Skip to content
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • Latest

ንጉስ ኢስዋቲኒ የዚምባብዌን ልማት ፕሮጀክቶችን አድንቁ።

The Ethiopian Media Council released press due to the current situation in Ethiopia regarding the issues about online media houses.

  • AFRICA
  • Latest
  • Magazine
  • News
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES
  • TOP VIDEOS

በአዲሱ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ፣  ምን እንገበያለን፣ ምን ይቀይራል

Ayele Addis June 13, 2023February 2, 2024

በመሰለች ዘላለም (armamedia7@gmail.com)

የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ‹‹ቀልጣፋ የፋይናንስ አሰራር፣ የተሻለ የቁጠባ  አቅም፣ ሰፊ የኢንቨስትመንት እድል፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚፈጥር አዲስ መንገድ ነው፡፡››

የካፒታል ገበያ ስርአት፣የኩባንያ ባለቤቶች ለግለሰቦች ሸር በመሸጥ ገንዘብ እንዲያሰባስቡ ያስችላል፡፡ በካፒታል ገበያ ከሸር በተጨማሪ የብድር ሰነዶችም ይሸጣሉ፡፡ ‹ካፒታል ገበያ ማለት በተለምዶ ‹‹ስቶክ ማርኬት›› ማለት ነው፡፡  ካፒታል ማርኬት ገንዘባቸውን ለጊዜው ለሌላው ሰው በመሸጥ (በማከራየት) ተጨማሪ ጥቅም የሚያገኙ ሻጮችን የሚፈጥር አሰራር ነው፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ ካፒታል በማሰባሰብ የገንዘብ ሥርዓቱን በአዳዲስ ፈጠራዎች በመደገፍ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ልማት የሚያጠናክር የካፒታል ገበያ ‘በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013’ ተቋቁሟል። በዚህ አዋጅ መሰረት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነ “የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን” መስሪያ ቤት ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሰነድ መዋዕለ ንዋዮችን በማውጣት የግብይት ሥርዓቱን ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ የተሟላ የካፒታል ገበያ ስነ- ምህዳር የመፍጠር ስልጣን ተሰጥቶታል። ኢንቨስተሮችን በመጠበቅና ከለላ በመስጠት ኢንቨስትመንቱን ለማበረታታት ምቹ ሁኔታን መፍጠርና የካፒታል ገበያው ተዓማኒነት እንዲኖረው የማድረግ ኃላፊነትም አለበት።

የገበያ ሀብት መፈጠር አላመው ያደረገው ይህ ተቋም የኢኮኖሚ ነፃነት የሽግግር ምዕራፍም ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የስቶክ ማርኬትና ኢንቨስትመንት መጽሐፍ ደራሲ  ዶ/ር  አቡሽ አያሌው እንደገለፁት ገንዘቡን ከአቅራቢዎች ማለትም ከሻጮች (አከራዮች) አስፈላጊውን ተጨማሪ ተመን በመክፈል ሥራ ላይ በማዋል ከገዙበት ዋጋ በላይ ከፍ ያለ ጥቅምን (ትርፍን) የሚያገኙ ገዥዎችን የያዘ ነው፡፡ የዚህ የካፒታል ገበያ ዋና ዓላማው ገንዘቡን የሚወክሉ ሰነዶችን በመሸጥና በመግዛት ውስጥ ተጨማሪ ገንዘብን የማግኘት ትልምን የያዘ መሆኑ ለየት የሚያደርገው ነው፡፡ ከሌሎች የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች የሚያመሳስለው ገንዘብም እንደ ሸቀጥ የሚገዛና የሚሸጥ መሆኑ ነው፡፡ ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት የሚያስችሉት ደግሞ መገበያያ ሰነዶች ናቸው፡፡››

ዶ/ር  አቡሽ አያሌው ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አለመጀመሯ ያስከተለውን ጉዳት አስመልክቶ ሲገልፁ ‹‹በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለመቋቋሙ ምክንያት ለኢንቨስትመንትና ፕሮጀክቶች የሚያስፈልግ ካፒታል ማመንጨት አልተቻለም፡፡ በዚህም ሳቢያ አገሪቱ ትልቅ ሀብት ሲያሳጣት ከዚህ በተጨማሪም፣ የተቀናጀ የአክሲዮን ገበያ አለመመሥረቱ በርካታ የኢኮኖሚ ጉዳቶች ማስከተሉ ሲነገር ስቶክ ማርኬት ካፒታሊዝም የፈጠረውን የኑሮ ውድነትና የኢኮኖሚው ጥረት ችግር የሰዎችን የካፒታል ምርታማነት በማሳደግ፣ ሰዎች ወደ ኢኮኖሚ ነፃነት የሚያሸጋግር ትልቅ የኢንቨስትመንት ድልድይ ነው፡፡›› እንደ ዶ/ር  አቡሽ ገለፃ ስቶክ ማርኬት ይዞት የሚመጣውን የካፒታል ምርታማነት ዕድል መጠቀም አለመቻል ወቅቱ የሚጠይቀውን ብልህነት አለመረዳት ይሆናል በማለት ይገልጻሉ፡፡

የአገራችን ባንኮች ለግሉ ዘርፍ ብድር ለመስጠት የኩባንዎች የፋይናንስ አፈጻጸም መሥፈርታቸው አንዱ ቢሆንም፣ የዋስትና መያዣ ጉዳይ ግን ትልቅ ፈተና ነው፡፡ ለተበደረው ገንዘብ ትልቁ መተማመኛ ከአሁን ቀደም ድርጅቱ ያሳያቸው ትርፋማነቶች እንደ አንድ መሥፈርት ቢሆኑም፣ የድርጅቱ የገበያ ዋጋ ግን ትልቁ መሠረት ነው፡፡ የስቶክ ማርኬት ሥርዓት ትልልቅ የገበያ ሀብት (ማርኬት ካፒታላይዜሽን) ያላቸው ድርጅቶች የሚያፈራ በመሆኑ፣ ከባንኩ የፈለጉትን ያህል ብድር ለመውሰድ ያስችላቸው ነበር፡፡ በኢትዮጲያ  ስቶክ ማርኬት ባለመኖሩ ታዲያ ብዙ ድርጅቶች መጎዳታቸውን ያስረዳሉ፡፡

ለአገር እየጠቀሙ ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ አገር ዜጎች ከተከለከሉ ዘርፎች ውስጥ አንዱ ታዲያ ስቶክ ማርኬት ነው የሚሉት አቡሽ አያሌው (ዶ/ር) የአገሪቱን 30 በመቶ ጥቅል ምርት የሚያበረክተው የግሉ ዘርፍ ሲሆን፣ ቀሪውን 70 በመቶ ኢኮኖሚ የሚቆጣጠረው ደግሞ መንግሥት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችም ሆነ የግሉ ዘርፍ ለማደግ ለሥራ ማስኬጃም ይሁን ለማስፋፊያ ኢንቨስትመንት ጥሬ ብርና ጥሬ ዶላር በእጅጉ እያስፈለጋቸው ማደግ የሚችሉትን ያህል ዕድገት ሳያድጉ፣  መቅጠር የሚችሉትን ያህል ሰው ሳይቀጥሩ መፍጠር የሚችሉትን ያህል ዕድገት ሳያድጉ፣ አዳዲስ ምርቶች ሳይፈጥሩ ቀርተዋል፡፡

የካፒታል ገበያ በዶላር እጥረት የተቸገሩ አምራች ድርጅቶችና ባንኮች በባንክ ብድር እጥረትና ወለድ ሳቢያ ተወዳዳሪ መሆን ያልቻሉትን ችግር የሚቀርፍ ነው፡፡ ዶ/ር አቡሽ አያሌው ‹‹የካፒታል ገበያ አለመኖሩ የንግድ ማኅበረሰቡ አማራጭ ገንዘብ እንዲፈጥርለት አላስቻለም፡፡ በዓለም ላይ እንደ ጎርፍ የሚፈስበት ትሪሊየን የሚቆጠር ዶላር ያለ ሲሆን፣ ይህን ሊያመጣ የሚችል የካፒታል ገበያ ሥርዓት መዘርጋት ባለመቻላችን ብቻ ብዙ ሀብት አጠናል፡፡›› ይላሉ፡፡ በዓለም ላይ በየቀኑ ከአራት ትሪሊዮን ዶላር የሚሆን ዋጋ ያለው የስቶክ ግብይት የሚደረግ ሲሆን በዚህ ግዙፍ ገበያ ውስጥ አገራችን አለመኖሯ ያስቆጫል ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

የስቶክ ማርኬት አለመኖር በድርጅቶች መካከል ውድድርና ፈጠራ እንዳይዳብር ሲያደርግ  ስቶክ ማርኬት ከተገበሩ አገሮች ውስጥ የውድድርና የፈጠራ አቅም ከፍ ያለ ፍጥነት አለው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የስቶክ ዋጋቸው በውድድርና በፈጠራ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ብዙ ሰው ገንዘቡን ባንክ ከማስቀመጥ፣ ባንክ በስቶክ ማርኬት ውስጥ ኢንቨስት በማድረግ የተለያዩ ድርጅቶችን የባለቤትነት ዕድል መጋራት ያስችለዋል፡፡ ዶ/ር አቡሽ አያሌው ይህ መሰል ስሜት በአገር ደረጃ ሲዳብር የአገር ሰላም ከመዳበር በተጨማሪ በአገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለተፈጠረው የሕዝብ ተቃውሞ አንዱ መነሻም ይኸው የሀብት ክፍፍል ጉዳይ መፍትሄ ይሰጣል ይላሉ፡፡  ዶ/ር አቡሽ አያሌው፣ ይህንን ሐሳብ የሚያጠናክሩትም የአሜሪካን ተሞክሮ በመጥቀስ ሲሆን፣ 45 በመቶ የአሜሪካ ሕዝብ የስቶክ ማርኬት ተጠቃሚ መሆኑን ስንመለከት ምን ያህል የአሜሪካንን 80 በመቶ ኢኮኖሚ የያዙት 20 በመቶ የሆኑት በኮርፖሬሽን ደረጃ የተዋቀሩ ትልልቅ የግል ድርጅቶች 45 በመቶ በሆነው የአሜሪካ ሕዝብ ባለቤትነት ድርሻ እንደተያዙ ይታወቃል በማለት ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ባለፈ ለአገር ሰላም የሚያበረክተውን አዎንታዊ ሚና ያስረዳሉ፡፡

አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የፌርፋክስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ሊቀ መንበር ናቸው። የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮችም በቅርበት ይከታተላሉ። ለስቶክ ማርኬት ‘የድርሻ ገበያ’ የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን ይላሉ።

ኩባንያዎች የኩባንያውን የባለቤትነት ድርሻ ለገበያ ያቀርባሉ። ሰዎችም ይህን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነ መጠን ያላቸውን ድርሻ መልሰው በመሸጥ ወይም ከትርፍ ክፍፍል ትርፋማ የሚያደርግ አሠራር ነው። ስቶክ ማርኬት ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል? አቶ ዘመዴነህ ኢትዮጵያ የስቶክ ገበያ ለማቋቋም በዝግጅት ላይ ብትሆነም የስቶክ ገበያ ጽንሰ ሐሳብ ለአገሪቱ ገበያ አዲስ አይደለም ይላሉ።

በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ጥምረት የሚቋቋመው የስቶክ ገበያ በዋናነት የሚከተሉትን ጥቅሞች ለኢትዮጵያ ይዞ እንደሚመጣ ይገልጻሉ። የካፒታል ገበያው የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ (ኢኤስኤክስ) እውን ሲሆን፤ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች ሲቋቋሙም ሆነ ማስፋፋት ሲፈልጉ አክሲዮኖቻቸውን ለመሸጥ ይከተሉት የነበረውን ረዥም መንገድ እንደሚያሳጥርላቸው ያክላሉ።

“እነዚህ ኩባንያዎች ሲቋቋሙ ስቶክ ኤክስቼንጅ ስላልነበረ በጣም ረዥም ሂደት በማለፍ ለእያንዳንዱ ሰው እየዞሩ ነው ሼር የሚሸጡት። ይህ ረዥም ጊዜ እና ገንዘብ ይወስዳል። አዋጭም አይደለም” ይላሉ ዘመዴነህ።

የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ መመሥረት አንዱ ጥቅም አዲስ ለሚመሠረቱም ሆነ ለነባር ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን መፍጠሩ ነው ይላሉ።  ካፒታል ማሰባሰብ ለሚፈልጉም ስቶክ ገበያ መልካም አማራጭ እንደሆነ አቶ ዘመዴነህ ያስረዳሉ።

“ጥሩ ሐሳብ ኖሯቸው የካፒታል እጥረት ላለባቸው ሰዎች ይጠቅማል። ዛሬ ላይ ከባንክ ብድር ማግኘትም ቀላል አይለደም። ለዘመድ ወይም ለጓደኛ ሼር የመሸጥ ሂደት ቀላል አይደለም። ስቶክ ማርኬት አዲስ ለሆኑም ይሁን መስፋፋት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን ይፈጥራል።”

ሌላው የስቶክ ገበያ ጥቅም፣ ፍትሐዊ እና ተመጣጣኝ በሆነ ሁኔታ ሀብት ማከፋፈል የሚችል ሥርዓት እንደሆነ አቶ ዘመዴነህ ይገልጻሉ። በአሁኑ ጊዜ ግዙፍ መንግሥታዊ ኩባንያዎች ወደ ግሉ ዘርፍ እየተሸጋገሩ እንደሆነ በማስታወስ፣ እነዚህ ከመንግሥት ወደ ግሉ የሚዘዋወሩት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሲገዙ የቆዩት ጥቂት ግለሰቦች እና ኮርፖሬሽኖች መሆኑን ይጠቅሳሉ።

ኢኤስኤክስ ሲመጣ ግን መንግሥት የሕዝብን ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማከፋፈል ይችላል። “ስቶክ ማርኬት ላይ አንድ ሼር በአምስትም፣ በአሥርም ዶላር ሲሸጥ ሁሉም የየአቅሙን በመግዛት ኢትዮጵያ ያካበተችውን ሀብት ማከፋፈል ይቻላል” ሲሉ ያብራራሉ። እነዚህ ወደ ግሉ ዘርፍ የሚዘዋወሩ ኩባንያዎች ወደ ስቶክ ገበያው ሲገቡ፣ ሁሉም የአቅሙን ያህል ባለቤት እንደሚሆንና ይህም የሀብት ክፍፍልን እንደሚያመጣ ያክላሉ።

የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ እውን ሲሆን የቁጠባ ባህልን ከፍ እንደሚያደርግ አቶ ዘመዴነህ ይናገራሉ። ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ኪሳራ አያስከትልም ብለው በሚያስቡት ዘርፍ ላይ ብቻ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ይገኛሉ። “ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የቤት ልማት ላይ ብቻ ትኩረት ሲያደርጉ ይታያል። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ደግሞ ተጎድቷል። ይህም ኢንቨስት የሚደረግባቸው ዘርፎችን ውስን በማድረግ የቁጠባ አለመመጣጠን ይፈጥራል። ስቶክ ማርኬቱ ግን ውጤታማ በሆነ መንገድ ካፒታል በሁሉም ዘርፎች ላይ ማሰራጨት ያስችላል” በማለት ያስረዳሉ።

ሌላኛው መልካም አጋጣሚ የድርሻ ገበያዎችን በቀላሉ፣ ግልጸኝነት በሰፈነበት መልኩ መግዛት እና መሸጥ ማስቻሉ ነው። ምን ያህል ሼር በምን ያህል ዋጋ ለገበያ እንደቀረበ ግልጽ ነው።  “ሰዎች ስልካቸው ላይ በሚጭኑት መተግበሪያ በቀላሉ የገበያ ድርሻዎችን መግዛት እና የገዙትንም መሸጥ ይችላሉ” ይላሉ አቶ ዘመዴነህ። የባንክ ባለ አክሲዮኖች ዓመት ጠብቀው ትርፍ ከመከፋፈል ውጪ በቀላሉ ያላቸውን አክሲዮን መሸጥ አይቻላቸውም። ኢኤስኤክስ እውን ሲሆን ግን በቀላሉ አክሲዮን የመሸጥ ዕድል ይዘረጋል።

የካፒታል ገበያ ስርአት የባንኮች የማበደር አቅምን ስለሚጨምር የንግድ እንቅስቃሴን እና ኢንቨስትመንትን የመጨመር ጥቅም አለው ሲሉ  የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ተክለማርያም ይገልፃሉ ፡፡ የካፒታል ገበያ የካፒታል እጥረት ያለባቸው ድርጅቶች የኢንቨስትመንት የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስባስቡ እና አዲስ ኩባንያ ለማቋቋም እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡  የካፒታል እጥረት ያለበት ኩባንያ ሸሩን ካፒታል ወደሚያገበያዩ ድርጅቶች በመሄድ በመሸጥ የማስፋፋት ስራ መስራት ያስችላቸዋል ይላሉ ፡፡

በካፒታል ገበያ ስርአት፣ ለኢንቨስትንት ማስኬጃ የካፒታል እጥረት ስለማይኖር ኢንቨስትመንት እንዲጨምር ያስችላል ያሉት አቶ ጌታቸው የካፒታል እጥረት ይኖራል የሚል ስጋት ስለማይኖር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት(ኤፍዲአይ) እንዲጨምር እና የአክሲዮን ገበያ ሲመሰረት ድርጅቶች ስለሚበዙ የስራ እድል ፈጠራ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡

አማካሪው እንዳሉት ካፒታል ገበያ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲጨምርም ያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን  ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) የህግ ማዕቀፍ እና መመሪያ መጨረሳቸውን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፥ 15 አሻሻጮች ፍቃድ የሚያገኙበት አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ገበያ ላይ ሊገዙ እና ሊሸጡ የሚችሉ ኩባንያዎች ዝርዝር ወጥቶ የማብቃት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም አምስት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተለይተዋል ነው ያሉት። በተጨማሪም ሰባት አዳዲስ መመሪያዎች መውጣታቸውንም ገልጸዋል።

ካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016’’  ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ስራ ላይ መዋሉን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ  አስታውቋል። የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ የሚሰጥበትን መመሪያ  ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቋል። ‹‹ይህ መመሪያ በሃገራችን የካፒታል ገበያን ለማስጀመር ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን ገበያው ተዓማኒ እና ፍትሐዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚረዳ እና የኢንቨስተሮችን ጥበቃ የሚያጎለብት የሕግ ማዕቀፍ ይሆናል›› ሲሉ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ገልጸዋል።

Next Post
  • News

The Ethiopian Media Council released press due to the current situation in Ethiopia regarding the issues about online media houses.

Ayele Addis July 23, 2023

Related Post

  • AFRICA
  • Africa News Journal of Research
  • Education
  • Latest
  • Radio & TV
  • Special Edition
  • TOP STORIES

RUSSIAN WORLD MEET AFRICAN WORLD: HOW CULTURE, LANGUAGE AND EDUCATION ARE BUILDING A HUMAN BRIDGE

Ayele Addis April 5, 2026October 3, 2026

From Pushkin poetry in Addis Ababa to African celebrating Russian traditions in Moscow, a cultural relationship is being rebuilt one conversation, song and friendship at a time By MESERET ABEBE ABAY,  EMMA NEWS  (publicmediaet@gmail.com) 05 April , 2026 A Russian poem is read in Addis Ababa. The voice is Ethiopian. The language is Russian. Nearby, […]

  • Radio & TV

EPISODE ONE: POWER AND PEOPLE: WHEN A MOTHER’S JOURNEY TO SURVIVE TAKES HOURS

Ayele Addis May 6, 2026June 6, 2026

GENDER, MEDIA AND SOCIAL JUSTICE IN ETHIOPIA EPISODE ONE WHEN A MOTHER’S JOURNEY TO SURVIVE TAKES HOURS THE HIDDEN HEALTHCARE CRISIS FACING RURAL WOMEN Millions of women across Africa continue to face barriers to healthcare, emergency services, and lifesaving support. What lessons can Ethiopia learn? Featuring: • Maternal Health Experts• Women’s Rights Advocates• Community Voices• […]

  • News

ስለ ፋና

Ayele Addis January 13, 2024January 13, 2024

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ ተቋማችን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በ1987 ዓመተ ምህረት ሲቋቋም በኃላ ቀር መሳሪያዎችና በጥቂት የሰው ሃይል በሀገራችን የብሮድካስት ሚዲያ አዲስ አቀራረብ ይዞ ወደ ስራ ገባ። በሂደትም አደረጃጀቱንና የፕሮግራም ይዘቱን እያሻሻለና ችግሮቹን እየቀረፈ ገስጋሴዉን ቀጠለ። ህብረተሰብ ተኮር ፕሮግራሞች ላይ በማጠንጠን የሚታወቀውና ለህዝባችን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ኑሮ መሻሻልና መዳበር የሚተጋው የሚዲያ ተቋማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ […]

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • ዜና
  • ልዩ ዕትም
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress