች አፈና እንዲወገድ የሚጠይቁ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ተቀጣጠሉ፤ – በአጠቃላይም የኢትዮጵያ ህዝብ ማንም ሳይቀሰቅሰውና ሳያደራጀው ሶስቱን የአብዮቱ ቁልፍ ጥያቄዎች በማንሳት በስርአቱ ላይ አመፀ፡፡ አብዮቱ በአጭር ጊዜ ውስ በመላ አገሪቱ ቢቀጣጠልና ግለቱ ሳይበርድ ቢቀጥልም ደርግ የሃይለስለላሴን መንግስት በመፈንቀል ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተደዳር መንግስት መሰረተ::

Happy World Radio Day 2024!
Happy World Radio Day 2024! “The Role of Radio for Peace and Development” by Ayele Addis Ambelu: Presentation with Ethiopian journalists: contact emmanews23@gmail.com Today, we celebrate radio’s remarkable past, relevant present, and promising future. Did you know that 96% of Ethiopians listen to the radio? Let’s take a moment to appreciate its role in informing, […]