the-role-of-social-media-in-preventing-hate-speech-in-ethiopia
በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርን በመከላከል ረገድ የማ በራዊ ሚዲያ አዉታሮች ሚና በዮሐንስ እንየው አያሌው <https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1955-the-role-of-social-media-in-preventing-hate-speech-in-ethiopia> “ The evangelists of hate and division are wreaking havoc in our society using social media.” Prime Minister Abiy Ahmed,Nobel Lecture, 11 December 2019 መግቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ በዓይነትምበስፋትምእየጨመረእናእየሰፋ ይገኛል፡፡ለዚህ ደግሞ የሚጠቀሰው አንዱ ምክንያት የማህበራዊ ሚዲያ አዉታሮች በጊዜና በፍጥነት ይዘትን ባለማረማቸው ( absence of effective content moderation) ነው፡፡ይህ ጽሁፍ የተዘጋጀው አዲስ ዘይቤ ሚዲያ ሸንጎ ግሎባል ከተሰኘ ውጥን ጋር በመሆን ነሀሴ 29 ፣ 2012ዓ.ም. በበይነ መረብ አማካኝነት በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ለንግግር መነሻነት የቀረበ ምልከታ ነው፡፡ የዚህ ጽሁፍ ዓላማም የጥላቻ ንግግር ጽንሰ ሃሳቡን በአጭሩ ማብራራት፣ አዲሱ የጥላቻ ንግግር መከላከያ አዋጅ ተስፋና ስጋት ፣ የእኩልነት ፍ / ቤት ወይም ችሎት ማቋቋም አስፈላጊነት ፣ ስለ ይዘት እርማት በዘርፋ ያሉ የሌሎች አገራትን ልምድ ለመጠቆም ፤ እንዴት የሰብዓዊ መብት ተኮር ዘዴ (Human rights based approach) ጠቃሚ እንደሆነ ለማሳየት እና ለወደፊቱ ምን ይደረግ በሚለው ጉዳይ ምክረ ሃሳቦችን መጠቆም ናቸው፡፡ የጥላቻ ንግግር ሰዎች በያዙት ማንነት ( የብሄር፣ጾታ፣ ሃይማኖት ) እንዲገለሉ ፣ እንዲጠሉ ወይም ጥቃት እንዲደርስባቸው የሚያደርግ ንግግር ነው፡፡ የዓለምአቀፉየሲቪልናየፖለቲካመብቶችቃልኪዳን(ICCPR) አንቀጽ 20(1) ላይ አገራት የጦርነት ቅስቀሳ የሚሰብኩ የጥላቻ ንግግሮችን በህግ እንዲከለክሉ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ የተ . መ . ድ . ሰብዓዊ መብት ኮሚቴም ይህንን በተመለከተ በሰጠው ጠቅላላአስተያየትቁ.11/1983 የጦርነት ቅስቀሳ ሲባል ከተ . መ . ድ ቻርተር በተጻረረ መልኩ ማነኛውም ዓይነት አሳሳች ውሸት ( propaganda) ሆኖ ወረራን ወይም ሰላምን የሚያሰጋ ንግግር ነው፡፡









2 አገራችን ኢትዮጵያም የጥላቻ ንግግር ስጋት ለመቀነስ በሚል በ 2012 ዓ . ም . ራሱን የቻል አዋጅ አጽድቃለች፡፡በእርግጥ በህግ መከላከል (legislative intervention) አንዱ መንገድ ቢሆንም ሌሎች ቅጣት አላባ ዜዴዎችን (non-punitive measures) እንደ ይዘት ይታረምልኝ (content moderation) ፣ብዙ ንግግርን በመፍቀድ እና የሚዲያ ትምህርት (media literacy) በተጓዳኝ በመውሰድ መካላከል እንደሚቻል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ 1. የጥላቻ ንግግር ጽንሰ ሳቦች አጭር ምልከታ የጥላቻ ንግግር ሁሉን አቀፍ ትርጓሜ ወይም ብያኔ አልተሰጠውም ለምን ቢባል ጥላቻ ከስሜት የሚመነጭ ጽንሰሃሳብ ነው፡፡የጥላቻ ንግግርን ብያኔ ለመስጠት ከባድ ነው፡፡ ብያኔ ሲሰጠውም እንደየአገራቱ ሁኔታ፣ አውድ እና ምሳሌ ይወሰናል፡፡ለዚህም ይመስላል አንድ የአሜሪካ ፍ / ቤት ዳኛ ስቴዋርት ስለ አስጸያፊ ንግግሮችን (obscenity) በሰጠው የፍርድ አስተያየት እንዲህ ይላል ፦ “የማውቃቸው ፣ ሳያቸው ነው ( “ I know it when I see it .” ) ሲል በጃኮቢሊስ እና ኦሃዮ መካከል በነበረው ክርክር አስፍሯል፡፡የጥላቻ ንግግሮችን ደግሞ ዳኛ ስቴዋርት ካለው በላይ ማንነታቸውን ለማወቅ ከባድ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡ የጥላቻ ንግግር የሰውን ልጅ ክብር እና ኩራት የሚያዋርድ ተግባር ነው፡፡ ፕ / ር ጀረሚ ፡ዋልዶርን ‘The Harm in Hate Speech ’ በሚለው መጽሃፋቸው ላይ የጥላቻ ንግግር የሰውን ልጅ ክብር የሚጎዳ በተለይም ልዩ መገለጫ በመለጠፋ ለምሳሌ የቆዳ ቀለሙ፣ ብሄሩ እና ሃይማኖቱን መሰረት አድርጎ ከማህበረሰቡ ለመንጠል እና ያላቸውን መልካም ገጽታ በማጉደፍ እንደሆነ ይናገራል፡፡ በተለይም የጥላቻ ንግግር በጽሁፍም፣ በምስል ወይም በድምጽ ሲነገር ቢያንስ ሁለት መልዕክትን በህብረተሰቡ ዘንድ ያስተላልፋል፡፡ የመጀመሪያው የጥላቻ ንግግር ተጠቂውን ቡድን ከሰውነት እርከን ያወረደዋል (dehumanise) ብሎም ከሰውነት ተርታ እንዲወርድ ያደርገዋል፡፡ ሌላው ደግሞ በአጥቂ ወገን የራስን ቡድን በስጋት ውስጥ እንዳለ በመቁጠር ሌሎች የቡድኑ አባላት የጥላቻ ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ሊያደርግ ይችላል፡፡ (ጀረሚ፡ዋልዶርን ፡ 2012 ፡ 5) የጥላቻ ትርጉምንም በሚመለከት በ ኔልሰን ማንዴላ ፍውንዴሽን እና አፍሪ ፎረም መካከል በነበረ አንድ ክርክር የደቡብ አፍሪካ የእኩልነት ፍ / ቤት እኤአ በ 2019 ዓ . ም የጥላቻ ንግግርን ለቃሉ በሚሰጠው ሰዋሰዋዊ ትርጉም (grammatical meaning) መተርጎም እንዳለበት አቅጣጫ ጠቁሟል፡፡ Hate speech means a “speech that expresses hatred towards a person or his or her group based on race or other attributes such as religion, sex, ethnicity, sexual orientation and the like.” በዚህም መሰረት የጥላቻ ንግግር ማለት የሌሎችን ሃይማኖትን፣ ጾታን፣ ጎሳን እና መሰል ነግሮችን መሰረት በማድረግ ቡድኖችን እንዲጠሉ ማድረግ ነው ሲል ፍርዱን አስቀምጧል፡፡ (የፍርዱአንቀጽ 94 ይመለከቷል፡፡ )











3 በ ማርክኖርውድእናየእንግሊዝመንግስት መካከል በነበረ ክርክር የእንግሊዝ ብሄራዊ ፓርቲ ቀኝ አክራሪ አስተባባሪ የነበረው ማርክ ፡ ኖሩድ ከመኖሪያ ቤቱ መስኮት ላይ “እስልምና ከእንግሊዝ ይውጣ ፣ የእንግሊዝን ህዝብ እንጠብቅ”/ “Islam out of Britain – Protect the British People የሚል እንዲሁም ከመስከረም 11 የአሜሪካ መንትያ ህንጻ በአሳት መያያዝ የሚገልጽ ብሎም ጨረቃን እና ኮከብን ምስል ላይ የክልከላ ምልክት ያለበት ትልቅ ፖስተር ሰቅሎ” ነበር፡፡ ጉዳዩን የተመለከተው የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ፍ / ቤትም እንዲህ መሰል የቃላትና ምስል ጥላቻ በእንግሊዝ አገር በሚኖሩ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት የሚከፍት ነው ብሎም ሃይማኖቱን ከሽብርተኝነት ጋር ማገናኘት ከአውሮፓ የሰብዓዊ መብት እሴት ጋር የማይሄድ ፣ ማህበራዊ ሰላምን እና መቻቻልን የሚሸረሽር እንደሆነ በፍርዱ አስቀምጧል፡፡ በሌላ ጉዳይም አንድ የደቡብ አፍሪካ እኩልነት ፍ / ቤት ፣ በ አፍሪ ፎረም እና ጁሊየስ ፡ማሌማ መካከል በነበረ ክርክር ተከሳሹ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ህዳጣን ቡድኖች ላይ በደቡብ አፍሪካ የነጻነት ወቅት ሲዘፈኑ ከነበሩ የትግል ዘፈኖች ውስጥ አንድ አዝማች ግጥም መዞ “shoot the Boers/farmers they are rapists/robbers ” “ቦሆርስን / ገበሬዎችን ግደሏቸው ፤ ደፋሪና ዘራፊ ናቸው”፡፡ ፍ / ቤቱም የቀድሞ የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (African National Congress-ANC) አባል የአሁኑ የኢኮኖሚ ነጻነት ታጋይ መሪ ጁሊየስ፡ ማሌማ የዘፈነው ዘፈን የጥላቻ ንግግር ነው በማለት ወስኗል፡፡በተለይም ይህ ንግግር የነጭ ገበሬዎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል አግላይ በመሆኑ በህዝብ በተሰበሰበበትም ሆነ በግል ስፍራ እንዳይዘፈን ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ (የፍርዱአንቀጽ 120 ይመለከቷል፡፡ ) በኢትዮጵያ ታሪክም የጥላቻ ንግግር አዲስ ጽንሰ ሃሳብ አይደለም ፡፡ ለምሳሌ፦ የቆዳ ቀለማቸው ጠቆር ያሉ ሰዎችን በተለምዶው ባሪያ (slave) የሚል አገላለጽ ነበር፡፡ (ተሻለ፡ጥበቡ ፡ 1995 ፡ 58) አጼ ሃ / ስላሴ ጀምሮ በተከታታይ የመጡ መንግስታትም ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ፖለቲካዊ ፍረጃ በማድረጋቸው የጥላቻ ንግግር እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል፡፡ በዘመነ ኢሕአዴግ ጠባብ፣ ትምክህተኛ እና ነፍጠኛ የሚሉ ቃላትን በተለያዩ አጋጣሚዎች የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር ሲናገሩ ተስተዉሏል፡፡ ( ዉብሸት፡ሙላት ፡ 2016) ለምሳሌ ፦ ነፋጠኛ የሚለው ቃል በቅርቡ ለደረሱ ጥቃቶች እንደ ኅቡዕየፖለቲካማጥቂያቃል (dog whistle call) እንደዋለ መረዳት ይቻላል፡፡ የኢፌዴሪ ህገ መንግስቱ ከመጣ ጀምሮ ፤ የጎሳ ፌዴራሊዝም የአገሪቱ ፖለቲካዊ ርዕዮት ሆኖ በመተከሉ ምክንያት ፣ ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ክልሎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ቢያጎናጽፍም ፤ ጎሳ ላይ ማጠንጠኑ በአንድ ክልል ውስጥ አንድ ብሄር የበላይ ሌላው የበታችነት እንዲሰማው በማድረጉ የአገሪቱ ጥንተ አብሶ (original sin) እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ (ዮናታን፡ተስፋየ፡ 2016 ፡ 232) በዚህ ረገድ የህገ መንግስቱን ህጽጽ ፕ / ር ምናሴ፡ሃይሌ እንደሚከተለው ተመልክቶታል፡፡ “የኢፌዴሪ ህገ መንግስት የሶቬት ሞዴል ፌደሬሽን በመከተሉ ዘጠኝ የጎሳ ክልሎችን (tribal homelands) ፈጥሯል፡፡” ይህም በመሆኑ ፣ ጎሰኝነት (ethnicity) በጣም ከመጠን በላይ ፓለቲካዊነት ስለተላበሰ እያንዳንዱ ጎሳ በሚኖርበት ክልል የበላይነት ስሜት እንዲኖር፤ ፍጹም የሃብት ባለቤትነት (exclusive ownership of








About AuthorYohannes Eneyew Ayalew
Monash University
Department MemberCurrently, I’m a doctoral researcher at the Faculty of Law, Monash University in Australia. Prior to joining Monash Law, I was a lecturer in law at School of Law, Bahir Dar University where I was teaching and researching on media law and human right … more
Hate Speech and Fake News In Ethiopia
ገጽ 1 የአውሮፓ የሰላም ተቋም | የውሸት ዜና የተሳሳተ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ፡ የተጋላጭነት ግምገማ 1የውሸት ዜና የተሳሳተ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ: የተጋላጭነት ግምገማ ኤፕሪል 12 ቀን 2021 ገጽ 2 የአውሮፓ የሰላም ተቋም | የውሸት ዜና የተሳሳተ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ፡ የተጋላጭነት ግምገማ 2ይዘቶችዋንኛው ማጠቃለያ ………………………………………… …………………………………………. ………………………………….. 3መግቢያ …………………………………………. …………………………………………. …………………………………………. […]