Skip to content
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action

EMMA NEWS: Ethiopian Mass Media Action

November 21, 2026
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check

Most Viewed This Week

November 19, 2026November 19, 2026

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

1
November 14, 2026November 14, 2026

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

2
November 2, 2026November 6, 2026

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

3
September 8, 2026September 8, 2026

18 ክስተቶች በኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም መስቀለኛ መንገድ!

4
September 7, 2026September 7, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

5
August 31, 2026August 31, 2026

ሸውከኛ ካፒታል (Corrosive Capital) የኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨሰትመንት ፈተና እና የሕዝብ የፋይናንስ ዕዳ ሸክም የሆነው እንዴት ነው?

6

Search Field

Subscribe Now


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • News

1ኛውን የምስራቅ አፍሪካ አግሮኮሎጂ ኮንፈረንስ በኬንያ ናይሮቢ በመካሄድ ላይ ነው ።

ንጉስ ኢስዋቲኒ የዚምባብዌን ልማት ፕሮጀክቶችን አድንቁ።

  • News

ከሳንሱር መቸ ነው የምንወጣው? Free Media Censorship in Ethiopia by Ayele Addis

Ayele Addis May 3, 2023May 3, 2023

ነፃ አሰተሳሰብን የምንገነባው እና የእኔ ብቻ ነው እውነት ከሚል አሉታዊ ሃይል የምንወጣው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ከመንግስታዊ ሳንሱር ነፃ ሲሆኑ እና የርስ በርስ ቁጥጥር ሲያጠናክሩ ብቻ ነው፡፡ የኢንተርኔት አፈናው – #የቴክኖሎጅ_ሳንሱር፣ የመንግስት መረጃን የማስራብ ፈተና ፤- #የይዘት_ሳንሱር፣ በዚህ መረጃን በመበከል (disinformation) ፣ መረጃን በማሳሳት (misinformation )፣ መረጃን በማዛባት (Mal-information)፣ በሃሰት መረጃ (fake news) በበዛበት ጊዜ ይህንን የሚታገል የመረጃ ስርዓት ለመገንባት አለመታደላችንን እንዴት መፍትሄ እንስጠው???  

ኢትዮጲያ በሳንሱር ውስጥ፡- 

የመገናኛ ብዙሐን ቁጥጥር ስራ ከመነሻው ለዚሁ ተግባር ተብሎ እንደዛሬው ለብቻው በተቋቋመ ድርጅት ውስጥ የሚካሄድ አልነበረም፡፡ በሌሎቹ ድርጅቶች ውስጥ ከሌላ የስራ ዘርፍ ጋር እየተያያዘ ሲሰራ እንደነበር የማስታወቂያ ሚኒስቴር መሰረት ታሪክ ያስረዳል፡፡

 በመጀመሪያ ጊዜ የሳንሱር ስራ ይከናወን የነበረው በ1934 ዓም በተቋቋመው በጽህፈት ሚኒስቴር ወስጥ ነበር፡፡ የፕሬስና የማስታወቂያ ክፍል ሀላፊነት ማስታወቂያና ኢንፎርሜሽን ስራ ማከናወንና የመንግስት ማተሚያ ቤቶችና  ጋዜጦችን መቆጣጠር ነበር፡፡ በጋዜጦች ቁጥጥር ስራ ውስጥ የሳንሱር ተግባር ይከናወን ነበር፡፡ ይህ በጽህፈት ሚኒስቴር ስር ይከናወን ነበረው የሳንሱር ስራ በ1935 በአዋጅ ታወቀ፡፡ አዋጁ ቲያትርና የሲኒማ አደራረግ ስለመምርመር የወጣ አዋጅ ቁጥር 37/1935 ዓ.ም ተብሎ ይታወቃል፡፡

ከ23 ዓመት በኋላ የማስታወቂያና ቱሪዝም ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባር የወሰነው፡፡ ትዕዛዝ ቁጥር 46/1957 ዓ.ም የሳንሱር ስራ በዚህ ሚኒስቴር ውስጥ ይካሄድ እንደነበር ይገለጻል፡፡ ይህ አዋጅ ሰተውን ስልጣን መሰረት በማድረግ የማስታወቂያና ቱሪዝም ሚኒስቴር የምርመራ ቦርድ በሚል ስያሜ አንድ የራሱን ቻለ የሳንሱር ክፍል አቋቋመ፡፡

የምርመራ ቦርዱ 4 ክፍሎች የነበሩት ሲሆን፡- እነሱም፡-

  1. የሀገር ውስጥ እትሞች ምርመራ ክፍል
  2. የውጭ ሀገር እትሞች ምርመራ ክፍል
  3. የፊልም   ምርመራ ክፍል
  4. የቲያትር  ምርመራ ክፍል ነበሩ፡፡

በማስታወቂያ ቱሪዝም ሰብሳቢነት የትምህርት ፣የሀገር ግዛት፣ ህዝባዊ ኑሮ እድገት ሚኒስቴሮች፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትና ፖሊስ ሰራዊት ተወካዮች ምርመራ ቦርድ አባል ሆነው እንዲሰሩ ተደረገ፡፡

ከሰኔ 20/19/64 ጀምሮ ደግሞ የምርራ ቦርድ የሚው ስያሜ ቀርቶ .. የምርመራ ዋና መምሪያ.. ተብሎ እንዲሰራ ተወሰነ፡፡

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከ5 ድርጅቶች ከተውጣጡ የቦርድ አባላት ይካሄድ የነበረው የምርመራ ስራ በምርምር ዋና መምሪያ መደበኛ ሰራተኞች ብቻ እንዲከናወን ተደረገ፡፡ በዚህ አኳኋን እስከ 1966ቱ የኢትዮጵያ አቢዮትፍንዳታ ድረስ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ከ1934 ጀምሮ እስከ 1966 ድረስ የሳንሱር ድርጅታዊ መዋቅር ደረጃ በደረጃ እየተጠናከረ እተስፋፋ መጥቷል፡፡ ከዚህ የመዋቅር ጥንካሬና መስፋፋት ጋር አንጻራዊ የሆነ ፖሊሲና የአሰራር እድገትም ታይቷል፡፡

በ1934 በጽህፈት ሚኒስቴር ስር የነበረው የፕሬስና የማስታወቂያ ክፍል ጋዜጦችን ይቆጣጠር እንደነበር ቢገለጽም የሳንሱሩ መምሪያ ፖሊሲ ምን እንደነበር አያታወቅም፡፡ ነገር ግን ከ 1 ዓመት በኋላ በ1935 የወጣው አዋጅ ቁጥር 37/1935 በቀጥታ ሳንሱርን የሚመለከት የመጀመሪያ አዋጅ ነበር፡፡ ከወጣበት ጊዜ አንጻር ሲገመገም በቂና ጥሩ እንደነበር መገመት ይቻላል፡፡ ምን ያህል ብቃትና ስፋት እንዲኖረው የተደረገበት ምክንያት ደግሞ የነበረው ስርዓት የህዝቡን ስሜት ለመቆጣጠር የነበረውን ፍላጎትና ያደረገውን ጥረት ያመለክታል፡፡ በእርግጥ የቁጥጥሩ ዓላማ ስርዓተ ነጸብራቅ ነበርና ለህዝቡ ሳይሆን በህዝቡ ላይ የሚደረግ ነበር፡፡

አዋጁ 10 ነጥቦች ይዟል፡፡ ሳይመረመሩ ለህዝብ መቅረብ የሌላቸውን ነገሮች በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ያልተመረመሩ ነገሮችን ለህዝብ  ማቅረብ የተከለከለ ስለመሆኑና ሊያስከትል የሚችውንም፣ ቅጣት ወስኗል፡፡ ባጭሩ ለምን እንደሚደረግ መግለጽ ይሞክራል፡፡ እነዚህን ነጥቦች አዋጁ እንዴት እንደገለጻቸው መመልከት አስፈላጊ ነው፡፡

  • .. በዚህ አዋጅ የጸና ህግ ከሆነበት ጊዜ በኋላ 15 ቀን ቆይቶ ማናቸውንም ፊልም ቲያትርና ..ቪዲዮ.. ይህም መሰለ ልዩ ልዩ ጨዋታ መርማሪ ሳይመረምራቸው በህዝብ እንዲታዩ ማቅረብ ኤቻልም፡፡ /4ኛ ቁጥር/
  • ማንኛውም ፊልም፣ ቲያትር ሪቪዮና ልዩ ልዩ ጨዋታ አስቀድሞ ለጨዋታ መርማሪው ሳይቀርብ ወይም ለጨዋታ መርማሪው እንደቀረበለት ዓይነት ሳይሆን ለህዝብ ሲታይ ይህንኑ የሰሩና ያስተባበሩ በአሰራርም ተከፋይ የሆነ ሁሉ በደለኞች ይሆናሉ፡፡ /9ኛ ቁጥር/
  • ይህንን አዋጅ የተላለፈ ለዚህም የተመሰከረለት ሰው ከ500 ብር በማይበልጥ መዋጫ ወይም ከ6 ወር በማይበልጥ እስራት ወይም በሁለቱም በገንዘብ መቀመጫ በእስራት ይቀጣሉ፡፡ /10ኛ ቁጥር/
  • በጨዋታ መርማሪው ፊልሙን፣ ተያትሩን ቪዲዮውንና ይህንኑ የመሰለውን ልዩ ልዩ ጨዋታ ህዝብ ና የህዝብን ጸጥታና ንጽህና የሚያበላሽና ብልግና ያለበት መሆኑን መሰረት አድርጎ ነው፡፡ /7ኛ ቁጥር/

የጽህፈት ሚኒሰቴር በንጉሰ ነገስቱ ውስጥ አስፈላጊ ሆኖ በሚታየው ከተማ ሁሉ ጨዋታ መርማሪ መሾም እንደሚችል በአዋጅ ተደንግጓል፡፡ በአዋጁ መሰረት በእያንዳንዱ ፊልም ፣ ቲያትር ሪቪውና ስለ ሌሎችም ምርመራ በሚደረግላቸው ጉዳዮች 5 ብር ይከፈል ነበር፡፡

በ1958 … የማስታወቂያና ቱሪዝም ሚኒስቴርን.. ስልጣንና ተግባር የወሰነው ትዕዛዝ ቁጥር 46/1958 በኢትዮጵያ ውስጥ ለህዝብ የሚታዩ ትርኢቶችን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የሚገቡና በኢትዮጵያም ውስጥ የሚታተሙ ጽሁፎች ይዘት ምን መምሰልና ከምን ነገሮች ነጻ መሆን እንዳለባቸው 23 ዓመት ስፋት ከወጣው አዋጅ ቁጥር 27 /1935 በጣም ሰፋ ባለ ሁኔታ ገልጾታል፡፡

  • .. በኢትዮጵያ ውስጥ ለህዝብ የሚታዩ ፊልሞች ፣ቲያትሮች፣ ሌሎችም ህዝብ መደሰቻ ትርኢቶች ሁሉ የህዝብን ግብረ ገብነት የማያበላሹ ወይም የንጉሰ ነገስቱን ጸጥታ የማያናጉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የሚገቡት የታተሙ ጽሁፎች እና በኢትዮጵያም ውስጥ የሚታተሙ ሁሉ የህብረተሰቡን ግብረ ገብነትን የማያበላሹ ወይም የህዝቡን ጸጥታ የማይጎዱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ኃላፊ ነው፡፡

በወጡት አዋጆችና ትዕዛዞች ላይ ተመስርቶ በውስጥና በውጭ ፖለቲካ እንዲሁም በሞራል ረገድ ሳንሱር ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ነጥቦች በዝርዝር መመሪያ ቀርበዋል፡፡ እነዚህ መመሪያዎች ያንን ስርዓት ያሳስቡትና ያሳደጉት የነበሩት ጉዳዮችን በግልጽ ያሳያሉ፡፡ የውስጥ የፖለቲካን አስመልክቶ ከተከለከሉት ነገሮች ውስት ጥቂቶችን ብቻ እንመለልከት፣

  • የንጉሰ ነገስቱን መሰረታዊ አቋም የሚነቅፍ
  • የንጉሰ ነገስቱን፣ የንጉሳውያን ቤተሰቦችንና የሚኒስቴሮችን ክብር የሚነካ
  • ስለ ስራ ፈት፣ ስለ ሴተኛ አዳሪና ስለ ለማኞች ብዛት፡፡
  • ስለ አሰሪና ሰራተኛ ግጭት፣ ስለ ተማሪ ሁከት
  • ስለ ኑሮ ውድነት፣ ስለ አድማ፣ ስለ መሬት ስሪት
  • ስለ ወታደር ደመወዝ፣ ስለ ኢትዮጵያ የኑሮ ደረጃ
  • ስለ ህብረተሰባዊነት /ስለ ሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም/ የሚያብራሩ ጽሁፎች፣ ፊልሞች፣ ቲያትሮች… ወዘተ ትርኢት የተከለከለ ነው፡፡

እነዚህ ከላይ የተተቀሱትን መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ በተግባር የሚተረጎሙ ነበሩ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ አዋጅና መምሪያ ወጥቶላቸው በተግባር የማይተረጎሙ ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ህዝብን ሞራል በሚመለከት የሚወጡ አዋጆች መመሪያዎችን ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ለህዝብ የሚታዩ ፊልሞች፣ ቲያትሮች… ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የታተሙ ጽሁፎችና  በኢትዮጵያም ውስጥ የሚታተሙ ሁሉ የህዝቡን ግብረ ገብነት የማያበላሹ መሆናቸው መረጋገጥ እንዳለበት በአዋጅ በግልጽ ተቀምጧል፡፡

ይሁን እንጂ ይህን የመሳሰሉት አዋጆች ሆኑ መምሪያዎች በጽሁፍ ይኑሩ እንጂ በተግባር የተተረጎሙ አልነበሩም፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታዩት ፊልሞችና ከውጭ የሚገቡት እትሞች ስለ ሽርሙጥና፣ ስለ ሌብነት፣ ስለ ስካርና፣ ሌሎችም ህዝብ ሞራል ስለሚያላሽቁ ነገሮች በሰፊው የሚያቀርቡ እንደነበሩ በቂ ማስረጃዎች ይገኛሉ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት እነዚህ ነገሮች ጎጂ መሆናቸው አልታወቀም ብሎ ወይም መከልከሉ ስለ ነገሮች ሳይሆን፣ የነበረው ስርዓት ህዝቡን ሞራል መበላሸት ይፈልግ ስለነበር ነው፡፡

በአድሀሪው ስርዓት ውስጥ አዋጅና መምሪያ በተግባር ለመተግበር የሚያስችሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያሻስል ከምርመራ ታሪክ መረዳት ይቻላል፡፡

በ1934 በጽህፈት ሚኒስቴር ስር በአንድ ክፍል ውስጥ ከሌሎች ስራዎች ጋር ተደርቦ ይሰራ የነበረው ሳንሱር ስር በ1958 በቦርድ ፣ በ1964 በዋና መምሪያ ደረጃ በተዋቀረ ድርጅት ራሱን ችሎ እንዲካሄደ ተደርጓል፡፡

በአመራርም ሆነ በሌላ ደረጃ በሳንሱር ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ሰራተኞች በጥንቃቄ ይመረጡ እንደነበር ይነገራል በየጊዜው በሳንሱር ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ሹሞች ታማኝነታቸው ከስርዓቱ ብቻ ሳሆን በግልም በስርዓቱ ቁንጮ ላይ በሚገኙት ባለስልጣኖችም የታወቀ መሆን እንደነበረባቸው በጊዜው የታሰሩ ሰዎች ያናገራሉ፡፡

ሳንሱር በቦርድ መስራቱ ከቀረ በኋላ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለሚኒስቴሩ ሆኖ በመረዳት ሚኒስቴር ይመራ ነበር፡፡ ይህም ሆኖ የሳንሱር ስር ንጉሱንና በንጉሱ አካባቢ የነበሩትን ባከስልጣኖች ይጨምር እንደነበር በጊዜው የነበሩ ሰዎች ያስታውቃሉ፡፡ ይህም የነበረው ስርዓት ህዝቡን በድንቁርና ለመግዛት ምን ያህል ይጥር እንደነበር ያሳያል፡፡

ሳንሱር በዘመነ ደርግ ከ1964-68 ድረስ በምርምር ዋና መምሪያነት ስራውን ያከናውን ነበር፡፡ በ1969 መምሪያ መሆኑ ቀርቶ በአገልግሎት ደረጃ እንዲዋቀርና ተጠሪነቱም ለቋሚ ተጠሪ እንዲሆን ተጠሪነቱም ለቋሚ ተጠሪ እንዲሆን ተደረገ፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አቢዮት ፍንዳታ ጋር አብሮ በተከሰተው የስነ ጥበባት እድገት ምክንያት ምርመራ ስራ ቀድሞ ታቶ ባልታወቀ ሁኔታ ስለሰፋ ቅድመ አቢዮት በ4 ክፍሎች ይሰራ የነበረው ሳንሱር ከ1970 ጀምሮ 2 ዋና ክፍሎች ከፍቶ በ2 ዋና ክፍሎችና በ4 ክፍሎች ተዋቀረ፡፡

በአቢዮቱ በፊት እና በኃላ ሳንሱር ለኢትዮጵያ መሪ የፖለቲካ ስርዓት ያገለግል ነበር፡፡ ይህም  ስርዓት በሳንሱር ፖሊሲ ያገለገለ ከዚያ ስርዓት፣ በመነጨለት ፖሊሲና መምሪያ ነበር፡፡ አቢዮት ፈንድቶ አዲስና ተራማጅ ስርዓት ሲተካና ሳንሱርም በዚህ አዲስ ስርዓት ውስት ለመስራት ሲነሳ የአዲስ ስርዓት ነጸብራቅ የሆነ አዲስ ፖሊሲና መመሪያ ማግኘቱ አስፈላጊና ግድም ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት የምርመራ አገልግሎት አቢዮታቸው ያወጣቸውን ስር ነቀል ፖሊሲዎች ተከትሎ ስራውን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ ዛሬ የሚሰራባቸው ልዩ ልዩ መመሪያዎች ለውጥ ሲመጣ ወዲያው የተገኙ ሳይሆኑ ከኢትዮጵያ አቢዮት ሂደት እድገትና ስፋት ጋር ቀስ በቀስ የተገኙ የዳበሩና የተሸሻሉ ናቸው፡፡

ከአቢዮታችን ፍንዳታ በኋላ በመመሪያዎቹ ጥቂት ወራቶች ውስጥ የዓዲሱ ስርዓት ነጸብራቅ የሆኑ መመሪያዎች ማግኘት ባለመቻሉ የምርመራ አገልግሎት ተግባር አስቸጋሪ ሁኔታ ላየረ ነበር፡፡ ለውጡን ተከትለው ሀገሪቱን ባጥለቀለቋት የሀገር ውስጥና የውጭ ከተሞች፣ ፊልሞች፣ ስዕሎች፣ ፓስፖተሮችና ሙዚቃዎች ላይ ሐገሪቱ ከምትከተለው ስርዓት አንጻር ውሳኔዎችን ለመስጠት ከባድ ችግር ነበር፡፡ ችግሩን ያከበደው የመመሪያዎች ለመኖር ብቻ ሳይሆን ሰራተኞች ለአዲሱ ስርዓትና ሳይንስ አዲሶች በመሆናቸው ጭምር ነበር፡፡

አቢዮታዊ ኢትዮጵያ መምሪያ ሶሻሊዝም መሆኑን ይፋ ሆኖ የታወቀው ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አቢዮት መለስተኛ ፕሮግራም በተግባር ላይ ከዋለ በኋላ ምርመራ አገልግሎት በመመሪያ በኩል የነበረበት ችግር ይፋ ባደረጋቸው ፖሊሲ ላይ ተመስርቶ ክፍሉ ላይ ልዩ መመሪያዎች በበላይ አካል እያስደነቀ ስራውን ያለ ብዙ ችግር ማከናወን ችሏል፡፡

በ1973 የማስታወቂያና መርሃ ብሄር ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ፖሊሲ መምሪያ ተዘጋጅቶ ከጸደቀና በተግባር ላይ ከዋለ ጀምሮ ምርመራ አገልግሎት ስራውን ለመፈጸም ጊዜ በተሸለ ሁኔታ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የፖሊሲ መምሪያ ውስጥ የምርመራ አገልግሎት ከኢትዮጵያ አቢዮት ፍንዳታ ወዲህ እንደየሁኔታው በየጊዜው የተከተላቸው ፖሊሲ መመሪያዎች በአንድ ላይ ተጠቃለው ይኖራሉ፡፡

በዘመነ ደርግ የወታደራዊ አገዛዝ የምርመራ አገልግሎት መምሪያ ከዚህ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይይዛል፡፡

  1. የምርመራ አገልግሎት በአዋጅ ለሚኒስቴሩ ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት ከኢሰፓአኮ በሚተላለፍለት መመሪያ፣ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ አቢዮት ፕሮግራም አቢዮቱ ከደረሰበት ደረጃና ከጊዜው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በማስታወቂያና መገናኛ ብዙሐን ሚኒሰቴር ስር ከሚተዳደሩ የኢንፎርሜሽን አገልግሎቶች በስተቀር፣

ሀ. በጋዜጦች፣ በመጽሄት በመጻህፍት፣ በበራሪ እትሞች በትያትርና በፊልሞች፣ በምልክቶች፣ በንድፎች፣ በቅርጾች፣ በፎቶ ግራፍና ስዕሎች የሚገለጹት ሀሳቦች፣ አስተያቶችና ሀተታዎች የሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያ መሰረታዊ መመሪያ የመንግስቱን አቋም የማይቃወም እንዲሁም የህዝቡን ሞራልና መልካም ባህል የማያበላሹ መሆናቸውን እያረጋገጠ እንዲሰራጩ ይፈቅዳል፡፡

ለ. በኢትዮጵያና በውጭ ታትመው የሚገቡት በጋዜጦች፣ በመጽሄት በመጻህፍት፣ በበራሪ እትሞች በትያትርና በፊልሞች፣ በምልክቶች፣ በንድፎች፣ በቅርጾች፣ በፎቶ ግራፍና ስዕሎች ወዘተ የሰውን መሰረተ እኩልነት የሚያከብሩ፣ የብሄረሰቦችን እኩልነት የሚጠብቁ ፣ በሀይማኖት፣ በጾታና በመሳሰሉት ባህሪያት የመብት ልዩነት የማይፈጥሩ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡

  • በውጭ ሀገር በፊልሞች፣ በቲያትሮች፣ በንድፎች በቅርጾች፣ በስዕሎች፣ በምልክቶች፣ በጋዜጦች፣ በመጽሄቶች፣ በመጽሀፍት፣ በበራሪ እትሞችና በመሳሰሉት፣ ስለ ኢትዮጵያ ትክክለኛና እውነተኛ ያልሆኑ ዜናዎች፣ ሁኔታዎችና መግለጫዎች ታትመው ሲወጡ እንዳይሰራጩ አግዶ ለበላይ ያስታውቃል፡፡
  • ማናቸውም የጽሁፍ፣ የስዕል ፣ የቅርጻቅርጽ፣ የፊልም፣ የቲያትርና የመሳሰሉት ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ቢያንስ 3 አባሎች በሚገኙበት ኮሚቴ በከፍተኛ ጥንቃቄ ተመርምሮ በአንድ ድምጽ ወይም በድምጽ ብልጫ አስተያየታቸውን ካቀረቡ በኋላ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡
  • ቲያትርና መ፣ድረክ ነክ ዝግጅት በመጀሪያ ጽሁፉ በንባብ ከተመረመረ በኋላ ከነ ሙሉ ዝግጅቱ በመድረክ ላይ ተመርምሮ ይፈቀዳል፡፡
  • ‹‹የምርመራ አገልግሎት ጽሁፍ፣ ስዕል፣ ቅርጻቅርጾችን ወይም ፊልምን አስመልክቶ አስተያየትና ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ ፈጽሞ የሚከለከሉትን ወይም ታርመው ለህዝብ የሚቀርቡትን እንደዚሁም የእድሜ ክልል ገደብ የሚደረግባቸውን የሚያስገነዝብ የመመዘኛ ነጥቦች ይኖረዋል፡፡

የምርመራ አገልግሎት ስራ የርዕዮተ ዓለም ቁጥጥር ስራ ነው፡፡ ከመንግስታዊ ስርዓት በድንገት  ወደ አዲሱ እና ተራማጁ ስርዓት ተሻግሮ ስር ነቀልነትና በፍጥነት በሚጓዘው አቢዮታዊ ስርዓት የሚመራ የኮሙኒኬሽን ፖሊሲ እና ህግ ነበር፡፡

ሰራተኞቹ የማሌ ሳይንስ ብልጭታ ከማየታቸው በፊት በቀድሞው ስርዓት ይወገዙ የነበሩ የውጭ እትሞች፣ ፊልሞች ሙዚቃዎች፣ ስዕሎች ወዘተ ከለውጡ ጋር ሀገሪቱን አጥለቅልቋታል፡፡ እነዚህን ልዩ ልዩ ስራዎች አንብቦ፣ተመልክቶና አዳምጦ ውሳኔ ለመስጠት በዛ ወቅት ሰራተኛ ሊኖራቸው ያልቻለው የማሌ ሳይንስ እጅግ አስፈላጊ ነበር፡፡

ለአያሌ ዘመናት ሀሳብ የመግለጽ መብታቸውን ተገፈው የኖሩት ድርጅቶች፣ግለሰቦች፣ ቲያትሮች፣ ሙዚቃዎች፣ ስዕሎች እንደ እንጉዳይ አፈሏቸው፡፡ በዛ ወቅት የምርመራውን ስራ በሚገባ ለማከናወን የማሌ ሳይንስ ብቻ ሳይሆን ወቅታዊ ሁኔታወችንም ማወቅ ያስፈልግ ነበር፡፡ ከኢትዮጵያ አቢዮት ጥቅም አንጻር የእያንዳንዱን የፖለቲካ ቡድን አቋም ማወቅና በተተሰለፈው ትግል ውስጥ የዕለቱን ተጨባጭ ሁኔታና እንቅስቃሴ ማወቁ አስፈላጊነት ነበር፡፡

ይሁን እነጂ የአገልግሎት ሰራተኞች በየግላቸው ከሚያውቁት ኢንፎርሜሽን ውጪ የፖለቲካ ቡድኖችን አቋምና የየወቅቱን ተጨባጭ ሁኔታ ከየጥንስሱ የሚጠቁም ኢንፎርሜሽን ማግኘት አይቻልም ስለነበር የተለያዩ ፖለቲካ ቡድኖችን አቋም የሚያንጸባርቁትን እትሞችና ሌሎች ስራዎች ያለ ችግር መገምገም አይቻልም ነበር፡፡

ይህን በመሰለው አስጨናቂ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የምርመራ አገልግሎት ደረጃ ያለውና የስራ የትግል አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

የምርመራ አገልግሎት የስራ ጠባዩ ስለሆነ በውስጡ የተሰለፉት ሰራተኞች ስለ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም ፍልስፍናና ስለ ወቅታዊ ሁኔታዎች የማወቅ ግዴታ ነበረባቸው፡፡ በዚህም ምክንያት በተለይ ከሰራተኞቹ ውስጥ የአቢዮታችን ሙሉ ደጋፊዎች የሆኑት ጥረታቸውን ከፍ አድርገው ሳይንሱን በማጥናትና የወቅቱን ተጨባጭ ሁኔታዎች በጥንቃቄ በመርመር ጠቃሚ የሆኑ የስራና የትግል አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

የመደብ ትግል ነውና በአንጻሩም በአቢዮቱ ያልተደሰቱ ጥቂት ሰራተኞች ነበሩ፡፡ ግን ብዙ ችግር ከመፍጠራቸው በፊት በሰራተኛው ትክክለኛ ትግል በየጊዜው ተወግደዋል፡፡

የአገልግሎቱን የስራና የትግል አስተዋጽኦ በ2 ከፍሎ መመልከት ይቻላል፡፡ በመጀመሪያ የኢትዮጵያን አቢዮት ለመቀልበስ የተነሱ ጸረ አቢዮት ቡድኖች ሊያራምዱ ከሞከሩት የሀሳብ ስርጭት ጋር የተደረገው ትልም ነበር፡፡

ከኢትዮጵያ አቢዮት ፍንዳታ በኋላ ብዛት ያላቸው መጽሄቶች፣ ጋዜጦችና ልዩ እትሞች ይታተሙ ነበር፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ ‹‹ጎህ›› የተባለው መጽሄት የቀንደኛው የኢትዮጵያ አቢዮት ተፎካካሪ ኢህአፓ  ፓርቲ ልሳን ነበር፡፡ ይህ መጽሄት በህጋዊ መድረክ በኩል አልፎ ይታተም ስለነበር የምርመራ አገልግሎት እየቀረበ መፈቀድ ነበረበት፡፡ የሰራተኞቹ የንቃት ደረጃ በፈቀደለት መሰረት ምርመራ አገልግሎት በመጀመሪያ ደረጃ በየጊዜው የመጽሄቱ አዘጋጆች ያቀረቧቸውን ጸረ ሳይንስ ጽሁፎች እንዳይታተሙ በማድረግ በጸና አቋም ታግሏል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ጽሁፎቻቸው እየታገዱባቸው  ስለተቸገሩ አዘጋጆቹ በረቀቀ መንገድ በልባስ ስዕሎች አማካኝነት ያንኑ ጸረ አቢዮት መልዕክታቸውን ማስተላለፍ ሲጀምሩ ከተወሰኑ ሙከራዎች በኋላ መጽሄት ያለ ሽፋን ስዕል እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም አገልግሎቱ ባደረገው ትግልና አቢዮታው መንግስት በወሰደው ቆራጥ እርምጃ መሰረት ጎህ መጽሄት መስከረም 20 ቀን 1969 ዓ.ም ሊታገድ ችሏል፡፡

በዛን ወቅት ጽሁፎቻቸው በታረሙና በተከለከሉ ቁጥር የመጽሄት አዘጋጆችና ደጋፊወቻቸው 5ና 6 እየሆኑ በትጥቅ በመምጣት ለምን ታረምንና ተከለከልን የሚሉ ጥያቄዎችን ከጉልበትና ከሀይል አንጻር ይሰነዝሩ ነበር፡፡ ይህም በመርማሪዎች ላይ ተጽዕኖ ያደርግ ነበር፡፡ ግለሰብ መርማሪዎች እንዳይጋለጡ ታስቦ የተመረመሩ ጽሁፎችን ና ውሳኔዎችን ከመዝገብ ቤት እንዲረከቡ በተደረገበት ጊዜም ምርመራ አገልግሎት ውስጥ በነበሩት አብዛኞዎች አማካኝነት ማን እንደከለከለ ጥቆማ ይደረግላቸው ስለነበር የአገልግሎቱ ሰራተኞች ከስጋት ሊድኑ አልቻሉም ነበር፡፡

ቀጥሎም በሀይማኖት ጥላ ስር በመካነ እየሱስ ድርጅት ተቆጣጣሪነት ይታተም የነበረው ብርሀን መጽሄት ከጎህ በኋላ ጎህን ተክቶ ሊሰራጭ የሞከረ የገዥው ፓርቲ (‹‹ጸረ አቢዮት››) መጽሄት ነበር፡፡ ይንን መጽሄት በየደረጃው ለመቆጣጠር ተሞክሮ ከጸረ አቢዮቱ ፕሮፖጋንዳው ሊታገስ ባለመቻሉ በመጨረሻ መጋቢት 23 /1973 ከህትመት ታግዷል፡፡

በህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ዋና ማደራጃ ታተም የነበረው ‹‹ሰረገላ›› ወርሃዊ ጋዜጣ ቀስ በቀስ የለየለት የፖለቲካ ተቃውሞ ይመራ የነበረ ‹‹ጸረ አቢዮት›› ተብሎ በተፈረጀ ሚና ይዞ ስለተገኘ የካቲት 1975 እትም በኋላ እንዲቆም ተደርጓል፡፡

በህትመት መልክ ከቀረቡት እነዚህ ለናሙና ያህል ተጠቀሱ እንጂ በጸረ አቢዮት ይዘታቸው የሚታረሙና የሚከለከሉ መጽሀፍቶች ፣ መጽሄቶች፣ ጋዜጦች፣ ቲያትሮች፣ ፊልሞች፣ ስዕሎች፣ ሙዚቃዎች፣ ቁጥር እጅግ ብዙ ነው፡፡

በተለይ የኢትዮጵያ አቢዮት ፍንዳታ ተከትለው ሀገር ወስጥ እንዲገቡና እንዲሰራጩ ጥረት ይደረግላቸው የነበሩት ልዩ ልዩ የምዕራባውያን እትሞች ቢሰራጩ ኖሮ አቢዮቱን ለማቆም ባይችሉም ጉዳት ያደርሱ ይችላሉ የሚል ግምት መንግስት አስቀምጦ ነበር፡፡

የምርመራ አገልግሎት 2ኛው ምዕራፍ የስራና የትግል አስተዋጽኦ፣ አቢዮታዊ ይዘት ያላቸው ግን ስነ ጥበባዊ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ስራዎች እየታረሙና እየተሸሻሉ ለህዝበ እንዲቀርቡ በማድረግ ረገድ የሰጠው ድጋፍ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

‹‹የመደብ ጥቅማቸው የተነካባቸው የኪነ ጥበብ ሰዎች ብዕርና ብሩሻቸውን ለኢትዮጵያ አቢዮት ማንሳት ሲሳናቸው፣ በምትካቸው የኢትዮጵያን አቢዮት የሚደግፉ ብዕሮችና ብሩሾች ፈለቁ፡፡›› ሲል የደርግ ዘመንን የ10 ዓመታት የሚዲያ ጉዞ የገመገመው ሰነድ ተቃውሞን በማገድ ከድጋፍ ወገን ማሰለፍ መቻሉን ይጠቅሳል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ አቋሙና ፍላጎቱ ቢኖራቸውም፣ የርዕዮተ ዓለማዊ ዓመለካከት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ነበሩ፡፡ የምርመራ አገልግሎት አቅሙ በፈቀደ መሰረት እነዚህን ከመደገፍና ከማበረታት አልዘለለም፡፡

ከዚህ በላይ የቀረቡ ማስረጃዎች ለናሙና የቀረቡ እንጂ ሁሉም ሚዲያዎች በሚያቀርቧቸው ዜና፣ ሀተታ፣ ልዩ ዝግጅትና ፕሮግራሞች ሁሉ ህዝባዊና አቢዮታዊ ወገናዊነታቸው በሚገባ አንጸባርቀዋል፡፡ ሁሉም ዝግጅት ለሶሻሊስት ስርዓት ግንባታ በሚል መፈክር ስር በመሰለፍ የማስታወቂያና መርሀ ብሄር ሚኒስቴር ሰፊው ህዝብ ለብሄራዊ አንድነት ለህልውናው በጋራ እንዲሰለፍ አቢዎታዊው መንግስት በየወቅቱ የሚያወጣቸውን አዋጆች መግለጫዎችና መመሪያዎች በሚገባ የሚያስተጋባ እና ለተግባራዊ እንቅስቃሴ ክንዱን እንዲያጠነክር የሚያግዝ መሳሪያ ነበር፡፡

እያንዳንዱ ሚዲያ ከአነስተኛ ዜና አንስቶ ስከ ልዩ ፕሮግራም ድረስ የሚያቀርባቸው ዝግጅቶች ሁሉ መደባዊ ይዘት እንዲኖራቸው በ66 የተጀመረውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንዲያጠናክሩ፣ አዲሲቷን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት አጋዥ ሀይል ሁኖ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡

በዚህም መሰረት የማስታወቂያና መገናኛ ብዙሐን ሚኒስቴር በዚያን ወቅት ከሶሻሊስት ሀገሮች ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር አሰራሩን ፍጹም ሶሻሊስታዊ ለማድረግ አይነተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ ከሶቭየት ህብረት፣ ከጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ከየመን ህዝባዊት ሪፐብሊክ ህብረት፣ ከቬትናም፣ ከኩባ፣ ከችኮዝላቫኪያ፣ ከኮሪያ ህዝባዊ ሪፐብሊክ ፣ ከዩ ጎዝላቪያ፣ ከሀንጋሪና ከሌሎች የሶሻሊስት ሀገሮች ሚዲያ ጋር ስምምነት ውል በመፈራረም የፕሮግራምና የዜና ለውጦችን በማድረግ ላ ነው፡፡ በዚህም ለሰፊው ህዝብ ዜናዎችን ልዩ ልዩ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካ አዘል ፕሮግራሞችን በማቅረብ ስለ ዓለም ህብረተሰብ ተጨባጭ ሁኔታ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው አድርጓል፡፡

የመገናኛ ብዙሐን የርስ በርስ ቁጥጥር በኢትዮጵያ አዲስ ለውጥ

የርስ በርስ ቁጥጥር በአንድ አገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች ሁሉም አካላት ከሕግ በታች መሆናቸውንና በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን የሚያመለክት በጋራ የሙያ መግባባያ ላይ የተመሰረተ የሙያ መመሪያ ጽንሰ ሐሳብ ነው። የመገናኛ ብዙሐን የርስ በርስ ቁጥጥር የሚያረጋግጥ ስርዓት መገንባት ዜጎች በኃይለኞች በተለይ በሚዲያ አካላት እንዳይጠቁ ዋስትና ይሰጣል። በተመሳሳይም የመገናኛ ብዙሐን በውጫዊ እና ውስጣዊ ተፅኖ ፈጣሪዎች ማለትም እንደ መንግስት፣ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች፣ አርታኢዎች የሚዲያ ባለቤቶች  የሚያደርሱትን ተፅኖ እንዳይደርስባቸው ያስችላል፡፡

በሚዲያዎች የርስ በርስ ቁጥጥር ከሌለ፣ የመንግስት ተቆጣጣሪ አካላት የሚጨቁኑበት እና ነፃነትን የሚነፍጉበት፣ የሙያው ገለልተኛነት የሚቀጨጭበት እና አድሎ፣ ኢፍትሃዊነት፣ ሚዛናዊ ያልሆነ አሠራር የነገሠበት ሁኔታ ይፈጠራል። የኃይል ባለቤት የሆነው መንግሥትም፣ ኃይሉ በሕግ የተገደበ እና ስልጣን የሚያጋራበት እድል እንዲፈጠር የሚያደርገው የሚዲያዎች የርስ በርስ ቁጥጥር መኖር ነው፡፡ የመንግሥት ሚዲያን የመቆጣጠር ስልጣን በሕግ ለመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች የርስ በርስ ቁጥጥር ካልተላለፈ ትልቅ አደጋ ነው፤ የሳንሱር እና የመረጃ ገዳቢነት ምንጩም ይኸው ነው። በዚህ መሰሉ ሁነት ውስጥ ደግሞ ሁለንተናዊ የጋዜጠኞችን ነፃነት ማስመዝገብ አደጋች ይሆናል፡፡

በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር1238/2013 አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ 34 ላይ “የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በእርስ ቁጥጥር” ማለት የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በፈቃደኝነት ላይ ተመስርተው የሚገዙበትን፣ የሙያ ሥነ ምግባርና የመልካም አሰራር ደንብ የሚያወጡበት፣ የዘርፉን የሙያ ብቃት የሚያሳድጉበትና የተጠቃሚውን ኅብረተሰብ ቅሬታዎች የሚያስተናግዱበትን አሠራር በመዘርጋት ራሳቸውን ለሕዝቡ ተጠያቂ አድርገው እርስ በእርስ የሚተራረሙበት ሒደት ነው::

የሙያ ነፃነትን በማረጋገጥ ሂደት የሕግ የበላይነትና በሕግ መግዛት ፈጽሞ የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን ማስታወስ ያስፈልጋል። ጥቂት ሰዎች፣ ምናልባት የአገሪቱ መሪ ወይም የመሪው ታማኞች ወይም ደግሞ ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮች ሚዲያውን ሕግ እያወጡ የሚገዙበት፣ እነሱ ግን በሕግ የማይጠየቁበት ስርዓት ሊኖር አይገባም። የመገናኛ ብዙሐን የርስ በርስ ቁጥጥር ውስጥ የሕጉ ዓላማ ሙያውን እና ሙያተኞችን ከኃይለኞች፣ ከጉልበተኞች በተለይ ከመንግሥት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ ህዝቡን በታማኝነት እና በወገንተኛነት ማገልገል ነው።

በሌላ መልኩ የመገናኛ ብዙሐን የርስ በርስ ቁጥጥር የፍትሕ ስርዓት ቀዳሚ በር ነው፡፡ ጥቂት የሚዲያ ተቋማት አጀንዳ ብቻ በኢፍትሃዊነት እንዳይቀርብ እና አሳሳች ዘገባዎች እንዳያቀርቡ በጋራ ሙያውን ባማከለ እና በሙያው ባለቤቶች ይሁንታ በተሰጠው ህግ መመራት ነው። ፍትሐዊነት እንዲሰፍን ሁሉም ጋዜጠኛ ለራሱ የሙያደህንነት ሲል በጋራ ለሙያው መመሪያዎችን ለማክበር የቆመ መሆን አለበት። ለመከበር ብቻ ሳይሆን ለማስከበርም የበኩሉን ማድረግ ይኖርበታል። የመገናኛ ብዙሐን ፍትህን በራስ እጅ ሳይሆን በሙያው ገለለተኛ አካላት ፍትህ  እንዲፈፀም መጣር ይገባል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ከተደረገ በሀገራችን የሚሰተዋሉት ዋልታ ረገድ ፅንፈኝነት፣ ስር የሰደደ የፖለቲካ ጥገኝነት፣ አድሏዊነት እና የሙያ እምነት ማጣት እንዲነግስ መንገድ ይጠርጋል።

የኢ-ፍትሃዊነት ጥግ በደረሰበት፣ ሰሚ መንግስት ባልነበረበት ወቅት ለነጻነት፣ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ ብዙ ዋጋ ተክፍሏል። ብዙሃኑ ዋጋ የከፈሉበት ትግል ውጤት ማስገኘት በጀመረበት ወቅት ከዚያ በተቃራኒ መጓዝ የተከፈለውን ዋጋ ማውረድ ይሆናል። በነጻነት ለመኖር ነጻነትን ማጣጣም፣ ከነጻነት ጋር የሚመጡ ኃላፊነቶችንም ጠንቅቆ መረዳት እና ለዚህም ለመገዛት መትጋት ያሻል።

የርስ በርስ ቁጥጥር ጅማሮ

በወርሃ የካቲት እና ሐምሌ  2013 ዓ.ም የተሻሻለው የኢትዮጵያ መገኛ ብዙሐን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ዓ.ም በፀደቀበት ዕለት እና ማግስት መርሳ ሚዲያ ተቋም የተሰኘው ግበር ሰናይ ድርጅት ከፎዮ አለም አቀፍ የሚዲያ ድጋፍ ጋር በመተባባር (ims-fojo) በኢትዮጵያ ውስጥ የመገናኛ ብዙሐን የርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከባለደርሻ አካላቶች ጋር የምክክር፣ የጥናት ምርምር፣ የፓናል ውይይቶች እያቀረበ የህትመት ውጤቶችን በይፋ አቅርቧል፡፡

በዚህ የሐገሪቱ ሚዲያዎች አዲስ ለውጥ ብለው በመዘገቡት ስነ ስርዓት ላይ መርሳ ሚዲያ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ስማእግዜር እንደተናገሩት ‹‹በአስገዳጅ ህግ ላይ ያልተመሰረተ የመገናኛ ብዙሐን የጋራ ቁጥጥር ስርዓት መዘረጋቱ የሐገሪቱ መገናኛ ብዙሐን ራሱን በራሱ እንዲቆጣጠር እድል ይሰጣል፡፡ የተጋጋለ ብሄርተኝነት፣ የማህበረሰብ ግጭት እና የዜጎች መፈናቀል የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሽግግር በተደጋጋሚ እየፈተነ ያለ ጉዳይ ቢሆንም ሃገሪቱ ለበርካታ የማህበረሰብ አደረጃጀቶች ፈቃጅና አካታች የሆነ ምህዳር በመፍጠር ላለፉት ሶሰት አመታት በዴሞክራሲ ሽግግር በማለፍ ላይ ትገኛለች፡፡››

የቀድሞው የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ ‹‹የመገናኛ ብዙሐን ቅሬታዎች ና የቅሬታ አስተናጋጀፐች አለመመጣጠን ፣ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሐን የርስ በርስ ቁጥጥር ሰርዓት ላይ ያሉ ምልከታዎች›› በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅኁፍ እንዳሰፈሩት ‹‹ቁጥራቸው የማይናቅ የመገናኛ ብዙሐን እንዲሁም ኢቢሲን ጨምሮ ሌሎች የሕዝብ መገናኛ ብዙሐን ምክር ቤት አባል አይደሉም፡፡ የመገናኛ ብዙሐን በሚጠራቸው ስብሰባዎች አባል ብንሆን ምን እንጠቀማለን በሚል የግል ጥቅም እንጅ የእርስበርስ ስርዓት ግንባታን በማምጣት ለህዝብ የሚኖራቸውን ወገንተኛነት የሚደራጀበት እድል አላዩም፡፡ ይህም በግንዛቤው ረገድ አሁንም ድረስ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለ የሚያሳይ ነው፡፡

የኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሐን ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ታምራት ኃይሉ በበኩላቸው አሁንም ድረስ ምክር ቤቱ ላይ ለሚነሱ አደረጃጀት እና ቁመና ችግሮች አባል መሆን የሚገባቸው የሚዲያ አካላት ያላቸው ተሰታፎ ዝቅተኛነት ያነሳሉ፡፡   

የምክር ቤቱ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መንቃት ይገባቸዋል ሲሉ አሰተያየታቸውን የሚሰጡት ወ/ሪት ፋሲካ ታደሰ ከኢትዮጲያ አርታኢያን ማህበር ባቀረቡት ፅሁፍ እንዳሉት ‹‹የመገናኛ ብዙሐን ምክር ቤት ከተቋቋመ አራት አመታት በላይ ቢሞላውም የተሰጠውን ስልጣን እና ተግባር በማስከበር ረገድ እንዲሁም የሚዲያዎችን የርስ በርስ ቁጥጥር ግቡን እንዲመታ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በተለይም ሊመለከታቸው የሚገቡ በሚዲያ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ በማስተናገድ ረገድ ወደ ስራ አልገባም›› ሲሉ ይገልፃሉ፡፡

የኢትዮጲያ የሚዲያ ህግ ሪፎርም ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ጎሹ በበኩላቸው ‹‹የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ቁጥር 590/2000፣ የብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 533/1999፣ እና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008ን ጨምሮ የመገናኛ ብሁሃን ሕጎች ከመፅደቃቸው በፊት በረቂቅ ደረጃ ሳሉ ጀምሮ አወዛጋቢ እንደነበሩ ይታወሳል። ሕጎቹ ታውጀው በሥራ ላይ ሲውሉ በይዘታቸውም ሆነ በአተገባበራቸው አወዛጋቢነታቸው ጨምሯል። በተለይም ሕጎቹ “መሰረታዊ የዜጎችን መብቶች ለማጣበብና ዘርፉን ለማዳከም ምክንያት ሆነዋል” በሚል ብዙ ትችት ሲቀርብባቸው ቆይቷል። ከዚህም በመነሳት፣ መንግሥት እነዚህን ሕጎች መልሶ በመፈተሽና ችግሮቹን በመለየት ለመገናኛ ብዙሐን ዘርፉ የርስ በርስ ቁጥጥርን በሚደግፍ መልኩ በገልፅ በህግ ደረጃ ተረቆ በምክር ቤት ዋስትና ተሰጥቶት ወጧል፡፡››

የኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሐን ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋየ ዋነኛዎቹ የመገናኛ ብዙሃን የርስ በርስ ቁጥጥር በኢትዮጵያ ሚዲያ ፖሊሲ፣ እና አዋጆች እውቅና የተሰጠው በመሆኑ ዘርፉን ባለሙያው እንዲመራው ለመስራት ባለስልጣኑ ዝግጁነት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

Next Post
  • News

ንጉስ ኢስዋቲኒ የዚምባብዌን ልማት ፕሮጀክቶችን አድንቁ።

Ayele Addis May 4, 2023

ንጉስ ኢስዋቲኒ የዚምባብዌን ልማት ፕሮጀክቶችን አድንቁ። በጃሬድ ኦኩሙ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ እና ንጉስ ምስዋቲ ሳልሳዊ የዚምባብዌን አዲሱን ፓርላማ በጎበኙበት ወቅት። ምስል፡ ጨዋነት ንጉስ ምስዋቲ ሳልሳዊ በዚምባብዌ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸው፣ አዲሱ የፓርላማ ህንጻ ማት ሃምፕደን ዘላቂ ቅርስ ሁኖ የሚኖር ነው ብለውታል። አዲስ ፓርላማ መገንባት የጀመረው የኢስዋቲኒ ግዛት ከምባፔ ወደ ሃራሬ ቡድን በመላክ […]

Related Post

  • News

History of Ethiopian Magazines Dawit Alemu eliasww@gmail.com

Ayele Addis May 1, 2022May 1, 2022

uploaded and edited by Ayeleradio@ayele-addis Introduction Ethiopian magazines had a shortage history, because of not established printing enterprises like Birhanena Selam huge printing press and also lately introduce other publishing technology. Under this title, we are trying to overview the recent three regimes, which are the Imperial, The Derg, and the EPRDF regimes respectively.  From […]

  • Magazine
  • News

የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ

Ayele Addis January 23, 2024

በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ማህበራዊ ገጽ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነውኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችውን ስምምነት ተከትሎ፤ አብን ስምምነቱን እንደሚቃወም በመጥቀስና ስምምነቱን ሌላ ትርጉም በመስጠት በሃሰተኛ የአብን የትዊተር ገጽ ላይ መረጃ ተሰራጭቷል።ይህንን መረጃ በተመለከተ የኢፕድ የመረጃ ማጣሪያ ጉዳዩን ለማጣራት ጥረት አድርጓል።በዚህም መሰረት በአብን ስም በሃሰት በተከፈተው የትዊተር ገጽ ላይ የተሰራጨው መረጃ በፓርቲው ያልወጣና ፓርቲውም የማያውቀው መሆኑን የፓርቲው […]

  • Africa News Journal of Research
  • ART & Media school of Africa
  • Education
  • Journalism and Communication
  • Latest
  • Magazine
  • Media Litracy
  • News
  • Public Relation
  • Radio & TV
  • Scholarship and Opportunities
  • Special Edition

ጥቂት ስለኢትዮጵያ ሬዲዮው ዜና ፋይል

Ayele Addis September 7, 2025September 7, 2025

By Eshetu Geletu ጥቂት ስለኢትዮጵያ ሬዲዮው ዜና ፋይል ዜና ፋይል በጋሽ ጌታቸው ሀ/ማርያም አማካይነት በ1979 ተጀመረ፡፡ ጋሽ ዳሪዎስ ሞዲ _ ጋሽ ጥላሁን በላይ _ ነጋሽ መሀመድ _ ዋጋዬ በቀለ _ ብርትኩዋን ሀ/ወይን እና እሸቱ ገለቱ እስከ 1997 ድረስ በቅደም ተከተል ዜና ፋይልን የመሩ ሙያተኞች ናቸው፡፡ በዜና ፋይል ክፍሉ እያንዳንዱ ጋዜጠኛ የራሱን የአጻጻፍና የአቀራረብ ቀለምን ይዞ […]

Breaking News

የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ፡ ጋዜጠኝነት በእውነት፣ በተጠያቂነትና በብሔራዊ እርቅ መካከል ያለውን ክፍተት ሊያጠብ ይችላል?

በአማራ ክልል ሥርዓተ ፆታን ያካተተና ለሁሉም እኩል የትምህርት ዕድል የሚፈጥር ሥርዓት ለመገንባት የተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

Anatomy of a Crisis: Inside the Africa CDC’s Urgent Warning on the Escalating Ebola Outbreak and the Battle for Continental Health Sovereignty

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • ዜና
  • ልዩ ዕትም
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • AMHARA REGION MEDIA AND JOURNALISTS ASSOCIATION (ARMJA)
  • ትምህርቶች
  • Afaan Oromoo
  • Tigrinya (ትግርኛ)
  • Advertising and Media Services
  • Radio Service
  • TV & Digital
  • EthioVerify : Ethiopian Fact Check
Copyright © 2026 EMMA NEWS; Ethiopian Mass Media Action. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress