አዲሱ የኢትዮጵያ ሚዲያ ፖለሲ የህግ ክልከላ አመላከቾችን የያዘ ፣ አሁንም ከቴክኖሎጅ ፣ የይዘት እና የሚዲያ ባላቤትነት ሳንሱር ያልተላቀቀ ሁኖ እናገኝዋለን፡፡ በዚህ የሚዲያ ፖሊሲም አሮጌ ህጎች የተሻሩበት ፣ አዳዲስ ማዕቀፎች የተካተቱበት፣ አዳዲስ የሚዲያ ህጎች አቅጣጫ የተቀመጡበት፣ ቶቀጣጣሪ አካል በስፋት ስልጣን ያገኙበት ነው፡፡ by Ayele Addis Ambelu (ayeleradio@gmail.com)
መግቢያ
መገናኛ ብዙሃን በአንድ ሀገር ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ውስጥ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ። በተለይም በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ሚና አላቸው። መገናኛ ብዙሃን ለሕዝብ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማቅረብ፣ በማሳወቅ፣ በማስተማርና በማዝናናት እንዲሁም የዜጎችን ሀሳብን የመግለጽ ሕገ መንግስታዊ መብት ተግባራዊ በማድረግ እና የተለያዩ አመለካከቶችንና አስተያየቶችን በማስተናገድ ለዲሞክራሲ ስርዓት መዳበር ተፈላጊ የሆነው ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠርና እንዲጎለብት የሚያደርግ መሳሪያ ነው፡፡ ስለሆነም መገናኛ ብዙሃን ሚናዎቻቸውን በተገቢ ሁኔታ እንዲጫወቱ አገራት ራሱን የቻለ የመገናኛና የኮሙዩኒኬሽን ፖሊሲ ሊኖራቸው ይገባል (Hand Book of Mass Media, R.K. RAVINDRAN፣ 2002)፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ከመገናኛ ብዙሃን ዘርፍና ስራ ጋር በተያያዘ መገናኛ ብዙሃንን ለማስፋፋት፣ ጥቅም ላይ ለማዋል፣ ዘላቂነታቸውን ለማረጋገጥ፣ ለመቆጣጠር እና በዘርፉ ከሚፈጠር ለውጥ ጋር አብሮ ለመጓዝ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በመንግስት የሚወሰኑ ውሳኔዎችን፣ አቅጣጫዎችን መርሆችንና ጋይድላይኖችን የያዘ ነው፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ የሚመነጨው አንድ አገር ከምትከተለው የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍናና ነባራዊ ሁኔታ፣ ከህብረተሰቡ ባህል፣ እሴት፣ አመለካከትና ፍላጎት፣ ከመሰረታዊ የሰው ልጅ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብትና ሕግጋት፣ በዘርፉ ካጋጠሙ መሰረታዊ ተግዳሮቶች፣ ከቴክኖሎጂ ውጤቶችና ከመሳሰሉት ነባራዊ ሁኔታዎች ነው፡፡ ይህም የአገራት የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲን እንደየአገራቱ የኢኮኖሚ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ደረጃ በይዘቱ የተለያየ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
በዚህም መሰረት የመገናኘ ብዙሃን ፖሊሲ በዋናነት የሚያካትተው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት፣ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ መብት፣ መረጃ የማግኘት መብት፣ የመገናኛ ብዙሃን ሊኖረው ስለሚገባው ሚና፣ ይዘት ከህግና ሙያ ስነምግባር አንፃር፣ የሚዲያ ባለቤትነትና የፋይናንስ ምንጭ ቁጥጥር፣ የሚዲያ መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ እድገት፣ ሚዲያው ከህዝቡ ጋር ሊኖረው የሚገባውን፣ ሚዲያው ከመንግስት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት፣ የሚዲያ ሬጉሌሽን ሁኔታን፣ የሚዲያው ነፃነትና ግዴታን፣ የግል ሚዲያ ባለቤትነትና ፍትሃዊ የሚዲያ ውድድርን፣ ለሚዲያው የሚደርግ የመንግስት ድጋፍን፣ የሚዲያ ቴክኖሎጂና የመሳሰሉትን ዋና ዋና አቅጣጫዎችንና የፖሊሲ ጉዳዮችን ያካተተ ነው፡፡ በአሁን ጊዜም በአለማችን በተፈጠረው የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽ ቴክኖሎጂ፣ ማሰራጫና መቀበያ መሳሪያ ውህደትን ተከትሎ መንግስታት በመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲዎቻቸው በሁሉም የማሰራጫ መሳሪያዎች ማለትም በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በኮምፒውተር፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የተሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶችን የፈቃድ፣ ምዝገባና የሬጉሌሽን አሰራሮችን በማካተት ላይ ይገኛሉ፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ በአመዛኙ በአገራት በመንግስት ደረጃ የሚዘጋጅ ቢሆንም እንደ የአውሮፓ ህብረት በመሳሰሉት አህጉራዊ ድርጅቶችና ህብረቶች፣ የአለም ንግድ ማህበርን በመሳሰሉ በአለም አቀፍ ድርጅቶች እና በራሱ በሚዲያው የሙያ ማህበር ወይም ካውንስል ሊዘጋጅ ይችላል፡፡ የፖሊሲ ዝግጅት ሂደቱም የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ፣ ልዩ ልዩ ሂደቶችንና ያለፈና በርካታ ግብአቶችን የተጠቀመ መሆን ይኖርበታል፡፡ አንድ ፖሊሲ ውጤታማ እንዲሆን በዝግጅቱ ሳይንሳዊ የሆኑ ቲዎረቲካልና ኢምፐሪካል የምርምር ውጤቶችን፣ በልዩ ልዩ መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎችን፣ አመራሮችን፣ የፊሎዘፈሮችን እውቀት፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አስተያየት ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
የመገናኘ ብዙሃን ፖሊሲ ከመሰረታዊ የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ መብቶች አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ በአሁን ጊዜ አገራት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ፖሊሲን በተናጠል ወይም በአንድነት የሚያዘጋጁበት ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን በዚህም መሰረት በበርካታ አገራት የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ አዘጋጅተው ተግባራዊ አድርገዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ ነፃነት የተረጋገጠ ከመሆኑ በተጨማሪ ፕሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነፃነት ኖሮት የተለያዩ አስተያየቶችን የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ተደርጎለታል (ህገ መንግስቱ፣ 1995)፡፡ ይሁንና በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የሚመራበት ራሱን የቻለ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ባለመኖሩ ዘርፉን በብቃት እና በጥራት በማስፋፋት ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጎች የመረጃ ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም፡፡ በመሆኑም መገናኛ ብዙሃንን በማስፋፋትና ቀጣይነታቸውን በማረጋገጥ የዜጎችን የመረጃ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይረዳ ዘንድ በአገራችን ራሱን የቻለ የመገናኛ ብዙሃን የፖሊሲ ሰነድ ሊዘጋጅ ችሏል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲው የዘርፉን ዋና ዋና ችግሮች እና መከናወን የሚያስፈልጋቸውን ወሳኝ ጉዳዮች ለይቶ ለማወቅ የሚያስችለውን አቅም መያዙን በዚህ ጥናት ነባራዊ ሁኔታውም ተገምግሟል፡፡ በጥናቱ ግኝት መሰረትም የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲና ማስፈፀሚያ ሕጎች ዝግጅት አስፈላጊነት ተለይተው ተጠቅሰዋል፡፡ በዚህም መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 88ኛ መደበኛ ስብሰባ በፖሊሲው ላይ በመወያየትና ተጨማሪ ግብአቶች እንዲካተቱ በማድረግ ፖሊሲው በሥራ ላይ እንዲውል የወስነው ይዘት እና ሽፋን አለማ እና ግብ በዝርዝር ተቃኝቷል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲው ለመገምገም በዋናነት የሚከተሉት አራት ዋና ዋና ጥያቄዎች የፖሊሲው የመገመገሚያ መስፈርት ሁነው አገልግለዋል፡፡
- የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ አስፈላጊነት፣ መሰረታዊ እሳቤዎች፣ ራእይ፣ ተልዕኮ፣ ግቦች፣ መርሆዎች፣ የፖሊሲ ወሰን፣ አላማዎች፣ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ዋና ዋና ሚና እና አጠቃላይ ሁኔታው ምን ይመስላል?
- የመገናኛ ብዙሃን የጋራ ፖሊሲዎች እና የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎችን ምን ምን ናቸው?
- ለእያንዳንዱ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የሚያገለግሉ የፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች የትኞቹ ናቸው?
- ፖሊሲውን የማስፈጸም ኃላፊነት ተለይቶ የተሰጣቸውን አካላት እነማን ናቸው?
የኢትዮጵያ ሚዲያ ዋና ዋና ፖሊሲ ጉዳዮች
አዲሱ የሚዲያ ፖሊሲ የመለሳቸው ጥያቄዎች ወይም ዋና ዋና አትኩሮቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- አዲሱ የመገናኛ ብዙሐን ፖሊሲ የሚከተሉትን ዋና ዋና
- የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት፣
- ሃሳብን በነፃነት መግለፅ መብት፣
- መረጃ የማግኘት መብት፣
- የመገናኛ ብዙሃን ሊኖረው ስለሚገባው ሚና፣
- ይዘት ከህግና ሙያ ስነምግባር አንፃር፣
- የሚዲያ ባለቤትነትና የፋይናንስ ምንጭ ቁጥጥር፣
- የሚዲያ መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ እድገት፣
- ሚዲያው ከህዝቡ ጋር ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነት፣
- ሚዲያው ከመንግስት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት፣
- የሚዲያ ሬጉሌሽን ሁኔታን፣
- የሚዲያው ነፃነትና ግዴታን፣
- የግል ሚዲያ ባለቤትነትና ፍትሃዊ የመቀም የሚዲያ ውድድርን፣
- ለሚዲያው የሚደርግ የመንግስት ድጋፍን፣
- የሚዲያ ቴክኖሎጂና የመሳሰሉትን ዋና ዋና አቅጣጫዎችንና የፖሊሲ ጉዳዮችን ያካተተ ነው፡፡
የመገናኛ ብዙሐን ፖሊሲው የመለሳቸው አዳዲስ መልሶች
በአሁን ጊዜም በአለማችን በተፈጠረው የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽ ቴክኖሎጂ፣ ማሰራጫና መቀበያ መሳሪያ ውህደትን ተከትሎ መንግስታት በመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲዎቻቸው በሁሉም የማሰራጫ መሳሪያዎች ማለትም በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በኮምፒውተር፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የተሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶችን የፈቃድ፣ ምዝገባና የሬጉሌሽን አሰራሮችን በማካተት ላይ ይገኛሉ፡፡
በተጨማሪም ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ሊደረግ እንደሚገባና ከፍተኛው የባለቤትነት የአክስዮን ድርሻ በኢትዮጵያውያን ይዞታና ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በፖሊሲው ተካቷል፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ባለቤትነት ቁጥርን ለመወሰንም አንድ የንግድ ድርጅት በአንድ ጊዜ የሬዲዮ፣ የቴሌቪዥን፣ የጋዜጣና የመፅሄት ባለቤት መሆን የሚችልበትን ሁኔታ ፖሊሲው ፈጥሯል፡፡
በተጨማሪም አገራዊ ጥቅምን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ፣ መገናኛ ብዙሃን በተለያዩ ሰዎች መያዝን የሚያበረታታ፣ መገናኛ ብዙሃንን የመረጃና የሀሳብ ስብጥርንና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በማበረታታት በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል ግልፅ የሆነ ዝርዝር የመገናኛ ብዙሃን ባለቤትነት ሕግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
የመገናኛ ብዙሐን ፖሊሲው ክልከላዎች
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ፖለሲ በዋናነት የሚከትሉትን የሙያው፣ የኢንዱስትሪው እና የህዝብ የነበሩ ክልከላዎችን አዳብሮ እንደቀጠለ ነው፡፡
አሁንም ድረስ በፖሊሲው የክልከላ ማዕቀፎች የተካተቱበት ነው፡፡ በሌላ በኩልም ፖሊሲው የውጭ አገር ዜጋና በውጭ አገር ዜጋ የተቋቋሙ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ፈቃድ የሚከለከሉ መሆኑን አስቀምጧል፡፡የሃይማኖት ተቋማት የሬዲዮ ሞገድ በመጠቀም ከምድር ወደ አየር ከሚሰራጭ የብሮድካስት አገልግሎት ይከለክላል፡፡በፖሊሲው የብሮድካስት ፈቃድ እንዳያገኙ ከተከለከሉት ውስጥ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የአክስዮን አባል የሆኑበት የብሮድካሰት ጣቢያ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አመራር የሆኑበት የብሮድካሰት ጣቢያ ይገኙበታል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎንም በማስታወቂያ አስነጋሪዎች የሚተላለፉ የምርትና አገልግሎት የንግድ ማስታወቂያዎች የህጻናትንና የወጣቶችን ጤንነትና ደህንነት የሚነካ፣ አገራዊ ባህልና እሴትን የሚሸረሽር፣ የአልኮል መጠጦችን የሚያስተዋውቅ፣ የተዛባ የፆታ ውክልናን የያዙ እንዲሁም ሌሎች ሕግን የሚተላለፉ መልዕእክቶችን ማሰራጨት በሕግ ሊከለከል እንደሚገባ በፖሊሲው ተመላካቷል፡፡
በመንግስት የአገልግሎት ግዥ ሕግና መመሪያም የማስታወቂያና የስፖንሰርሽፕ አገልግሎትን በቀጥታ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን መስጠት የሚፈቀድ ሲሆን፤ የመንግስት ወጪን ከመቆጠብ ጋር በተያያዘም ለንግድ መገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያና ስፖንሰር መስጠት ይከለከላል፡፡
በተጨማሪም የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን በመንግስት የሚደጎሙ ሲሆን፤ የንግድ የመገናኛ ብዙሃን ግን አይደጎሙም፡፡ ይህ መሆኑም በሕገ መንግስቱ ፕሬስ ጥበቃ ይደረግለታል የሚለውን ድንጋጌ ሊቃረን እንዲሁም የግል መገናኛ ብዙሃንን ቀጣይነት በማዳከም ከገበያ ሊያስወጣ እና በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ ሊያዳክም ይችላል፡፡
አውንታዊ ሃሳብ
ፖሊሲውን በሚመጥን መልኩ የሚዲያ ተቆጣጠሪ አካላት ተግባር እና ስራን ያዋሀደ የተከለሰ አዲስ አደረጃጀት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡
***/
የሚያካትተው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት፣ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ መብት፣ መረጃ የማግኘት መብት፣ የመገናኛ ብዙሃን ሊኖረው ስለሚገባው ሚና፣ ይዘት ከህግና ሙያ ስነምግባር አንፃር፣ የሚዲያ ባለቤትነትና የፋይናንስ ምንጭ ቁጥጥር፣ የሚዲያ መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ እድገት፣ ሚዲያው ከህዝቡ ጋር ሊኖረው የሚገባውን፣ ሚዲያው ከመንግስት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት፣ የሚዲያ ሬጉሌሽን ሁኔታን፣ የሚዲያው ነፃነትና ግዴታን፣ የግል ሚዲያ ባለቤትነትና ፍትሃዊ የሚዲያ ውድድርን፣ ለሚዲያው የሚደርግ የመንግስት ድጋፍን፣ የሚዲያ ቴክኖሎጂና የመሳሰሉትን ዋና ዋና አቅጣጫዎችንና የፖሊሲ ጉዳዮችን ያካተተ ነው፡፡ በአሁን ጊዜም በአለማችን በተፈጠረው የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽ ቴክኖሎጂ፣ ማሰራጫና መቀበያ መሳሪያ ውህደትን ተከትሎ መንግስታት በመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲዎቻቸው በሁሉም የማሰራጫ መሳሪያዎች ማለትም በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በኮምፒውተር፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የተሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶችን የፈቃድ፣ ምዝገባና የሬጉሌሽን አሰራሮችን በማካተት ላይ ይገኛሉ፡፡
2. የአገራችን የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ዳሰሳ
መገናኛ ብዙሃንን በማስፋፋትና የሕዝብን ጥቅም ለማረጋገጥ የዘርፉን ነጻነት ያረጋገጠና ለሌሎች ተነጻጻሪ መብቶች ጥበቃ የሚያደርግ ወጥ የሆነ ፖሊሲና የሕግ ማእቀፍ ያስፈልጋል፡፡ ስለአመለካከት እና ሃሳብን በነጻ የመያዝና መግለጽ መብት፣ ስለሚዲያ ነጻነት፣ በዘርፉ ስለሚሰማሩ አካላት መብትና ግዴታ፣ ስለሌሎች ተነጻጻሪ መብቶች ጥበቃ፣ መረጃ የማግኘት መብትንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በግልጽ ፖሊሲ ሊወሰኑ ይገባል።
በአገራችን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወጥ የሆነ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ አልነበረም፡፡ ይሁንና በልዩ ልዩ ሰነዶች መገናኛ ብዝሃን የሚመሩበት የፖሊሲ ሰነድ የነበረ መሆኑን ለመረዳት እንችላለን፡፡ ከነዚህ ሰነዶች ውስጥ የኢ.ፌ.ዲሪ ሕገ መንግስት፣ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጉዳዮች በኢትዮጵያና መሰል ሰነዶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጉዳዮች በኢትዮጵያ (1994) በተሰኘው የፖሊሲ ሰነድ ስለሚዲያና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንታባ ትግላችን በሚለው ክፍል ውስጥ ሚዲያን በተመለከተ ውስን የፖሊሲ ጉዳዮች ተካተዋል፡፡ የፖሊሲ ሰነዱ የሚዲያ ጠቀሜታን በሰፊው ዘርዝሮ ይዟል፡፡ በዚህም መሰረት የፖሊሲ ሰነዱ ሚዲያ አገሪቱ የምትከተላቸው መሠረታዊ አቅጣጫዎችና ፖሊሲዎችን በማስተዋወቅ፣ የሚከናወኑትን ተግባራት እየተከታተለ ለሕዝብ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በመስጠት፣ በሳል የፖለቲካ ውይይትና ክርክር መድረክ ሆኖ በማገልገል እና ሃሳቦችን በነፃ በማንሸራሸር የዴሞክራሲ ባህል እንዲያብብ በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና መጫወት የሚገባው መሆኑን ያስቀምጣል፡፡
በተጨማሪም የፖሊሲ ሰነዱ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የብዙሃንና የሙያ ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚዲያ ስራ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ በዚህም መሰረት መንግስት በሚዲያ ስራ ሰፊ ተሳትፎ በማድረግ ለህዝቡ ወቅታዊ መረጃ በማድረስና የሚዲያ ሚናን በተገቢው በመጫወት ረገድ ትልቅ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ ሰነዱ የብዙሃን፣ የሙያ ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚዲያ ስራ በመሳተፍ በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ተገቢውን ሚና መጫወት ያለባቸው መሆኑንና የግል ሚድያውም ከሚታዩበት የስነምግባር፣ የሙያ፣ የኪራይ ሰብሳቢነትና የመዋቅራዊ ችግሮች ተላቆ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት በጋራ ጉዳዮች ላይ መግባባትን በመፍጠር ረገድ ተገቢውን ሚና መጫወት ያለበት መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ ችግሮቹ የሚፈቱበትን የአጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሄዎችን ይዘረዝራል፡፡ በተጨማሪም ሚዲያ ለዴሞክራሲ ስርዓት መዳበር እጅግ በጣም ተፈላጊ የሆነውን የጋራ አገራዊ እምነትና አመለካከት በመፍጠር ረገድ የላቀ ሚና መጫወት እንዳለበትና ሕዝቡ ለልማትና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በሰፊው እንዲሳተፍ የማድረግ ተልዕኮ እንዳለው ያስቀምጣል፡፡
ይሁንና በአገራችን የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የሚመራበት ወጥ የሆነ የፖሊሲ ሰነድ ለረጅም ጊዜያት ያልነበረ በመሆኑ በዘርፉ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ መፍጠሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ዘርፉን ለማሳደግ የሚረዱ በርካታ የፖሊሲ ጉዳዮች ምላሽ ሳያገኙ ቆይተዋል፡፡ በተለይም እንደ ክፍተት ሊቆጠሩ ከሚችሉት ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
- እንደአጠቃላይ ሲታይ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የሚመራበት፣ የሚደገፍበት የፖሊሲ ሰነድ ለረጅም ጊዜ ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ ዘርፉን ለማሳደግ የሚረዱ ልዩ ልዩ የፖሊሲ ጉዳዮች ምላሽ ባለማግኘታቸው የህግ አካል በማድረግ ዘርፉን ለማሳደግ ሳይቻል መቅረቱ፤
- የመገናኛ ብዙሃን ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት የፖሊሲ ምላሽና ድጋፍ አለማግኘቱ፤
- ለመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ሊደረግ የሚገባው ድጋፍና ማበረታቻ የፖሊሲ ምላሽ አለማግኘቱ፤
- በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ፍትሃዊ ውድድር አለመዘርጋቱ፤
- የሚዲያ ባለቤትነትና ተሳትፎ አሳታፊ አለመሆኑና ውስብስብ የፈቃድ መስፈርቶች መዘርጋት፤
- የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በማቋቋም የርስ በርስ ቁጥጥርን ለማጠናከር የሚያስችል የፖሊሲ ውሳኔ ሳይኖር መቆየቱ፤
- የጋዜጠኞች የስልጠና፣ የጥናት፣ የምርምርና የሽልማት ማዕከልን በማቋቋም ረገድ የታዩ ክፍተቶች፤
- የጋራ የብሮድካስት መሰረተ ልማትን በማቋቋምና በመጠቀም ረገድ ያሉ ክፍተቶች ወዘተ፡፡
በመሆኑም መገናኛ ብዙሃን በአገራችን ሁለንተናዊ እድገት አስዋፅኦ በሚያበረክትበት ሁኔታ እንዲከናወን ለማድረግ የሚያስችል ራሱን የቻለ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ሰነድ መዘጋጀት እንዳለበት በፖሊሲው ሰነድ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ እነዚህም የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ አስፈላጊነት፣ መሰረታዊ እሳቤዎች ፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ግቦች፣ መርሆዎች፣ የፖሊሲው ወሰን፣ ዓላማዎች፣ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ሚና እና የመገናኛ ብዙሃን ሁኔታ ይገኙበታል፡፡
የፖሊሲው አስፈላጊነት ራዕይ እና ተልዕኮ
በፖሊሲው ክፍል አንድ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ አስፈላጊነት፣ መሰረታዊ እሳቤዎች፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ግቦች፣ መርሆዎች፣ የፖሊሲው ወሰን፣ ዓላማዎች፣ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ሚና እና የመገናኛ ብዙሃን ሁኔታ በዝርዝር ተካተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ አስፈላጊነት ዋና ዋና ምክያቶችን እንደሚከተለው ይዘረዝራል፡፡
- በሕገ መንግሥቱ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች የተረጋገጠውን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ፤
- ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊና ከቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር የሚጣጣምና ዘርፉ የሚመራበትን አገራዊ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ፤
- መገናኛ ብዙሃንን ለማስፋፋትና አቅማቸውን ለመገንባት የሚያስችሉ የድጋፍና ማበረታቻ ስርአቶችን ተግባራዊ ለማድረግ፣
- ፖሊሲውን መሰረት ያደረገ ምቹ የሕግ ማዕቀፍ በመዘርጋት ዘርፉን በቀጣይነት ለማሳደግ ነው፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ መሰረታዊ እሳቤዎች መረትም ሀገራችን ተቀብላ ባጸደቀቻቸው አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነት እና የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ድንዳጌ አንቀጽ 19 መሰረት ማንኛውም ሰው ሃሳቡን በነጻ የመግለጽ መብት እንዳለው፣ ይህ መብትም መረጃ የመሰብሰብ፣ የማግኘትና ለሌሎች የማስተላለፍ መብትን የሚያጠቃልል ሆኖ በቃል፣ በጽሁፍ፣ በህትመት ወይም በመረጠው በማንኛውም የመገናኛ ዘዴ በመጠቀም ሃሳብን መግለፅ እንደሚቻል እና ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ኃላፊነቶችና ግዴታዎች ያሉበት እንደ መሆኑ ለሌሎች መብቶችና ነፃነቶች፣ ለሀገር ፀጥታ፣ ለህዝብ ሰላም፣ ጤንነትና ሞራል መከበር ሲባል መብቱ በሕግ ሊገደብ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 29 መሰረት ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሃሳቡን የመግለፅ ነፃነት ያለው መሆኑ፤ ይህ ነፃነትም በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በፅሁፍ ወይም በህትመት፣ በስነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም አይነት መረጃና ሃሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት መብትን ማካተቱ፣ የፕሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙሃን የስነ ጥበብ ፈጠራ ነፃነት መረጋገጡ፡፡ በተጨማሪም የፕሬስ ነፃነት የቅድመ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ ስለመሆኑና የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት መብትን አካቶ መያዙ፡ ለዲሞክራሲ ስርአት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሃሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባልም ፕሬስ በተቋምነቱ የአሠራር ነፃነትና የተለያዩ አስተያየቶችን የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ተደርጎለታል፡፡
በመንግስት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ መመራት ያለበት መሆኑ፤ የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስም ለመጠበቅ ሲባል ሕጋዊ ገደቦች በነዚህ መብቶች ላይ ሊደነገጉ እንደሚችሉ፤ የጦርነት ቅስቀሳዎች እና ሰብአዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በሕግ እንደሚከለከሉ በሕገ መንግስቱ ተደንግጓል፡፡
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ራዕይ
ሙያዊ ስነ-ምግባርን የሚያከብር፣ የአመለካከትና የሃሳብ ብዝሃነትን የሚያስተናግድ፣ የዲሞክራሲ ባህልን የሚያጎለብት፣ ማህበራዊ ሃላፊነቱን የሚወጣ፣ ገለልተኛ፣ ሚዛናዊና ተወዳዳሪ መገናኛ ብዙሃን ተፈጥሮ ማየት ነው።
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ተልዕኮ
የመገናኛ ብዙሃንን አቅም በማሳደግ፣ ተደራሽነቱን በማስፋፋት፣ መሰረተ ልማትን በማጠናከር እና የቁጥጥር ወይም ሬጉላቶሪ ስራዎችን በመስራት ተወዳዳሪነቱ የተረጋገጠ መገናኛ ብዙሃን መገንባት ይሆናል።
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ዋና ዋና ግቦች
∙ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸውን መብትና ግዴታ በመወጣት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ፤
∙ አመኔታና እርካታን ማሳደግ፤
∙ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት፤
∙ የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም፤
∙ ሀገራዊ ባህልና እሴትን ማጠናከር ናቸው፡፡
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ መርሆዎች
ፖሊሲው መርሆ አድርጎ የተዘጋጀው ብዝሃነትን፣ ተደራሽነትን፣ ሙያዊ ስነ-ምግባርን፣ እንዲሁም ሕግን ማክበርን ነው፡፡
⮚ የፖሊሲው ወሰን
ፖሊሲ ጋዜጣና መጽሄትን፣ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥንን፣ እንዲሁም የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን ያካትታል፡፡
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ዓላማዎች
∙ የመገናኛ ብዙሃን ከማናቸውም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጽዕኖና ጣልቃ ገብነት መጠበቃቸውን ማረጋገጥ፤
∙ የመገናኛ ብዙሃን ብዝሃነትንና ስብጥርን እንዲሁም የህብረተሰቡን መረጃ የማግኘት መብት ማረጋገጥ፤
∙ የመገናኛ ብዙሃን ሙያዊ ስነ-ምግባር ተከትለው ለተገልጋዩ ሕዝብ ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ፤ ተአማኒና ተጨባጭነት ያለው መረጃ እንዲያቀርቡ ማድረግ፤
∙ መገናኛ ብዙሃን የዲሞክራሲያዊ ልምዶችን በማስረፅ፣ የዜጎችን ትስስር በማጠናከር፣ የአገርን አጠቃላይ ገፅታ ከፍ በማድረግ ረገድ ሊጫወቱ የሚገባቸውን ሚና ማጠናከር፣ ∙ የመገናኛ ብዙሃን መረጃን በማሰባሰብና በማሰራጨት ሂደት የተጠያቂነትን እሴቶችን
በማዳበር የድርጅቶችን እና የግለሰቦችን መልካም ስምና ዝና እንዲሁም ሌሎች መብቶችንና ጥቅሞችን መጠበቃቸውን ማረጋገጥ ናቸው፡፡
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች
∙ መገናኛ ብዙሃን በዓለም ዓቀፍ ድንጋጌዎችና በሀገሪቱ ሕገ መንግስት ላይ ተንተርሰው ለተገልጋዩ ሕዝብ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ሁኔታ እንዲደራጁ ማድረግ፤ ∙ በሕዝብና በንግድ መገናኛ ብዙሃን መካከል ፍትሃዊ ውድድር እንዲኖር ማድረግ፤ ∙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያገለግሉ የማህበረሰብ አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የማቋቋም እድል መፍጠር፤
∙ የመገናኛ ብዙሃን መሰረተ ልማትን በማስፋፋት መገናኛ ብዙሃንን በአይነት፣ በቋንቋና በቁጥር ለማስፋፋት ድጋፍ ማድረግ፤
∙ የመገናኛ ብዙሃን አመራሮችና ሙያተኞች ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፤
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ዋና ዋና ሚናዎች
∙ ለሕዝቡ መረጃ መስጠት፣ ማስተማር፣ ማሳወቅና ማዝናናት፣
∙ ለሰላም፣ ለልማትና ለአገራዊ ሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት የሕዝቡን ተሳትፎ ማሳደግ፣
∙ የዜጎችን ሀሳብን የመግለጽ ሕገ መንግስታዊ መብት ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም የተለያዩ አመለካከቶችን፣ አስተሳሰቦችንና አስተያየቶችን በማስተናገድ የዲሞክራሲ ባህልና ስርዓት ግንባታ እንዲሁም የብሄራዊ መግባባት እንዲጠናከር ማድረግ፣
∙ የዜጎችን የእርስ በእርስ ግንኙነትና ትስስር ማጠናከር፣
∙ የሕዝቦችን ቋንቋ፣ ባህልና ዕሴት ማስተዋወቅና ማጎልበት፣
∙ የአገርን አጠቃላይ በጎ ገፅታ ከፍ ማድረግ፣
II. የመገናኛ ብዙሃን የጋራ ፖሊሲዎች እና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች
ፖሊሲው በክፍል ሁለት ስር ሁሉም አይነት የመገናኛ ብዙሃን ሊከተሏቸው የሚገቡ 22 ዋና ዋና የጋራ አሰራርና አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን የሚያገለግሉ የጋራ ፖሊሲዎች እና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
1. ምቹ የሕግ ማዕቀፍ መዘርጋት
ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማረጋገጥ የሚወጡ ሕጎች ከአለም አቀፍና አህጉራዊ ስምምነቶችን ጋር የማይቃረኑና የተጣጣሙ መሆን እንዳለባቸው፤ መረጃ የመሰብሰብ፤ የመቀበልና የማሰራጨት እንዲሁም ምንጮችን ያለማሳወቅ መብቶች በሕግ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ፤ ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ ሕጎች መሻሻል ያለባቸው መሆኑ በፖሊሲው ተካቷል፡፡
2. መረጃ የማግኘት መብት
በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 29 ማንኛውም ሰው መረጃ የመሰብሰብ፤ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነት እንዳለው ተደንግጓል፡፡ ስለሆነም ዜጎች ከመንግስት ተቋማት መረጃ ማግኘት እንዲችሉ ተቋማቱ መረጃ የመስጠት ግዴታቸውን እንዲወጡ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን፣ ሁሉም ተቋማት መረጃ በኦንላይን የሚያሰራጩበትን ዘመናዊ አሰራር ማዳበርና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው፤ ፈጣንና ቀልጣፋ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ብሔራዊ የመረጃ ማዕከል በማቋቋም መረጃ በቀላሉ የሚሰጥበት አሰራር መዘርጋት ያለበት መሆኑና እራሱን የቻለ የመረጃ ነጻነትን የተመለከተ ሕግ ከዝርዝር ማስፈጸሚያ ደንብና መመሪያዎች ጋር መውጣት ያለበት መሆኑ በፖሊሲው ተካቷል፡፡
3. የመገናኛ ብዙሃን ባለቤትነት
መገናኛ ብዙሃን የህዝብን የመረጃ ባለቤትነት ያረጋገጠ፣ ዋነኛ ትኩረቱም ዜጎችን የማገልገልና ዲሞክራሲ እንዲጠናከርና እንዲዳብር ለማድረግ የሚያስችል መሆን ይኖርበታል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለቤትነት በሕዝብ፣ በንግድና በልዩ ልዩ ማህበረሰቦች የተያዘ ይሁን እንጂ የንግድ መገናኛ ብዙሃን ባለቤትነትና ስብጥር ፍትሃዊ አይደለም፡፡ ስለሆነም በንግድ መገናኛ ብዙሃን የተለያየ ስብጥር እና ብዝሃነት ያለው የሚዲያ ምህዳር እንዲፈጠር ለማድረግ ግለሰብን ጨምሮ የንግድ ተቋማት የንግድ የህትመት መገናኛ ብዙሃን ባለቤት እንዲሆኑ መፍቀድ የሚገባ መሆኑ በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ሊደረግ እንደሚገባና ከፍተኛው የባለቤትነት የአክስዮን ድርሻ በኢትዮጵያውያን ይዞታና ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በፖሊሲው ተካቷል፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ባለቤትነት ቁጥርን ለመወሰንም አንድ የንግድ ድርጅት በአንድ ጊዜ የሬዲዮ፣ የቴሌቪዥን፣ የጋዜጣና የመፅሄት ባለቤት መሆን የሚችልበትን ሁኔታ ፖሊሲው ፈጥሯል፡፡
የንግድ መገናኛ ብዙሃን አወቃቀርን በተመለከተም የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ለማቋቋም በንግድ ማህበር መደራጀት አስፈላጊ ሲሆን፤ ጋዜጣና መፅሄት ለማሳተም ግን አንድ ግለሰብ ብቻውን በባለቤትነት እንዲያቋቁም ይደረጋል፡፡ መገናኛ ብዙሃን የሃብት ምንጫቸውን ግልፅ በማድረግ ለተደራሲያኖቻቸው ከመገናኛ ብዙሃን ባለቤቶች ተፅእኖ ነፃ መሆናቸውን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። ይህም ሲሆን በጋዜጠኛና በባለቤቱ መካከል የጥቅም ግጭቶችንና አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችን ማስወገድ፣ በኤዲቶሪል ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ የተጠያቂነት ግንኙነት መፍጠርና ለአዘጋጅ ነጻነት የተበጀውን የሕግ ዋስትና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ፖሊሲው አፅንዎት ሰጥቶበታል፡፡
የሕዝብ መገናኛ ብዙሃንን በተመለከተም በፌዴራል መንግስት ወይም በክልል መንግስታት ወይም በኮርፖሬሽን መልክ ሊቋቋሙ እንደሚችሉና የበጀት ምንጫቸው አቅም በፈቀደ መጠን ከመደበኛው የፌዴራልና የክልል መንግስታት በጀት የተለየ ምንጭ ኖሯቸው ሊደራጁ እንደሚገባ በፖሊሲው ተወስኗል፡፡ ከዚህ ባሻገርም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመንግስት አስፈጻሚ ተቋማት የሕዝብም ሆነ የንግድ ብሮድካስት ባለቤት መሆን አይችሉም።
የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃንን በተመለከተም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ማህበራት፣ ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ማህበራት አባላት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች አካታች በሆነ መልኩ ተደራጅተው የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ባለቤት ሊሆኑ ይችላሉ።
በተጨማሪም አገራዊ ጥቅምን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ፣ መገናኛ ብዙሃን በተለያዩ ሰዎች መያዝን የሚያበረታታ፣ መገናኛ ብዙሃንን የመረጃና የሀሳብ ስብጥርንና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በማበረታታት በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል ግልፅ የሆነ ዝርዝር የመገናኛ ብዙሃን ባለቤትነት ሕግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
4. የብሮድካስት ፈቃድ የሚሰጣቸውና የሚከለከሉ አካላት
በመገናኛ ብዙሃን እና በኢንቨስትመንት ሕጎች ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የውጭ አገር ዜጎች በመገናኛ ብዙሃን ስራ መሰማራት እንደማይችሉ ተደንግጓል፡፡ ይሁንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዚህ ረገድ የሚያበረክቱት የካፒታልና የሙያ ሽግግር ለዘርፉ እድገት አስተዋፅኦ ስለሚኖረው ውስን ድርሻ በመያዝ በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ እንዲሳተፉ በፖሊሲው ተፈቅዷል፡፡ በሌላ በኩልም ፖሊሲው የውጭ አገር ዜጋና በውጭ አገር ዜጋ የተቋቋሙ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ፈቃድ የሚከለከሉ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ ከዚህ በሻገር በውጭ አገር ተቋቁመው የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙሃን በአገር ውስጥ ቅርንጫፍ ከፍተው የሚሰሩበት ወይም የዜና ወኪል በመመደብ ከአገር ውስጥ ለማሰራጨት ፈቃድ ከጠየቁ የሚሰጣቸው መሆኑን አካቷል፡፡
የሃይማኖት ብሮድካስት ጣቢያዎችን በተመለከተም የሃይማኖት ድርጅቶች አስተምህሮታቸውን በመገናኛ ብዙሃን ለማድረስ ስለሚፈልጉና በርካታ ህብረተሰብም ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞችን ለመከታተል ፍላጎቱ ስላለው የሃይማኖት ተቋማት የሬዲዮ ሞገድ በመጠቀም ከምድር ወደ አየር ከሚሰራጭ የብሮድካስት አገልግሎት አይነት ውጪ በሌሎች ማሰራጫ መንገዶች የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ እንዲያገኙ እንደሚደረግ ይገልፃል፡፡ በተመሳሳይም የሃይማኖት ጣቢያዎችም ሆኑ ሌሎች ብሮድካስተሮች የሃይማኖት ፕሮግራም ለማሰራጨት ከፈለጉ የሚፈቀድላቸው መሆኑንና የሃይማኖት ጣቢያዎች የምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ እንዲሁም ተያያዥ ሁኔታዎች በመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል፣ በሃይማኖት ተቋማት እና የሃይማኖት ተቋማትን በሚመዘግበው አካል በጋራ የሚከናወን መሆኑን አካቷል፡፡
በፖሊሲው የብሮድካስት ፈቃድ እንዳያገኙ ከተከለከሉት ውስጥ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የአክስዮን አባል የሆኑበት የብሮድካሰት ጣቢያ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አመራር የሆኑበት የብሮድካሰት ጣቢያ ይገኙበታል፡፡ በመሆኑም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት ንብረቶች የብሮድካስትና የህትመት መገናኛ ብዙሃን ስራ ተሳትፎ በፖሊሲው መልስ ተሰጥቶታል፡፡ ፡ በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲ መገናኛ ብዙሃን በግልፅ የፖለቲካ ልሳን ሆነው ለመስራት ከፈለጉ በጋዜጣና መፅሄት ሕትመት እንዲስተናገዱ የሚደረግ መሆኑንና በብሮድካስት የማይሰጥ መሆኑን ፖሊሲው ወስኗል፡፡ በተጨማሪም በህዝብና በንግዱ መገናኛ ብዙሃን እና በፖለቲካ ፓርቲ ልሳኖች መካከል ያለው ልዩነትም ግልፅ መስፈርትና አሰራር ሊበጅለት እንደሚገባ ፖሊሲው ያሳስባል፡፡
5 የመገናኛ ብዙሃን መሰረተ ልማት
አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ዜጎች የመገናኛ ብዙሃን ተደራሽ አይደሉም፡፡ በመሆኑም ለመገናኛ ብዙሃን መስፋፋት ይረዳ ዘንድ መንግስት ለመገናኛ ብዙሃን መሰረተ ልማት ዝርጋታ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ እንዳለበት፤ የማሕበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ከፌዴራልና ከክልል ብሮድካስተሮች ጋር ተቀናጅተው መሰረተ ልማትን በጋራ የሚጠቀሙበትን ስልት መቀየስ እንዳለባቸው፤ የብሮድካስት ማሰራጫ ኔትወርክ፣ የአንቴና ምሰሶ እና መሰል መሰረተ ልማቶችን በግልም ሆነ በጋራ በማቋቋምና ብሮድካስተሮች በቁጠባና በውጤታማነት የሚጠቀሙበት፣ በዝቅተኛ ዋጋ የሚከራዩበት እንዲሁም አማተር ባለሙያዎችን ለማበረታታት ፊልምና ፕሮግራም በነፃ የሚቀርፁበት የጋራ የሚዲያ ስቱዲዮ ህንፃ የሚገነባበት፣ የህትመትም ሆነ የብሮድካስት ዘርፍ በየጊዜው ከቴክኖሎጂው ጋር አብሮ የሚዘምንበት አሰራር መዘርጋት እንዳለበት በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
6 የመገናኛ ብዙሃን አመራር
በፖሊሲው የሕዝብ መገናኛ ብዙሃንና የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካሉን የቦርድና የተቋም የአመራር ሁኔታ በተመለከተ የሕግና የአሰራር ክፍተቶች እንደሚስተዋሉና የአብዛኛዎቹ ብሮድካስተሮች የአመራር ወይም የስልጣን ተዋረድ በማዕከል የተገደበ መሆኑን በጥናት ለይቷል፡፡ በመሆኑም የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን የአመራር ምደባ ሙያዊ ብቃትንና የፆታ ስብጥርን፣ ብዝሃነትንና ገለልተኛነትን መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት፤ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን እውነተኛ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃንነቱን ለማረጋገጥ በመገናኛ ብዙሃን አመራር፣ በጋዜጠኝነት፣ በባህል፣ በኢኮኖሚና በቴክኒክ ብቃታቸው የሚታወቁ እንዲሁም በፍትሃዊነት የተወከሉ የሲቪል ማህበረሰብ አባላትን የያዘ የቦርድ አመራር ሊኖረው እንደሚገባ፤ የቦርድ አባላት አስፈላጊውን የምርጫ ሂደት ያለፉና በፌዴራል ወይም በክልል የህዝብ ምክር ቤቶች ይሁንታ ያገኙ መሆን እንዳለባቸው፤ በሌላም በኩል የፋይናንስና ኤዲቶሪያል ስልጣንና ኃላፊነትን ለታችኛው የስልጣን እርከኖች በውክልና ማውረድ እንዳለባቸው ፖሊሲው ግልፅ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
የንግድ መገናኛ ብዙሃን የቦርድ አባላት እና ስራ አመራሮችም በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ሊሆኑ እንደሚገባና ከየትኛውም የፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ መሆን ያለበት መሆኑን፤ ከሦስተኛ ወገን የሚገኝ የኢኮኖሚ ጥቅም ካለም በሚታወቅና ግልፅ በሆነ አሠራር የሚመራ መሆን እንዳለበት በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
7 የመገናኛ ብዙሃን የይዘት ብዝሃነት እና ስብጥር
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ያለው የመገናኛ ብዙሃን የይዘት ብዝሃነትና ስብጥር በውስን ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ የሕዝብና የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማገልገል የሚጠበቅባቸው ቢሆንም፤ ከፍተኛ የሆነ የይዘትና የቋንቋ ብዝሃነት ውስንነት ይታይባቸዋል፡፡ የንግድ መገናኛ ብዙሃንም ቢሆን ተደራሽነታቸው በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ከተሞች የተወሰነ በመሆኑ ስርጭታቸው በጣም ውስን ነው፡፡ የንግድ መገናኛ ብዙሃን በተለይ በኢኮኖሚ እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ጥልቅና ገንቢ የሆነ ትችት አዘል ዘገባ ለማቅረብና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ለማገልገል የሚቸገሩበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም ፖሊሲው የመገናኛ ብዙሃን ስብጥርንና ብዝሃነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ያሰምርበታል፡፡ ይሀን ተግባራዊ ላማድረግም፡-
⮚ ጋዜጠኞች፣ ኤዲተሮች እና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ተቀዳሚ ትኩረታቸው የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ሃሳብና አመለካከት ማስተናገድ ላይ ያተኮረ እንዲሆን ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የሚሰጡ ትምህርቶችና ስልጠናዎችን ማሻሻልና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ፤
⮚ የሕዝብም ይሁን የንግድ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት ወይም በበይነ-መረብ አማካኝነት የሚሠራጭ መገናኛ ብዙሃን ከአጠቃላይ ይዘታቸው ቢያንስ 15 በመቶውን ቢበዛ 40 በመቶውን ለግል ይዘት አምራቾች፣ ተባባሪ አዘጋጆች ወይም የትርፍ ጊዜ ጋዜጠኞች መመደብ እንዳለባቸው፤
⮚ ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሄረሰቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተናጋሪ ማህበረሰቦች የሚኖሩባት አገር በመሆኗም ሁሉም ማህበረሰቦች ከራሳቸው አካባቢና ከጎረቤት ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለቤት እንዲሆኑ እንደሚደረግ፤
⮚ በሂደትም የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ከአገር ውስጥ እና ከአለም አቀፍ አጋሮች የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጠር፤
⮚ በመንግስት ገንዘብ የሚከናወኑ የመገናኛ ብዙሃን ልዩ ልዩ አመለካከቶችን በሚያስተናግዱበት ሁኔታ ሊመሩ እንደሚገባ፤
⮚ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ለአገራዊ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአገሪቱ የቋንቋ ፖሊሲ መነሻነት አቅም በፈቀደ መጠን ይዘቶችን በሁሉም የአገሪቱ ቋንቋዎች እንዲያሰራጩ እንደሚደረግ፤ እና
⮚ በሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ውስጥ የጋዜጠኞች የብሔርና የፆታ ስብጥር መረጋገጥ እንደሚኖርበት በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
8 የመገናኛ ብዙሃን ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት (Universal Access) ማረጋገጥ በአገራችን ለመገናኛ ብዙሃንና ለመረጃ ተደራሽ ያልሆኑ በርካታ ማህበረሰቦች ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ሁሉንም ዜጎች የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ተደራሽ ለማድረግ ቢያንስ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃንን ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት (Universal Access) ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ ከላይ እንደተመለከተው በበርካታ አገራት የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎትን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በእኩልነትና በፍትሀዊነት ለማድረስ የፋይናንስ ድጋፍ (Universal Access Fund) ተመድቦለት ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ ከፍተኛ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ፖሊሲው በዚህ ረገድ ልዩ ልዩ የፖሊሲ ውሳኔዎችን አካቷል፡፡ ለአብነት ያህልም፡-
⮚ የሕዝብ፣ የንግድና የማህበረሰብ ብሮድካስተሮች እንዲሁም የህትመት መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ህዝቦችን የመረጃ ፍላጎትና ተጠቃሚነት መሰረት አድርገው መስራት እንደደለባቸው፤
⮚ አቅም በፈቀደ መጠንም ሁሉም ዜጎች የመረጃ ተደራሽ የሚሆኑበት ሁኔታ መመቻቸት እንዳለበት፤
⮚ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋፋትም የብሮድካስት አገልግሎትን ለመላ የአገሪቱ ሕዝብ ማዳረስ እንደሚገባ፤
⮚ ሁሉም የአገሪቱ ዜጎች የሬዲዮ ወይም የቴሌቪዥን ተከታታይ እንዲሆኑ ለማስቻል፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሽፋን መቶ በመቶ እንዲሆን ማድረግ እንደሚያስፈልግ፤ ⮚ የህዝብ ብሮድካስተሮች ለአካባቢ የማህበረሰብ ብሮድካስት ጣቢያዎች የቴክኒክ፣ የስልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም ንብረታቸውንና የአዕምሮ ውጤታቸውን ለማህበረሰብና ለንግድ ብሮድካስተሮች በማጋራት ተደጋግፈው መስራት እንዳለባቸው፤ ⮚ የሕዝብ ብሮድካስተሮችም የንግድ ብሮድካስተሮችን ህልውና ሳይነኩ የራሳቸውን ገቢ የሚያመነጩበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንዳለበት፤
⮚ በመሆኑም በአገራችን ሁሉም ዜጋ የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ተደራሽ የሚሆንበትን ሁኔታ ለማስፋፋትና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ዩኒቨርሳል አክሰስ ፈንድ ማቋቋም እንደሚያስፈልግ፤
⮚ በተለያዩ ምክንያቶች የመረጃ ተደራሽ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የገጠሩ ማህበረሰብ ቅድሚያ ትኩረት አግኝቶ በቂ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚደረግ፤
⮚ መገናኛ ብዙሃን ለልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ለህፃናት፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለሴቶችና ለአካባቢ ጉዳዮች በቂ ትኩረት በመስጠት ተገቢውን ሽፋን መስጠት እንዳለባቸውና መንግስትም ለመሰል ፕሮግራሞች ድጋፍ የሚደረግበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንዳለበት፤ እንዲሁም
⮚ የንግዱ ዘርፍ ልዩ ልዩ ሃሳቦችን በማንሸራሸር ረገድ ለዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ከፍተኛ ሚና ስለሚጫወት በመገናኛ ብዙሃን ስራ ሰፊ ተሳትፎ እንዲያደርግ መበረታታት እንዳለበት በፖሊሲው ተወስኗል፡፡
9 የይዘት ምርትና ይዘትን በትብብር ስለማዘጋጀት
የይዘት ምርት አንድ ጠቃሚ የሥራ መስክና ኢንዱስትሪ ነው፡፡ ከመገናኛ ብዙሃን የይዘት ዝግጅት ጋር በተያያዘ የአቅም ግንባታና የድጋፍ አገልግሎት በማግኘት ረገድ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ዘርፍ ነው፡፡ ይህ ዘርፍ በስሩ የዜና አገልግሎት፣ የኪነጥበብ፣ ሙዚቃ፣ ድራማ፣ ቴአትር፣ የቪዲዮና ፊልም፣ የዶኩመንተሪ፣ የማስታወቂያ፣ የመዝናኛና መሰል ተዛማጅ ስራዎች ኢንዱስትሪን ያካተተ ሲሆን ለመገናኛ ብዙሃን በግብአትነት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ይዘቶችን በማምረት ለመገኛኛ ብዙሃን እንዲያቀርብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ አንዱስትሪ ይዘቶችን በአይነትና በጥራት ማምረት ከቻለ መገናኛ ብዙሃን ተፈላጊውን ይዘት መግዛት ስለሚችሉ ለህብረተሰቡ አይነተኛ የመረጃ ምንጭ ለመሆንና ኢንዱስትሪውንም በማሳደግ አገሪቱ ተጠቃሚ እንድትሆን ከማስቻል አኳያ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት በፖሊሲው ግንዛቤ ተወስዷል፡፡
በመሆኑም የኢንዱስትሪው መሰረታዊ ማነቆዎች ወይም ችግሮች በጥናት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ መፈታት እንዳለባቸው፤ በአእምሮ ውጤቶች መብት ጥበቃ እንዲሁም በሰው ሃይል፣ በፋይናንስና በቁሳቁስ ረገድ ያሉት ችግሮች መቀረፍ እንዳለባቸው፤ የብሮድካስት የፈቃድ የጨረታ ውድድር መስፈርቶች በሚዘጋጁበት ወቅት ጣቢያዎቹ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብዝሃነት የሚያንፀባርቁ ፍላጎቶችን ያካተቱ ይሆኑ ዘንድ ከተለያዩ የአካባቢ፣ የክልልና አገራዊ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጋር በጋራ ይዘት የማምረት ስራ ለሚሰሩ ተቋማት ቅድሚያ መሰጠጥ እንዳለበት፤ በተለያዩ የክልልና የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን መካከል የጋራ ትብብር በመፍጠር በህዝቦች መካከል የጋራ መግባባት እና መተማመንን ማጠናከር፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን የሙያ ዕድገትን የተቃና ማድረግ እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና የግል ይዘት አምራቾችን ሙያዊ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ ፖሊሲው አፅንኦት ሰጥቷል፡፡
10 ለአገራዊ ፕሮግራም ወይም ይዘት ትኩረት ስለመስጠት
በበርካታ አገራት የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲና ሕጎች ለአገር በቀል ይዘቶች ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራበታል፡፡ መገናኛ ብዙሃን ጥራታቸውን የጠበቁ እና የተለያዩ ይዘት ያላቸውን አገራዊ፣ አካባቢያዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ፕሮግራሞችን ሊያቀርቡ ይገባል፡፡ ስለሆነም የሕዝብ፣ የንግድና የማህበረሰብ ብሮድካስተሮች ሊያቀርቡት የሚገባውን የአገራዊ ፕሮግራም ይዘት ዝቅተኛውን መጠን መወሰን ተገቢ እንደሆነ እና ይህም መጠን ተግባራዊ የሚሆንበትን ጊዜ በሕግ መወሰን እንደሚያስፈልግ፤ በተጨማሪም ለመገናኛ ብዙሃን ፈቃድ የሚሰጠው አካልም መገናኛ ብዙሃን ከሚያሰራጩት ይዘት የተወሰነ መቶኛውን ድርሻ ለአገር ውስጥ ጉዳይ እንዲመድቡ በፈቃድ ጨረታ መስፈርት ውስጥ ማካተት እንዳለበት በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
11 የመገናኛ ብዙሃን የሕዝብ አገልጋይነት ሚና እና ልዩ ፕሮግራም
የመገናኛ ብዙሃን ለሕዝብ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ከማቅረብ፣ ከማሳወቅ፣ ከማስተማርና ከማዝናናት በተጨማሪ መገናኛ ብዙሃን፡-
⮚ የሕዝብ ድምፅ ትኩረት አግኝቶ እንዲሰማ ማበረታታት፤
⮚ የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ እንደመሆናቸው ውሳኔ ሰጪ የመንግስት አካላትን ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ በሰላም፣ በልማትና በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ወሳኝ ሚና መጫወት፤
⮚ ልዩ ልዩ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮግራሞችን በማሰራጨት የሕዝብ አገልጋይነት ሚናቸውን መወጣት፣
⮚ መገናኛ ብዙሃን ለዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስፈላጊውን ሚና መጫወታቸውን፤ ብዝሃነትን በማረጋገጥ አገራዊ አንድነትን ማጠናከራቸውን፣ በመረጃ የበለፀገ ህብረተሰብ በመገንባትና መሰል የመገናኛ ብዙሃን ሚናን በመወጣት ረገድ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ ማረጋገጥ፤
⮚ በምርጫ ወቅት ነፃ የአየር ሰዓት በመመደብ፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ወይም የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ወይም ሕገ መንግስታዊ ሥርአትን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰት መንግስት የሚሰጣቸውን መግለጫዎች በማሰራጨት ሃላፊነታቸውን መወጣት፤ እንዲሁም
⮚ ከዚህ ጎን ለጎን በተለየ ሁኔታ ትኩረቱን በአንድ ጉዳይ ላይ ያደረገ ፕሮግራም እንዲያቀርቡ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ በፖሊሲው ተወስኗል፡፡
12 ይዘትና የማስታወቂያ ተፅእኖ
ማስታወቂያና ስፖንሰር ሽፕ በይዘት ላይ የሚፈጥሩትን ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ ተፅዕኖ ለመከላከል ልዩ ልዩ የፖሊሲና የህግ ውሳኔዎች ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡
በዚህ ረገድ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃንን ስናይ አብዛኛውን ጊዜ የሚተዳደሩት በሕዝብ ገንዘብ ሲሆን፤ ፕሮግራሞቹ የሚደገፉትም ዜጎች ለተለያዩ አገልግሎቶች በቀጥታ ወይም በግብር መልክ ከሚከፍሉት ክፍያና ከማስታወቂያ ገቢ ነው፡፡ በመሆኑም የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ትኩረታቸውን የአድማጭና ተመልካቾችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ወይም ለማሳደግ በሚረዱ ፕሮግራሞች ላይ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይሁንና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት ለአድማጮች መቅረብ ያለባቸውን ፕሮግራሞች በማጠፍ ማስታወቂያና ስፖንሰርሽፕ በሚያስገኙ ፕሮግራሞች ላይ የሚታጠሩበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡
በተመሳሳይም የንግድ መገናኛ ብዙሃን ገቢያቸውን የሚያመነጩት ከማስታወቂያና ከስፖንሰርሽፕ ክፍያ በመሆኑ የፕሮግራም ትኩረታቸው የሚወሰነው ፕሮግራሞቹ በሚያስገኙት አድማጭ ተመልካችና የማስታወቂያ አስነጋሪዎች ድርሻ ነው፡፡ የንግድ መገናኛ ብዙሃን ከተዳከሙ ክፍያ ለሚሰጣቸውና ስፖንሰር ለሚያደርጋቸው የንግድ ድርጅት ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ተፅዕኖ እንዲጋለጡ በማድረግ የነሱን አላማ ለማስፈጸም በሚያተኩር ዘገባ ላይ እንዲጠመዱ ጫና ሊፈጥርባቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም የዚህን ተፅዕኖ ለማቃለል ፖሊሲው የሚከተሉትን የፖሊሲ ውሳኔዎች አስቀምጧል፡-
⮚ ሁሉም የሕዝብ፣ የንግድና የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን በፍትሃዊነት ከመንግስት የማስታወቂያ በጀት ተጠቃሚና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የመንግስት ተቋማት የማስታወቂያ በጀት ክፍፍል ግልፅ የአሰራር ስርአት ሊዘረጋለት እንደሚገባና የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል በየዓመቱ የሚያከናውነው የመገናኛ ብዙሃን ተደራሲያን ድርሻ የጥናት ውጤት አንዱ የመንግስት የማስታወቂያ ገቢ ማከፋፈያ መስፈርት ሆኖ ሊያገለግል እንደመሚችል፤
⮚ የንግድ መገናኛ ብዙሃን ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን የመገናኛ ብዙሃንን ኤዲቶሪያል ነጻነትና የጋዜጠኝነት ሙያ የብቃት ደረጃ መመዘኛ ወይም ስታንዳርድ ለድርድር ሳያቀርቡ የሕዝብን የመረጃ ፍላጎት ለማርካት ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም ኢኮኖሚያቸውን በቋሚነት ለማሳደግ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው፤ እና
⮚ መንግስትም ለንግድ መገናኛ ብዙሃኑ የፋይናንስና ሌሎች የአቅም ማሳደጊያ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ናቸው፡፡
ከዚህ ጎን ለጎንም በማስታወቂያ አስነጋሪዎች የሚተላለፉ የምርትና አገልግሎት የንግድ ማስታወቂያዎች የህጻናትንና የወጣቶችን ጤንነትና ደህንነት የሚነካ፣ አገራዊ ባህልና እሴትን የሚሸረሽር፣ የአልኮል መጠጦችን የሚያስተዋውቅ፣ የተዛባ የፆታ ውክልናን የያዙ እንዲሁም ሌሎች ሕግን የሚተላለፉ መልዕእክቶችን ማሰራጨት በሕግ ሊከለከል እንደሚገባ በፖሊሲው ተመላካቷል፡፡
13 የሕዝብና የንግድ መገናኛ ብዙሃን ፍትሃዊ ውድድር
በመገናኛ ብዙሃን በካከል ፍትሃዊ ውድድርን የሚያሰፍኑ አሰራሮችን መከተል አስፈላጊ ነው፡፡ እንደ ፖሊሲው ጥናት ከሆነ በሕዝብና በንግድ መገናኛ ብዙሃን መካከል ፍትሀዊ ውድድር አለመዘርጋቱን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ለአብነት ያህልም በማስታወቂያ አዋጁ ለሕዝብም ሆነ ለንግድ ብሮድካስተሮች የተመደበው የማስታወቂያ ጊዜ ምጣኔ ከጠቅላላ የሥርጭት ጊዜው እኩል 20 በመቶ ሲሆን፤ በጋዜጣና መፅሄትም እኩል 60 በመቶ ነው፡፡ በሌላም በኩል አብዛኛዎቹ የመንግስት ተቋማት የማስታወቂያ በጀት የሚከፋፈለው ለሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ነው፡፡ በመንግስት የአገልግሎት ግዥ ሕግና መመሪያም የማስታወቂያና የስፖንሰርሽፕ አገልግሎትን በቀጥታ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን መስጠት የሚፈቀድ ሲሆን፤ የመንግስት ወጪን ከመቆጠብ ጋር በተያያዘም ለንግድ መገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያና ስፖንሰር መስጠት ይከለከላል፡፡ በተጨማሪም የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን በመንግስት የሚደጎሙ ሲሆን፤ የንግድ የመገናኛ ብዙሃን ግን አይደጎሙም፡፡ ይህ መሆኑም በሕገ መንግስቱ ፕሬስ ጥበቃ ይደረግለታል የሚለውን ድንጋጌ ሊቃረን እንዲሁም የግል መገናኛ ብዙሃንን ቀጣይነት በማዳከም ከገበያ ሊያስወጣ እና በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ ሊያዳክም ይችላል፡፡
በመሆኑም ፖሊሲው በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች ፍትሀዊ የሆነ የውድድር ስርአት እንዲጠናከር እንደሚደረግ፤ በሕዝብና በንግድ መገናኛ ብዙሃን መካከል ፍትሃዊ ውድድር እንደሚዘረጋ፤ እንዲሁም ለሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ይፈቀድ የነበረው በአንድ ሰአት ውስጥ 12 ደቂቃ የማስታወቂያ ጊዜ ዝቅ እንደሚደረግ እና በጋዜጣና መፅሄትም ለንግድ ወይም ለግል ጋዜጣና መፅሄቶች በአንድ እትም ውስጥ ይፈቀድ የነበረው 60 በመቶ የማስታወቂያ ምጣኔ ወደ 80 በመቶ እንዲያድግ ወስኗል፡፡
14 ማህበራዊ ሚዲያ
ማህበራዊ ሚዲያ የራሱ ጠቀሜታዎች ያሉት የመሆኑን ያህል ህዝብን ለሚጎዳ አላማ በተለይም የጥላቻ ንግግርንና አሳሳች ዜናና መረጃን ለማሰራጨት፣ አመፅና ግጭት ለማነሳሳት፣ ስምን ለማጥፋት ሊውል እንደሚችል ፖሊሲው በጥናቱ አረጋግጧል፡፡
በአገራችን የማህበራዊ ሚዲያን የተመለከተ ራሱን የቻለ የሕግ ማዕቀፍ የሌለ ከመሆኑም ባሻገር ከመደበኛው መገናኛ ብዙሃን በተለየ ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩና የወንጀል ድርጊቶችን የያዙ ሁሉንም ይዘቶች፣ ይዘት አሰራጮችንና ተቀባዮችን ለይቶ ማጣራት ወይም መመርመርና በሕግ ተጠያቂ ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑ በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡ በመሆኑም ፖሊሲው በዚህ ረገድ ሊከናወኑ የሚገባቸውን ልዩ ልዩ ተግባራት አስቀምጧል፡፡ ለአብነት ያህልም፡-
⮚ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ይዘት ታማኝነትንና እውነተኛነትን ለማረጋገጥ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚውን ሕዝብ ስለአጠቃቀሙ ስነምግባርና ልዩ ልዩ መመዘኛዎች ወይም ስታንዳርዶች በማስተማር የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ መፍጠር እንደሚገባ፤
⮚ የማህበራዊ ሚዲያ አዎንታዊ ሚና ተጠቃሚነትን የሚያስተጓጉሉ ይዘቶች ሲኖሩ በተቻለ ፍጥነት እንዲወገዱ ለማድረግ የሚያስችል ስልት መከተል እንደሚያስፈልግ፤ ⮚ በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት በሚሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ላይ የሚታየውን የተዛባ የመረጃ ስርጭት ለመከላከል እንደ መደበኛው መገናኛ ብዙሃን ሁሉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የመገናኛ ብዙሃን ገፅ ባለቤቶች ወይም የመገናኛ ብዙሃን ይዘት አሰራጮች ማንነታቸውን በይፋ እንዲገልጹ የሚያደርግ ሕግ ማውጣት፤ እንዲሁም ⮚ ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ተከታይ አገር በመሆኗ የአለም አቀፍ ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ ስራውን ቀድመው ከጀመሩት ዲሞክራቲክ አገሮች ተሞክሮ በመውሰድና ከአገራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመና አስቻይ የሆነ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የፖሊሲ አቅጣጫ መከተል እንደሚያስፈልግ በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
15 የህትመት መገናኛ ብዙሃን የወደፊት ዕድሎች
የአገራችን የህትመት መገናኛ ብዙሃን ቁጥርም ሆነ ተደራሽነቱ በእጅጉ አናሳ ነው፡፡ ለህትመት መገናኛ ብዙሃን ስርጭት ማነስ እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱት ውስጥ ጋዜጣና መፅሄቶችን ለማሰራጨት የሚያስችል በቂ የማሰራጫ አማራጭ መንገድ አለመኖር፣ የማተሚያ ቤት አለመስፋፋት፣ ለጋዜጣና መፅሄት ህትመት የሚጠየቀው የማተሚያ ዋጋ ከፍተኛ መሆን፣ የህብረተሰቡ የንባብ ባህል አለመዳበር፣ የመረጃ አለማግኘት እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
በመሆኑም መደበኛውን የህትመት መገናኛ ብዙሃን በህትመት ምርት፣ በማሰራጫ ዘዴ እና ቀጣይነቱን በማረጋገጥ ረገድ ለማዘመን የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ሞዴሎችን መመርመር፣ ማጥናትና መተግበር፤ ዘመናዊ፣ ያልተማከለና አስተማማኝ የማተሚያ ቤት ድርጅትና የስርጭት ስርዓት በማቋቋም ተግባራዊ ማድረግ፤ ሁሉም አሳታሚዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በአገሪቱ በሚገኙ ክልሎች የሚዘጋጁ ህትመቶችን በዝቅተኛ ዋጋ ማሳተምና ማሰራጨት እንዲችሉ መደገፍ፤ የጋዜጣና መፅሄት የሥርጭት ሂደትንም በማዘመን በፖስታ ቤትና በሌሎች አማራጭ መንገዶች እንዲሰራጭ ለማድረግ የስርጭት ሂደቱን ዘመናዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
16 የመገናኛ ብዙሃን ድጋፍና የኢንቨስትመንት ማበረታቻ
በፖሊሲው በጥናት ከተለዩ ዋነኛ ችግሮች መካካል አንዱ መገናኛ ብዙሃን ድጋፍና ማበረታቻ ባለማግኘታቸው በማስፋፋትም ሆነ ቀጣይነታቸውን በማረጋገጥ ሂደት እንቅፋት ሲፈጠር የቆየ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ለሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ከሚደረገው አነስተኛ ድጋፍ ባሻገር ለንግድና ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን የሚደረግ ቀጥተኛ የሆነ የመንግስት ድጋፍ የለም፡፡ ስለሆነም መገናኛ ብዙሃን የዜጎችን አስተሳሰብ በማነፅ ዜጎች በአገር ግንባታ እንዲሳተፉ የሚያደርግ በመሆኑ ከማንኛውም ዘርፍ በተሻለ ድጋፍና ማበረታቻ እንደሚያስፈልገው ፖሊሲው እውቅና የሰጠ ሲሆን መገናኛ ብዙሃኑን ለመደገፍም የሚከተሉት እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚገባ የፖሊሲ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
⮚ በመገናኛ ብዙሃን መሳሪያዎች ላይ የተጣለውን ከፍተኛ የገቢ ቀረጥ መቀነስ፣ በተቻለ መጠን በአገር ውስጥ የሚመረቱበትን ሁኔታም ማመቻቸት፣
⮚ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ፣ መስርያ ቦታ፣ ብድር፣ የውጭ ምንዛሪ ቅድሚያ ዕድል ማመቻቸት፣
⮚ የዜና ወኪሎችን በማጠናከር መገናኛ ብዙሃን ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ፣
⮚ የመንግስት ተቋማት የማስታወቂያና ስፖንሰርሽፕ በጀት በውድድር እንዲከፋፈል ማድረግ፣
⮚ ከበይነ-መረብ ጋር የተሳሰረ ያልተማከለና ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶች በሁሉም ቦታ ተደራሽ የሆነ ብሄራዊ የማተሚያ ቤት ማደራጀት፣
⮚ የማተሚያ ቤት ወጪንና የመሸጫ ዋጋን መደጎም፣ የህትመት ግብአቶች፣ ወረቀትና ሌሎች ለህትመት ሥራ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች በአገር ውስጥ እንዲመረቱ ማድረግ፣ ⮚ በቂ ማተሚያ ቤት መቋቋሙንና የግሉ ዘርፍ መሳተፉን ማረጋገጥ፣ አሳታሚዎችም በግልም ይሁን በጋራ የራሳቸው የማተሚያና የማሰራጫ አውታር እንዲኖራቸው መደገፍ፣
⮚ ጋዜጣና መፅሄት በፖስታ ቤትና በመሰል አማራጭ ቴክኖሎጂዎች ታግዞ እንዲሰራጭ ማድረግ፣
⮚ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መሳሪያዎች፣ የህትመት ግብአቶችና አገልግልቶች ላይ የተጣለውን ግብርና ታክስ በጥናት በመመስረት መቀነስ፣ የእፎይታ ጊዜ መስጠት፣
⮚ መገናኛ ብዙሃንን ለማስፋፋት፣ ለመደገፍና ቀጣይነታቸውን ለማረጋገጥ በፋይናንስና በቴክኒክ የሚደገፉበትን አሰራር መዘርጋት፤ እንዲሁም
⮚ የድጋፍ ፈንድ በማቋቋም ወይም በተቆጣጣሪ አካሉ በኩል የድጋፍ ስራ ማከናወን ናቸው፡፡
17 የመገናኛ ብዙሃን ራስን በራስ ስለመምራት እና የጋዜጠኞች ማህበራት በበርካታ አገራት እንደሚሰራበት ሁሉ በአገራችንም መገናኛ ብዙሃን የራሳቸውን ምክር ቤት በማቋቋም ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይሁንና በአሁን ጊዜ በአገራችን የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የተቋቋመ ቢሆንም መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን በራሳቸው የሚመሩበትና የሚቆጣጠሩበት ደረጃ ላይ አልደረሱም፡፡
ስለሆነም የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤቱን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን በራሳቸው የሚመሩበትና የሚቆጣጠሩበትን ስልት መቀየስ እንደሚያስፈልግ፤ እንዲሁም ምክር ቤቱ የራሱን የሙያና የስነ ምግባር ደንብና ኤዲቶሪያል የብቃት ደረጃ መመሪያ ወይም ስታንዳርድ በማውጣት የመገናኛ ብዙሃን ኤዲተሮችና ጋዜጠኞችን አቅም መገንባት፣ ዜጎች፣ ድርጅቶችና የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀርቧቸውን ቅሬታዎችና አቤቱታዎች በሙያዊ ሥነ ምግባር ላይ ተመስርቶ በገለልተኝነትና በታማኝነት መመርመር ወዘተ እንደለበት በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሁሉንም ዓይነት የጋዜጠኛ ማህበራትን አጠቃሎ የሚያሰባስብ አንድ አገራዊ የጋዜጠኖች ማህበር መቋቋም እንዳለበትና የሚቋቋመው አገር አቀፍ የጋዜጠኞች ማህበር ልዩ ልዩ ድጋፍ በማሰባሰብ የአገልግሎት አቅሙን በቀጣይነት እያጠናከረ መጓዝ እንደሚገባው፤ እንዲሁም የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ከተልዕኳቸው አኳያ በተናጠል የሚያደራጁዋቸው የሙያ ማህበራት ለኤዲቶሪያል ነጻነት ጥብቅና በመቆም፣ የማህበሩን አባላት ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች በማስጠበቅ፣ የሙያ ብቃት ደረጃ መመዘኛ ወይም ስታንዳርድ አውጥቶ በመተግበር፣ የጋራ ትብብርን በማሳደግ እና በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የወጡ መመሪያዎችንና ስታንዳርዶችን ለመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በማሳወቅ ሰፊ ሚና ያላቸው በመሆኑ መበረታታት እንዳለባቸው፤ በተመሳሳይም ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት የሚደግፉ የሙያና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲቋቋሙ እንደሚደረግ በፖሊሲው ተወስኗል፡፡
18 የጋዜጠኞች ደህንነትና ጥበቃ
ፖሊሲውን ለማዘጋጀት በተካሄደው ጥናት መሰረት የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት ፕሬስ በተቋምነቱ የሕግ ጥበቃ እንደሚደረግለትና የሙያ ነጻነቱም እንደሚከበርና በልዩ ልዩ ሕጎችም ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት የተረጋገጠ ቢሆንም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች ነፃነት ተገድቦ ቆይቷል፡፡
ስለሆነም በፖሊሲው የጋዜጠኞችን የስራ ነጻነት የሚያደናቅፉ፣ አደጋ ላይ የሚጥሉና ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ የመገናኛ ብዙሃንና ሌሎች የሕግ ማዕቀፎች እንደገና መፈተሽና መሻሻል እንዳለባቸው፤ በመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና በጋዜጠኞች የአሰራር ነጻነት ላይ የሚከሰት ጣልቃ ገብነትንና ተፅዕኖን ለመከላከል ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ጋዜጠኞች መብትና ደህንነት ሕጋዊ ጥበቃ ወይም ከለላ መደረግ እንዳለበት፤ በአንፃሩም ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን አካላት የአገርንና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይጥሉ የተጠያቂነት አሰራር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አካቷል፡፡
19 የጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር እና የብቃት ደረጃ መመዘኛ ወይም ስታንዳርድ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን በአመዛኙ የሙያ ስነ ምግባርን በማክበርና የፕሮግራም ደረጃ መመዘኛዎችን ወይም ስታንዳርድን ጠብቆ በመስራት በኩል ሰፊ ውስንነት የሚታይበት መሆኑን ለፖሊሲ ዝግጅት የተካሄደው ጥናት አሳይቷል፡፡ በመሆኑም ፖሊሲው መገናኛ ብዙሃን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ እራስን በራስ መቆጣጠር የሚያስችል የጋዜጠኝነት የሙያ ስነ ምግባርና የፕሮግራም ይዘት ስታንዳርድ በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስቀምጥ ሲሆን፤ ሁሉም ይዘቶች የሚቀርቡበት የራሳቸው የሙያ ብቃት ደረጃ መመዘኛ ወይም ስታንዳርድ ሊኖራቸው እንደሚገባ እንዲሁም የዘገባና የአሰራር መመሪያ በማዘጋጀትና የማስፈፀም አቅምን በመገንባት በዚህ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችንና ክፍተቶችን መፍታት እንደሚያስፈልግ በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
20 የዜና አገልግሎት
መገናኛ ብዙሃንና የኮሙዩኒኬሽን ልማት ያለጠንካራና ታማኝ የዜና ምንጭ ተቋም የሚታሰብ አይደለም። አሁን ባለዉ ሁኔታ በአገራችን የሕዝብ የዜና አገልግሎት በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑ በፖሊሲው ተመላክቷል፡፡
በመሆኑም፡-
⮚ በመገናኛ ብዙሃንና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ የአገሪቱን የዜና አገልግሎት አሰራር፣ አደረጃጀት፣ አመራርና ፈጻሚ አቅም፣ ቴክኖሎጂና ግብአት ዘመኑ ከደረሰበት የዜና አገልግሎት እድገት ደረጃ ማድረስ እንደሚገባ፤
⮚ አገሪቷ አሁን ከደረሰችበት የእድገት ደረጃና እያደገ ከመጣው የህዝብ የመረጃ ፍላጎትና አለም አቀፋዊው የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፈጣንና ተለዋዋጭ እድገት አንፃር የተቃኘ ወቅታዊና ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ የሚንቀሳቀስ የህዝብ ዜና አገልግሎት ተቋም መገንባት የመንግስት የፖሊሲ ትኩረት መሆኑን፤ እንዲሁም
⮚ አማራጭ የግል የዜና አገልግሎቶች የሚስፋፉበትንና የሚጠናከሩበትንም አቅጣጫ መቀየስ አስፈላጊ መሆኑን ፖሊው አመላክቷል፡፡
21 የአቅም ግንባታ ስራዎች
የአገራችን መገናኛ ብዙሃን ለማህበራዊ፣ ለኢኮኖሚያዊና ለፖለቲካዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ማበርከት በሚያስችል ሁኔታ ብዝሃነቱን፣ ጥራቱን እና ተደራሽነቱን ጠብቆ አልተስፋፋም፡፡ ስለሆነም የመገናኛ ብዙሃን ዘርፉን ሁለንተናዊ አቅም በቀጣይነት ከመገንባት አንጻር፡-
⮚ በቴክኖሎጂና በሰው ሀይል አቅም ግንባታ በመንግስት የሚደገፉና የራሳቸው ጠንካራ አደረጃጀት ያላቸው የማሰልጠኛ ተቋሞችን በማቋቋም በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የረጅምና የአጭር ጊዜ የስራ ላይ ስልጠናዎች በመስጠት የጋዜጠኞችን ሙያና ክህሎት ማሳደግ፤
⮚ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ከክልልና ከአካባቢ ማህበረሰብ ጋር ትስስር በመፍጠር የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ማዳረስና አቅም መገንባት፤ እንዲሁም
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካሉ በዚህ ረገድ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ መደረግ እንዳለበት በፖሊሲው ተቀምጧል፡፡
22 የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል
አገራት የመገናኛ ብዙሃን ፈቃድ ሰጪና ሬጉላቶሪ አካል የሚያቋቁሙ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለአብነት ያህል በደቡብ አፍሪካ Independent Communications Authority of South Africa፣ ኬንያ Communications Commission of Kenya (CCK)፣ በዩናይትድ ኪንግደም Office of Communication (OFCOM)፣ በአሜሪካ Federal Communications Commission (FCC)፣ በካናዳ Canadian Radio-television and Telecommunications Commission (CRTC)፣ በአውስትራሊያ Australian Communication and Media Authority (ACMA) ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል አደረጃጀትን በተመለከተም ገለልተኛነቱ የተረጋገጠ ሆኖ ከልዩ ልዩ የማህበረሰብ አካላት የተውጣጣ ቦርድ እና ለሙያው ብቁ የሆነ አመራር እንዲኖረው እና ተጠሪነቱም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን ይደረጋል፡፡
በመሆኑም ፖሊሲው የልዩ ልዩ አገራትን ተሞክሮና አሰራር መሰረት በማድረግ የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል በሕግ የሚቋቋም መሆኑን፤ አደረጃጀትን በተመለከተም ገለልተኛነቱ የተረጋገጠ ሆኖ ከልዩ ልዩ የማህበረሰብ አካላት የተውጣጣ ቦርድ እና ለሙያው ብቁ የሆነ አመራር እንደሚኖረው፤ እና ተጠሪነቱም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሆን፤ የሚጠበቅበትን አላማ ከግብ ለማድረስም ተግባርና ኃላፊነቱ መሻሻል እንዳለበትና የሰው ኃይል፣ የፋይናንስና የቴክኒክ አቅሙም ሊገነባ እንደሚገባ እንዲሁም ሕገ መንግስቱን የሚተላለፍ የመገናኛ ብዙሃን ሲኖርም በሕግ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት በግልፅ አስቀምጧል፡፡
III. የመገናኛ ብዙሃን የፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች
የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ በክፍል ሦስት ስር በእያንዳንዳዱ የሕትመት፣ የብሮድካስትና፣ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ካለው የግል የሥራና አሠራር ባህሪ አንፃር በተናጠል ሊተገበር የሚገባውን የማስፈፀሚያ ስትራቴጂ አካቶ ቀርቧል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
1. የሕትመት መገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች
የሕትመት መገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች ዋና መርህ ፈርጀ ብዙ የህትመት ውጤት መጎልበት እና የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት መረጋገጥ ወሳኝ ነው በሚል መርህ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ተፈፃሚነቱም በጋዜጣ፣ በመጽሄት ህትመት እና በበይነ-መረብ አማካኝነት በሚቀርብ ጋዜጣ እና መጽሄት ላይ መሆኑን በማብራራት የሕዝብ፣ የንግድና የማህበረሰብ የህትመት መገናኛ ብዙሃንን ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች በዝርዝር አስቀምጧል፡፡
ሀ. በመንግስት የሚተዳደሩ ጋዜጦችና መፅሄቶች
⮚ በመንግስት ባለቤትነት ስር ያሉ አገር አቀፍ ጋዜጦችና መፅሄቶች ሁሉንም የአገሪቱ ክፍሎች መሸፈን እና ለሁሉም ሕዝቦች መሰራጨት እንዳለባቸው፤
⮚ የመንግስት ጋዜጦችና መጽሄቶች ነጻና ገለልተኛ የሕዝብ አገልግሎት ህትመት መገናኛ ብዙሃን መሆን እንዳለባቸው፤
⮚ አገር አቀፍ የመንግስት ጋዜጣና መፅሄት ለአገር አቀፍ እትም የጽሁፍ ዝግጅት የሚውል ግብአት ለማግኘት እንዲረዳ በክልል ደረጃ ካሉ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጋር በመተባበር መስራት እንዳለባቸው፤ በፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂነት ውስጥ ተካተዋል፡፡
ለ. የንግድ ጋዜጦችና መፅሄቶች
⮚ የግልና የንግድ ጋዜጦችና መፅሄቶች በተቀመጠው አገራዊ የምዝገባ ስርዓት መሰረት ተመዝግበው ወደ ሥራ መግባት እንዳለባቸው፤
⮚ የንግድ ፈቃድ በማውጣት ግብር መክፈል እንዳለባቸው፤
⮚ የንግድ ጋዜጦችና መፅሄቶች ሁሉንም የአገሪቱን ክፍሎች እንዲሸፍኑ ከክልል እና ከአካባቢ መገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር በህትመት እና በስርጭት ሂደት ግብአቶችን በመለዋወጥ በጋራ እንዲሰሩ ድጋፍ መደረግ እንደሚገባ በፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂነት ውስጥ ተካተዋል፡፡
ሐ. የማህበረሰብ ጋዜጦችና መፅሄቶች
⮚ ለትርፍ ያልተቋቋሙ አነስተኛ የአካባቢ ወይም የማህበረሰብ ጋዜጦችና መፅሄቶች መበረታታት እንዳለባቸው በፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂነት ውስጥ ተካቷል፡፡
2 የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች
የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች የብሮድካስት አገልግት ሠጪዎች መላውን ሕዝብ የመረጃ ተደራሽ የማድረግ፣ የማስተማር፣ የማሳወቅና ለአገሪቱ ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፤ ተፈፃሚነቱም ከምድር ወደ አየር ወይም በሳተላይት ወይም በኬብል በሚሰራጭ ብሮድካስት እና በኢትዮጵያ ሉአላዊ ክልል ውስጥ ባሉ ሌሎች የማሰራጫ መንገዶች ላይ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የጋራ የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች፡-
⮚ የሕዝብ፣ የንግድ ወይም የማህበረሰብ ብሮድካስት አገልግሎት ሰጪዎች ለሕዝብ መረጃ ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ቅድሚያ መስጠት፤
⮚ መንግስትም ለዘርፉ ተገቢውን የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረግ፤
⮚ ብሮድካስተሮች የሕዝብ ንብረት የሆኑ የማሰራጫ አውታሮችን፣ የአንቴና ምሰሶ እና መሰል መሰረተ ልማቶችን በመጠቀም ይዘታቸውን ማሰራጨት እንዲችሉ ድጋፍ ማድረግና የመገናኛ ብዙሃን መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፤
⮚ መንግስት የብሮድካስት አገልግሎቶችን ለመምራት የሚያስችሉ ሕጎችን በማውጣት፣ በሕገ መንግስቱ ድንጋጌ መሰረት የኢዲቶሪያል ነጻነትና ዋስትናቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ማድረግ፤ ⮚ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የሕዝብ ብሮድካስተር ጨምሮ የክልል ብሮድካስተሮች በአደረጃጀት እና በኤዲቶሪያል ነፃነታቸውን ጠብቀው ህዝባዊ አገልግሎት መስጠት፤
⮚ የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል ከሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመመካከር ለብሮድካስት ስርጭት የሚውል አጠቃላይ አገር አቀፍ የሬዲዮ ሞገድ ድልድልና አጠቃቀም እቅድ ማዘጋጀት፤
⮚ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ የብሮድካስት የሬዲዮ ሞገዶች ምደባ ከአለም አቀፍ የቴሌኮምዩኒኬሽን ህብረት እና ከሌሎች ተገቢነት ካላቸው ክልላዊ እና አለም አቀፋዊ አካላቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ መፈፀም፤
⮚ ለሕዝብ፣ ለንግድና ለማህበረሰብ ብሮድካስተሮች የሚዘጋጀው የሬዲዮ ሞገድ ምደባ እና የፈቃድ መስፈርት በግልፅና በዝርዝር የሚወስንና የኢዲቶሪያል ይዘትን በተመለከተም አጠቃላይ መመሪያን የያዘ መሆን፤
⮚ በተቆጣጣሪ አካሉ ቀላል፣ ግልጽና ፍትሃዊ የፈቃድ አሰጣጥ ሥርአት መዘርጋት፤ ⮚ የብሮድካስት ፈቃድ ለማግኘት በሚዘጋጀው መስፈርት ውስጥም የተወሰነ መቶኛ በአገር ውስጥ ለተዘጋጁ ይዘቶች ትኩረት የሚሰጥ አስገዳጅ መስፈርት ማካተት፤
⮚ ልዩ ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ህጻናትን፤ ወጣቶችን፤ ሴቶችን እና አካባቢን የሚመለከቱ ፕሮግራሞችን በመስፈርቱ ማካተት፤
⮚ ራሱን የቻለ የተለየ የትምህርት እና የሙያ፣ የዜና፣ የልጆች፣ የመዝናኛ ወይም የሃይማኖት ፕሮግራም ለማሰራጨትም የብሮድካስት ፈቃድ መስጠትን፤ ያካተተ ሲሆን ⮚ ከዚህ በተጨማሪም የጋራ የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
ሀ. የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎት
⮚ የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎት በአገር አቀፍ ወይም በክልል የሚቋቋም ሆኖ ነጻነቱና ገለልተኛነቱ የተጠበቀ፣ በመንግስትና በራሱ ገቢ የሚተዳደር ይሆናል፡፡ የቦርድ አመራሩ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተውጣጡና በፌዴራል ወይም በክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚሾሙ ነጻና ገለልተኛ አካላት የሚመራ ይሆናል፡፡
⮚ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ለፕሮግራም ልውውጥ እና አገራዊ ፕሮግራም በቂ ሽፋን እንዲሰጥ፣ መረጃን በጥራትና በወቅቱ ተደራሽ እንዲያደርግ፣ አገራዊ አንድነትን እንዲያጠናክር፣ ወጪ ቆጣቢ አሰራርን እንዲከተል በሚያስችል መልኩ እንዲመራ ይደረጋል፡፡
⮚ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ለአካባቢ የማህበረሰብ ብሮድካስተሮች የይዘት፣ የባለሙያ፣ የመሳሪያና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለማህበረሰቡ የመረጃ ተደራሽነት የበኩላቸውን ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል፡፡
⮚ ከውጭ አገር መገናኛ ብዙሃን ጋር መሰል የፕሮግራም ልውውጥ ቢደረግ የባህል፣ ቱሪዝምና፣ ኢንቨስትመንት ዘርፍን የሚያበረታታ ይሆናል፡፡
⮚ አገር አቀፍ የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎት በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ከአጠቃላይ የአየር ሰአቱ ውስጥ ቢያንስ 80 በመቶውን አገር ውስጥ ለተዘጋጁ ይዘቶች ማዋል ይኖርበታል፡፡
⮚ የክልል የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎት በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ከአጠቃላይ የአየር ሰአቱ ውስጥ 70 በመቶውን ክልሉን ለሚመለከቱ ፕሮግራሞች፤ ቀሪውን የሥርጭት ጊዜ ለአገራዊና ሌሎች ፕሮግራሞች ማዋል ይኖርበታል፡፡
⮚ አገር አቀፍ እና የክልል የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎቶች ለአገራዊ አንድነትና ሰላም መስፈን የሚረዱ የተለያዩ ይዘቶችን በማቅረብ ህብረተሰቡን ማስተማር አለባቸው፡፡
⮚ አገር አቀፍ የህዝብ ብሮድካስት አገልግሎት የመረጃ ተደራሽ ላልሆኑና በገጠሪቷ የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ማህበረሰቦች መረጃን ተደራሽ ለማድረግ የስርጭት ሽፋኑን ማስፋት አለበት፡፡
⮚ አገር አቀፍም ሆነ የክልል የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎቶች የአገር ውስጥ የይዘት ምርት አቅምን እና የሃሳብ ብዝሀነትን ለማሳደግ ለተባባሪ ፕሮግራም አዘጋጆች በመገናኛ ብዙሃን ተሳታፊ እንዲሆኑ፤ የፕሮዳክሽን መሳሪያዎችን ተከራይተው ይዘት ለሚያዘጋጁ የግል ፕሮግራም አዘጋጆችም ድጋፍ ማድረግ እንደላባቸው ተካቷል፡፡
ለ. የንግድ ብሮድካስት አገልግሎት
⮚ የንግድ ብሮድካስተሮች ነፃነታቸው የተጠበቁ የንግድ ድርጅቶች በመሆን አገልግሎት መስጠት አለባቸው፡፡
⮚ የንግድ ብሮድካስተሮች በተሰጣቸው ፈቃድ ውስጥ የተጠቀሱትን የሕዝብ አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች ማክበር አለባቸው፡፡
⮚ የንግድ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከአጠቃላይ የአየር ሰዓታቸው ውስጥ 60 በመቶውን ፈቃድ የወሰዱበት አካባቢን ለሚመለከቱ ፕሮግራሞች፤ ቀሪውን የሥርጭት ጊዜ ለአገራዊ፣ ክልላዊና ሌሎች ፕሮግራሞች ማዋል ይኖርባቸዋል፡፡
⮚ አገልግሎታቸውን በክፍያ የሚያቀርቡ ብሮድካስተሮች ከቻናሎቻቸው ውስጥ ቢያንስ ሁለት አገራዊ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃንን ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡
⮚ ትኩረታቸውን በገጠር አካባቢዎች ላደረጉ ወይም በክልልና በአካባቢ ደረጃ ለሚቋቋሙ፣ ወይም ግጭትን በማስወገድ በሰላም ዙሪያ ለሚሰሩ፣ ትምህርታዊና እና ማህበራዊ ልማትን የሚያጎለብቱ ፕሮግራሞችን የሚያሰራጩ የንግድ ብሮድካስተሮች ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸውና ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተካቷል፡፡
ሐ. የማህበረሰብ ብሮድካስት አገልግሎት
⮚ የማህበረሰብ ብሮድካስተሮች ዲሞክራሲን፣ የማህበረሰቡን ዕውቀት፣ ባህል፣ ልምድ፣ ማህበራዊ ልማት፣ የእርስ በእርስ መስተጋብር፣ ሰላም እና መግባባትን የሚያጠናክሩ መሳሪያዎች በመሆን በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ሊቋቋሙ ይገባል፡፡ በተለይ የመገናኛ ብዙሃን በሌለባቸው፣ በኢኮኖሚ በጣም ዝቅተኛ በሆኑ እና የተለያዩ ችግሮች ባሉባቸው አካባቢዎች የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን እንዲቋቋም ትልቅ ድጋፍ ይደረጋል፡፡
⮚ የማህበረሰብ ብሮድካስተሮች ለትርፍ ያልተቋቋሙና በማህበረሰቡ የሚተዳደሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ይዘትን በተመለከተ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ማህበራዊ፣ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ቡድኖችን የሚያካትት፤ ለማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወገንተኛ ያልሆነ፣ ከማንኛውም የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሀይማኖታዊ ወይም ከአገራዊ፣ ክልላዊ፣ አካባቢያዊ እና ባህላዊ ተፅእኖ ተቋም ነጻ መሆን አለባቸው፡፡
⮚ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን በአካባቢው ያሉ ሁሉንም ቋንቋዎች ወይም ማህበራዊ ቡድኖች ፍላጎት እንዲያሟላ እና በተቻለ አቅም ማህበረሰቡ በአስተዳደር፣ በይዘት ዝግጅትና በፋይናንስ እንዲሳተፍ ጥረት ይደረጋል፡፡
⮚ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች የፕሮግራሙን 70 በመቶ አካባቢውን ለሚመለከቱ ወይም በሌላ በተመሳሳይ የማህበረሰብ ብሮድካስት ለተዘጋጁ እና ስለማህበረሰቡ ጉዳይ ለሚያተኩሩ ፕሮግራሞች ማዋል አለበት፡፡ ቀሪው የሥርጭት ጊዜ ክልላዊ ወይም አገራዊ ዜና፣ ወቅታዊ ጉዳይ ወይም የተለየ አርዕስተ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ፕሮግራም ሊሆን ይችላል፡፡
⮚ የማህበረሰብ ብሮድካስት ጣቢያዎች ገቢያቸውን ከማስታወቂያና ከሌሎች ልዩ ልዩ ምንጮች በማሰባሰብ ቀጣይነታቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
⮚ የማህበረሰብ ብሮድካስት ሲቋቋም በመክፈቻው ምዕራፍ እንዲሁም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ለጣቢያው ማጠናከሪያ የሚሆን ድጋፍ ከንግድ መገናኛ ብዙሃን ከተሰበሰበ የአገልግሎት ክፍያና በመንግስት ከሚመደብ አመታዊ የድጋፍ በጀት ተውጣጥቶ ሊደገፉ የሚገባ ሲሆን፣ የድጋፍ በጀቱም በመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካሉ በኩል ሊከፋፈል ይችላል፡፡
⮚ የማህበረሰብ ብሮድካስተሮች የማህበረሰቡ የመረጃ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ማረጋገጫ መሳሪያ በመሆናቸው ለቀጣይነታቸው እና ለውጤታማነታቸው ሁሉን አቀፍ የቦታና የመሳሪያ አቅርቦት፣ የገንዘብ፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ አመራርና አደረጃጀታቸውም በማህበረሰቡ በራሱ የሚመራ መሆኑን ፖሊሰው አካቷል፡፡
3 የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ሚዲያ ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ሚዲያ በመደበኛው የብሮድካስት እና የህትመት መገናኛ ብዙሃን ስርጭት ላይ በአንድ በኩል መልካም የሚባሉ አጋጣሚዎችን፤ በሌላ በኩልም ተግዳሮቶችን ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም መልካም አጋጣሚዎቹን ለማስፋትና ተግዳሮቶቹን ለመቀነስ የፖሊሲው የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡-
⮚ የኢትዮጵያ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጪዎች ገቢ በሚያስገኝ ስራ ላይ ከተሰማሩ በንግድ ቢሮ እና በግብር ሰብሳቢ አካላት መመዝገብ ያለባቸው ሲሆን፤ ከመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካልም ፈቃድና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አባል በመሆን የምክር ቤቱን አሰራርና መመሪያ ተከትለው ሊሰሩና ሊተዳደሩ ይችላሉ፡፡
⮚ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን እና ማህበራዊ ሚዲያው የጋዜጣና መፅሄት ይዘት በማሠራጨት ሥራ ላይ ከተሰማራ መደበኛው ጋዜጣና መፅሄት በሚመራበት የሙያ ስነ ምግባርና ሕግ የሚመራ ይሆናል፣
⮚ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን እና ማህበራዊ ሚዲያው የሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም በማሠራጨት ስራ ላይ የተሰማራ ከሆነም መደበኛ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ብሮድካስተሮች በሚመሩበት ሕግ እና ደንብ የሚመራ ይሆናል፡፡
⮚ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና ኦንላይን ሚዲያ አገልግሎቶች ተለይቶ በሚወጣ የሙያ ስነ ምግባር ደንብ፣ የብቃት ደረጃ መመዘኛ ወይም ስታንዳርድና ሕጎች እንዲመሩም ይደረጋል፡፡
IV. ፖሊሲውን የማስፈፀም ኃላፊነት
በፖሊሲው ክፍል አራት ፖሊሲውን በማስፈፀም ረገድ በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ድርሻ ያላቸው ቢሆንም፤ በዋናነት በፖሊው አፈፃፀም ረገድ ከፍተኛ ሚና ያላቸውን አካላትንና የእንዳንዱንም ሀላፊነት ፖሊሲው በክፍል አራት ውስጥ ለማስቀመጥ ሞክሯል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
1. የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል፡- የመገናኛ ብዙሃንን በማስፋፋት፣ የአቅም ግንባታ ስራ በማከናወን፣ በመከታተልና በመደገፍ፤
2. የመገናኛ ብዙሃን፡- የመገናኛ ብዙሃንን ሚናና ሕገ መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት በመወጣት፣ ሕዝብን በማገልገል፤
3. የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤትና የጋዜጠኞች የሙያ ማህበራት፡- የዘርፉን እድገት በማረጋገጥ፣ መገናኛ ብዙሃን የሚመሩበትን የስነ ምግባር ደንቦች በማዘጋጀትና በማስተዋወቅ፣ መገናኛ ብዙሃን በሃላፊነት መንሳቀሳቸውን በማረጋገጥ፣ ልዩ ልዩ የድጋፍ ስራዎችን በመስራት፤
4. የትምህርት ተቋማት፡- ጥራቱን የጠበቀ የሰው ኃይል በማፍራት፣ ለዘርፉ ባለሙያዎች ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በመስጠት፤
5. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የፌዴራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ የህዝብ ምክር ቤቶች፡- መገናኛ ብዙሃን የዲሞክራሲ ተቋማት እንደመሆናቸው ለመገናኛ ብዙሃን ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ፣
6. መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፡- ለመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት፤ ለፖሊሲው ተፈፃሚነት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት የሚኖርባቸው መሆኑ በፖሊሲው ተወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሳፖረት አንደኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በታላቅ ስኬት እያከበረ ነው፡፡
ድርጅቱ በላከው የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ ባለፈው አንድ ዓመት በአጭር ጊዜ በጥናት ምርምር ፣ በስልጠና እና ማማከር የሚዲያ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኙ አጋር ተቋማት ጋር አበረታች ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ሚዲያ እድገት እውን የሚሆነው ከየትኛውም የወገንተኝነት ቡድን ነጻ የሆነ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ለሙያዉ እድገት ብቻ ሲበረታ መሆኑን አምነን ወደ ሥራ በመግባታችን ያየናቸዉ አበረታች ሁኔታዎች […]