Skip to content
  • Ethiopian Mass Media Action | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት

May 16, 2022
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት

Search Field


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • News

Advertisements opportunity in Amhara and Benishanguel Gumuze Region (ARMA media production) ለማስታወቂያ የጣቢያዎች ዝርዝር የፕሮግራም ዓይነት

Ethiopian Mass Media Action (EMMA) give training for Ethiopian journalists

  • News

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛአዋጅ

Ayele Addis January 9, 2022

አዋጅ ቁጥር 274/2013 ዓ/ም

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛአዋጅ

የሚዲያ አገልግሎት ህዝብና መንግሥትን በማገናኘት ሠላምን፣ የልማት ተሳትፎን፣ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ እኩልነትንና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል አይነተኛ መሳሪያ እንደሆነ ስለሚታመን፤

የመንግሥትና የህዝብ ሚዲያ በክልሉና በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ-ሀብታዊና ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎችውስጥ የሚኖረውን የላቀ አስተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማስገባት በተበታተነ መንገድ ሲሰራባቸው የቆዩትን የሚዲያ ሕግጋት ወደአንድ የተዋሃደ ማእቀፍ በማምጣት ሚዲያዎች የአገልግሎት አድማሳቸውን ለማስፋት የሚያስችላቸውን ተቋማዊ ጥንካሬ እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤

በሕገ-መንግሥቱ በተደነገገው መሠረት በመንግሥትናበህዝብ ባለቤትነት ሥር በሚተዳደሩት የክልሉ መገናኛ-ብዙኃን ድርጅቶች በሕብረተ-ሰቡ ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችና አመለካከቶችሚዛናዊ በሆነ መንገድ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ የክልሉ ሚዲያ ይበልጥ የተጠናከረ ተቋማዊና የአሠራር ነፃነት፣ እንዲኖረውና የተሟላ ሕጋዊ ጥበቃ እንዲያገኝ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ፈጣን የሆነ ሀገራዊናአለም-አቀፋዊ የመረጃ ልውውጥ ፍላጎት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገናበዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየተደገፈ መምጣቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የክልሉ ሚዲያ የሕብረተ-ሰቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች በቅርበት እየተከታተለ በወቅቱ በመዘገብ ረገድ ሊጫወት የሚችለውን ሰፊ ሚና አጉልቶ ማሳየት ተገቢ በመሆኑ፤

በስራ ላይ ያለው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ሳቢና የተሻሻለ ስያሜንጨምሮ የዘመነ አደረጃጀትናአሰራር እንዲኖረው በማድረግ በሀገሪቱ ከሚገኙት አቻ የሚዲያ  ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲገነባና ኃላፊነቱን በብቃት እንዲወጣ ማስቻልተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤

የአማራ ክልል ምክር ቤት በተሻሻለው የብሄራዊክልሉ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 3 (1) ድንጋጌ ስር በተሠጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን አዋጅ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌዎች

  1. አጭር ርዕስ

ይህ አዋጅ“የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 274/2013 ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

  • ትርጓሜ
  • የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-

ሀ)“ሚዲያ”ማለትበሬዲዮ፣በቴሌቪዥን፣በድረ-ገፅ፣በህትመት፣እንዲሁምበበይነ-መረብ [Internet] በማሕበራዊመገናኛና  በኤሌክትሮኒክ ዘዴዎች የሚደረግ ተግባቦት [Online] አማካኝነት መረጃ /ኢንፎርሜሽን /የማሰባሰብ፣የማዘጋጀትና የማሰራጨት ሥራዎችንየሚያከናውኑየዜናና የፕሮግራም ሥራዎችንና መጣጥፎችን በማጠናቀር በልዩ ልዩ ዘዴዎች ለሕዝብ የሚያሰራጩወይም እነዚህኑ በቀጥታ ለሚያስተላልፉለሌሎች ተቋማት የሚያከፋፍሉ ተቋማት ናቸው፡፡

ለ) “ቦርድ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት የተቋቋመው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ነው፡፡

ሐ) “ጋዜጠኛ” ማለት በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንውስጥ በአዘጋጅነት፣ በአቅራቢነት፣ በአርታኢነት፣ በዘጋቢነት፣ በካርቱን አዘጋጅነት፣  በግራፊክስ ባለሙያነት፣ በፎቶግራፍ ወይም በተንቀሳቃሽ ፊልም አንሽነት፣ በፊልም ኤዲተርነት ወይም ዳይሬክተርነት፣ ወይም በዜናና መረጃዎች አሰባሳቢነት፣ በአቀነባባሪነት፣ በአሰራጪነት፣ በስልጠናና ምርምር፣ በገቢ ልማት ወይም በፕሮሞሽንየሙያ ተግባር ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰውነው፡፡

መ)“ቴክኒሻን”ማለትበሬዲዮ፣ በቴሌቪዢንና መሰል የሚዲያ ቴክኖሎጂዘርፍየድምጽና ምስል ቀረጻና ስርጭትም ሆነ ሌሎች ተዛማጅ ስራዎችን የሚያከናውኑ ባለሙያዎችን ያጠቃልላል፡፡

ሠ) “ሌላ ሠራተኛ” ማለት በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ውስጥበዚህ አንቀጽ ፊደል ተራ “ሐ”ናመ” ስር እንደአግባብነቱ ለጋዜጠኛ ወይም ለቴክኒሻንከተሰጠው ትርጓሜ ውጭ ያሉትንየኮርፖሬሽኑን ሠራተኞች ይገልጻል፡፡

ረ)“ፕሮግራም” ማለት በድምጽ ወይም በምስል ወይም በሁለቱም ተቀነባብሮ ለማሳወቅ፣ ለማስተማር ወይም ለማዝናናት ወይም ሁሉንም አካትቶ የሚቀርብ ስርጭት ነው፤

ሰ)“ህትመት” ማለት በጋዜጣ፣ በመጽሄት፣ በበራሪ ወረቀት እና በተለያየ ዓይነት ተዘጋጅቶ

የሚቀርብ የመረጃ አይነት ነው፤

ሸ)“የሚዲያ አገልግሎት” ማለት ሕዝብን ለማስተማር፣ ለማሳወቅ ወይምለማዝናናት በሬዲዮ፣

በቴሌቪዥን ወይም በህትመትተዘጋጅቶ የሚቀርብ የመረጃ አይነት ነው፤

ቀ)“ድረ-ገጽ”ማለት በበይነ-መረብ፣ በማሕበራዊ መገናኛም ሆነ በኤሌክትሮኒክ ዘዴዎች

በሚደረግ ተግባቦትና በሌሎችየሚከናወን ተግባር ነው፡፡

በ)”የዜና ወኪል” ማለት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተደራሽ

ባልሆነት  አካባቢ ወይም አገር የዜና ዘገባ የሚያደርስ ባለሙያ ነዉ፤

ተ) “ፍሪላንሰር” ማለት ከኮርፖሬሽኑ ውጭ ያለ ሌላ ሥራ የሚሠራ ሆኖ      

በየሚዲያ አውታሮች በክፍያ የዜና ንባብ ተግባር፤የትውውቅስራ፣ፕሮግራም ሰርቶ

የሚያቀርብ፣ልዩ ቃለ-መጠይቅ የሚሰራ፣የግራፊክስ ስራ፣ የካርቶን ስራ፣የትወና ስራ፣

የትረካ ስራ እና ሌሎችንም የሚያከናውን ባለሙያ ነው፤

ቸ) “ዜና”ማለት በድምፅ፣ በምስል ወይም በሁለቱም ተቀነባብሮ በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን፣በድረ-ገፅ፣

በህትመት፣እንዲሁም፤በበይነ-መረብ [Internet] ፣በማህበራዊ መገናኛ፣በኤሌክትሮኒክስ

የሚደረግ ተግባቦት [Online] መረጃ ለመስጠት እና ለማሳወቅ የሚቀርብ ዝግጅት ነው፤

ኀ) “ሰው”ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠውአካል ነው፤

  • በዚህአዋጅ ውስጥ በወንድ ጾታ የተደነገገው የሴትንም ጾታ ያካትታል፡፡
  • የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ አዋጅ ከፍተኛ የስራ አመራሩን ጨምሮ በኮርፖሬሽኑ የሚያገለግሉትን ጋዜጠኞች፣ ቴክኒሻኖች፣የዜና ወኪሎች፣የፍሪላንስናሌሎች ሰራተኞች በተመለከተ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት

ስለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን  መቋቋም፣ አላማ፣ አወቃቀርናሥልጣን

  • ስለመቋቋምና ተጠሪነት
  • የአማራ ክልል ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣/ከዚህ በኋላ “ኮርፖሬሽኑ/ እየተባለ የሚጠራውአካል ራሱን የቻለናሕጋዊ ሰውነት ያለው የክልሉ መንግሥትና ህዝብ ተቋም ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል፡፡
  • የኮርፖሬሽኑ ተጠሪነትለክልሉ ምክር ቤት ይሆናል፡፡
  • ዓላማዎች

ኮርፖሬሽኑበዚህ አዋጅ መሰረት የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡-

  • በክልሉምሆነ በፌደራሉ ሕገ-መንግሥት አግባብነት ባላቸው ፖሊሲዎች፣ ሕግጋት፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት ኃሣብን በነፃ የመግለፅ ነፃነትን ማነቃቃት፤
  • የክልሉ ምልአተ-ህዝብ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን እንዲያገኝ ለማድረግበዋና ዋናጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር በትጋት መሥራት፤
  • በክልሉውስጥ በሚከናወኑ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ-ሀብታዊና ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎችረገድ አጋዥ ሚና መጫወትና በሕብረተ-ሰቡ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ እሴቶችእንዲጎለብቱማበረታታት፡፡
  • ዋና መሥሪያ ቤት
  • የኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በባሕርዳር ከተማ ይሆናል፡፡
  • ኮርፖሬሽኑአስፈላጊ ሆኖ ባገኘው መጠን በክልሉ ውስጥናከክልሉ ውጭበተመረጡ የሀገሪቱ አካባቢዎችና በተለያዩ አገራት ቅርንጫፍ ወይም ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶችና የዜና ወኪሎች ሊኖሩት ይችላል፡፡
  • የኮርፖሬሽኑ ሥልጣንና ተግባር

ኮርፖሬሽኑበዚህ አዋጅ መሠረት የሚከተሉት ዝርዝር ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

  • በክልል እና በሀገር-አቀፍ ደረጃ የጎላ ፋይዳ ያላቸውን የሀገር ውስጥና የውጭ ዜናዎች፣ መዋዕለ-ዜናዎች፣ ሌሎች መረጃዎችና ተዛማጅ የፕሬስ ውጤቶች ያሰባስባል፣ እነዚህኑ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በድረ-ገጽ፣ በማሕበራዊመገናኛ፣ በኤሌክትሮኒክ ተግባቦት ህትመቶችን እያዘጋጀ በሚዲያ አገልግሎት በኩል በማሰራጨት ለሕዝብ ያደርሳል፣ ለዚህም ያግዘው ዘንድ እንዳስፈላጊነቱየሬዲዮ፣ የቴሌቪዥን፣ የህትመት፤ የማህበራዊ መገናኛ፣ የድህረ-ገጽ፣ የበይነ-መረብ፣ የኢሌክትሮኒክስ ተግባቦት [Online] ፕሮግራሞች እንዲኖሩት ያደርጋል፤
  • የመንግሥትን ስትራቴጃዊ አቅጣጫዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች በሚዲያው አማካኝነት ለክልሉ ሕዝብ ያስተዋውቃል፣ ሕብረተ-ሰቡም በነዚሁ ረቂቅ ሰነዶች ላይ አስቀድሞ ኃሳብ፣ ትችትና አስተያየት እንዲሰጥባቸውበማበረታታት ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስባቸው ምቹ መድረኮችን ይፈጥራል፤
  • ዜጎች ሰብዓዊናዲሞክራሲያዊ መብቶችናተነጻጻሪ ግዴታዎችን በተመለከተ ያላቸውን ግንዛቤ በየጊዜው ለማጎልበት የሚረዱ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን በተሞክሮዎች እየቀመረ ለህዝቡ ያቀርባል፣ ያሰራጫል፤
  • ነፃ የሕዝብ አስተያየቶችንናጥቆማዎችን ተቀብሎ ያጣራል፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት በመጠየቅ ምላሽ እንዲያገኙ ያደርጋል፣ ውጤቱንም መልሶ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል፤
  • የሕዝቡን ጠቅላላ ዕውቀትና ፈጠራ የሚያዳብሩና የመዝናናት ፍላጎቱን የሚያረኩ የተለያዩ የስነ-ፅሁፍ ውጤቶችን በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣  በህትመት፣ በማሕበራዊመገናኛ፣ በድረ-ገፅና በሌሎች የሚዲያ አውታሮች አማካኝነት ያሰራጫል፤
  • ለህዝብ ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑናወቅታዊነት ያላቸውን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ-ሀብታዊና ማሕበራዊ ጉዳዮችእየተከታተለ በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎችይዘግባል፣ ያሰራጫል፤
  • የፎቶግራፍና የተንቀሳቃሽ ምስል ዶክመንቴሽን፣ የህትመት፣የመዝናኛና የማስታወቂያ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤
  •  ሥራውንለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ የህትመት አገልግሎቶችን፣ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ማቀናበሪያና ማሰራጫዎችን፣ የዜናና መረጃ ማስተላለፊያ ወይም ማሸጋገሪያ፣ እንዲሁም ለተመሳሳይ አገልግሎቶች የሚውሉ ሌሎች መሰል ተቋማትን ይመሰርታል፣ መሣሪያዎችን በተገቢው ሥፍራ ይተክላል፣ ያቋቁማል፣ ያደራጃል፣ ያሥተዳድራል፤
  • ሕግ በሚፈቅደው መሠረት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚገኙ ተመሳሳይ ተቋማት ጋር ዜናና መረጃዎችን ይለዋወጣል፣ የሥልጠናና የልምድ ልውውጦችን ለማካሄድ የሚያስችሉትን የሥራ ግንኙነቶች ያደርጋል፤
  • የዘርፉን ቴክኒካዊ አቅም በመገንባት ረገድ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነቱ ካላቸውየሐገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ተቋማት ጋር ተባብሮ ይሠራል፤
  • የክልሉሚዲያተቋማት የሚስፋፉበትንናበተስማሚ ቴክኖሎጂ የሚደራጁበትን፣ እንዲሁም ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ በየጊዜው  እያጠና ለክልሉ መንግሥት ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
  • በራሱ ወይም ከተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚዲያ መሳሪያዎች ጥገናና ተከላ፣የማቃዳትና የማባዛት፣ የስልጠና፣ የምርምርና የማማከር ተግባራትን ያከናውናል፤
  • በሕግ መሰረት የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውሎችን ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
  • ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉትን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትያከናውናል፡፡
  • ድርጅታዊ አቋም
  • ኮርፖሬሽኑ የሚከተሉት አካላት ይኖሩታል፡-

ሀ)የሥራ አመራር ቦርድ፤

ለ) ዋና ስራ አስፈጻሚ፤

ሐ) ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎችእና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ፤

መ) ሌሎች የስራ ክፍሎች እና ሠራተኞች፡፡

2)ኮርፖሬሽኑ ሥራውን ለማከናወን በሥሩ የሬዲዮ፣ የቴሌቪዥን፣ የህትመት፣ የማሕበራዊ መገናኛ፣ እንዲሁምየድረ-ገጽ፣ የበይነ-መረብ፣ የኤሌክትሮኒክ ተግባቦት[Online] እና ሌሎችየሚዲያአገልግሎት ዘርፎች ይኖሩታል፡፡

ክፍል ሶስት

ስለኮርፖሬሽኑየሥራ አመራር ቦርድና ስለሥራ አስፈጻሚዎች

  • ስለቦርዱምስረታና ተጠሪነት
  • ኮርፖሬሽኑንበፖሊሲ-ነክ ጉዳዮች የሚመራ፣ የሚከታተልና በበላይነት የሚቆጣጠር የስራ አመራር ቦርድ፣ ከዚህ በኋላ /ቦርዱ/ እየተባለ የሚጠራ አካል በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል፡፡
  • ቦርዱ ሰብሳቢውን ጨምሮ ከሰባት የማያንሱና ከዘጠኝ የማይበልጡ አባላት ይኖሩታል፡፡
  • የቦርዱ ሰብሳቢ፣ምክትል ሰብሳቢና አባላቱአግባብነትካላቸውየክልሉ መንግሥት አካላትና የሕብረተ-ሰብ ክፍሎች ተወጣጥተውበርዕሠ-መሥተዳድሩ አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤትይሾማሉ፡፡
  • የቦርዱ ተጠሪነት ለክልሉ ምክር ቤቱይሆናል፡፡
  • የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የቦርዱ አባልና ፀሃፊ በመሆንያገለግላል፡፡
  • የቦርዱ አባላት የአገልግሎት ዘመን አምስት ዓመት  ይሆናል፤ ሆኖም አስፈላጊነቱ ሲታመንበት ማንኛውም የቦርድ አባል የአገልግሎት ጊዜው ሲያበቃ ለዳግመኛ ጊዜ ሊሠየም ይችላል፡፡
  • ማንኛውም የቦርድ አባል በአገልግሎቱ እንዳይቀጥል የሚያደርግ በቂ ምክንያት ስለመኖሩ  ከቦርዱ በኩል ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ በርዕሠ-መሥተዳድሩ  አሳሳቢነት ምክር ቤቱ በማናቸውም ጊዜ ከአባልነት ሊያነሳውና በሌላ ሊተካውይችላል፡፡
  • የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር

ቦርዱ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚከተሉትዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

  • ሚዲያን የሚመለከቱ ሀገር-አቀፍ ፖሊሲዎች፣ሕጎች፣ደንቦችና መመሪያዎችበኮርፖሬሽኑ ዘንድ ተግባራዊ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
  • በክልሉ ሕዝብ ሊታወቁ የሚገባቸውየመንግሥት ፖሊሲዎች፣ሕጎች፣ደንቦችና መመሪያዎች በኮርፖሬሽኑየተለያዩ የሚዲያዘርፎች አማካኝነት በወቅቱ መተላለፋቸውን ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፤
  • የክልሉ ህዝብ ኮርፖሬሽኑበሚሰጣቸው አገልግሎቶች ምን ያህል እንደረካ ይገመግማል፣ይበልጥ ተጠቃሚ የሚሆንባቸውን ስልቶችበየጊዜው እየፈተሸ ያሻሽላል፣ ተግባራዊ ይሆኑ ዘንድ ለኮርፖሬሽኑ መመሪያዎችን ይሰጣል፣ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፤
  • ኮርፖሬሽኑ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚፈፅማቸውን ተግባራት በተመለከተ ከውስጥና ከውጭበሚነሱ ስሞታዎችና በሚቀርቡ ቅሬታዎች ላይ ተገቢ ማብራሪያዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ እንዳስፈላጊነቱም ስሞታዎችንና ቅሬታዎችን ከመረመረ በኋላ ተገቢ ነው ብሎ ያመነበትን ውሳኔ ይሰጣል፤
  • ኮርፖሬሽኑ በብሄር-ብሔረሰብ፣ በፆታ፣በእድሜ፣ በአካል ጉዳት፣ በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ አመለካከቶችና የመድልዎ ምንጭ ሊሆኑ በሚችሉ ሌሎች ጉዳዮች አንዳች ልዩነት ሳያደርግ ለሁሉም ወገኖች ሚዛናዊ የመረጃ ሽፋን መስጠቱን ይቆጣጠራል፤
  • በኮርፖሬሽኑ የሚዲያ አውታሮችየሚሰጡትንአገልግሎቶችውጤታማነት ይገመግማል፣ ስለሚሻሻሉበት መንገድ መመሪያ ይሰጣል፤
  • የኮርፖሬሽኑን መዋቅር ገምግሞ ያፀድቃል፣ በሥራ ላይ እንዲውል መመሪያ ይሰጣል፤
  • የተቋሙን የሥራ ባህርይ ባገናዘበና አግባብ ካላቸው ሕግጋት ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር ተጠንተው የሚቀርቡለትን የጋዜጠኞች፣ቴክኒሻኖችና ሌሎች ሠራተኞች ቅጥር፣የደምወዝ ስኬል፣አበልና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ይወስናል፣እንዳስፈላጊነቱም ያሻሽላል፤ የተሻሻሉትንም በስራ ላይ እንዲዉሉ ያደርጋል፤
  • ጋዜጠኞችን፣ ቴክኒሻኖችንና ሌሎች ሠራተኞችን የሚመለከቱ የስራ ማከናወኛ ማንዋሎች ተረቀው እንዲቀርቡለት ያደርጋል፣ እነዚህኑ መርምሮ ያፀድቃል፣በሥራ ላይ እንዲውሉ መመሪያ ይሰጣል፤
  • በክልሉ ውስጥ የሚሠራባቸውን የፋይናንስ፣የግዥና የንብረት አሥተዳደር ሕግጋት፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በኮርፖሬሽኑ ስራ-አመራር በኩል ተዘጋጅተው የሚቀርቡለትንና ከኮርፖሬሽኑ የሥራ ባህርይ ጋር የተጣጣሙ መሰል መመሪያዎችንና ማኗሎችን መርምሮ ያፀድቃል፣ ይህንም ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ  ያሳውቃል፤
  • የኮርፖሬሽኑን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የስራ እቅድም ሆነ ዓመታዊ የካፒታልና የመደበኛ በጀት መርሓ-ግብርና የክንውን ሪፖርት መርምሮ ያፀድቃል፣አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  • ኮርፖሬሽኑ ከመንግሥትና ከውስጥ ገቢ የሚመደብለትን በጀት በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋሉንበቅርብ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
  • ኮርፖሬሽኑ የሚጠነክርበትንና አሠራሩን የሚያሻሽልበትን መንገድ ይቀይሳል፤
  • የኮርፖሬሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት ወቅታዊ ሪፖርቶችን ለክልሉ ምክር ቤት ያቀርባል፤
  • ኮርፖሬሽኑን በሚመለከቱ ሌሎች ፖሊሲ-ነክ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፣ ይወስናል፡፡
  • የቦርዱ ስብሰባዎች
  • ቦርዱ ቢያንስ በሦስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያካሂዳል፡፡
  • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1)ስር የተደነገገው ቢኖርም አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም በሰብሳቢው ጥሪ ወይም ከቦርዱ አባላት መካከል አንድ-ሶስተኛ የሚሆኑት ከጠየቁ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል፡፡
  • በስብሰባው ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አባላት ከተገኙ ምልአተ-ጉባዔ ይሆናል፡፡
  • ቦርዱ ማናቸውንም ውሣኔ የሚያሳልፈው በድምፅ ብልጫ ሲሆን፤ድምጹ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ኃሳብ የቦርዱ ውሣኔ ሆኖ ያልፋል፣ ሆኖም የቀረበው የልዩነት ሀሳብ በቦርዱ ቃለ-ጉባኤ ተመዝግቦ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  • የቦርዱ ሰብሳቢ በማይኖርበት ጊዜ ምክትል ሰብሳቢውየቦርዱን ስብሰባዎችይመራል፡፡
  • ከዚህ በላይ ከንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 5የሰፈሩት ድንጋጌዎች ቢኖሩም ቦርዱ ይህንን አዋጅ ተከትሎ የራሱን ተጨማሪ የስብሰባና የአሠራር ሥነ-ሥርዓት መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፡፡
  • ለቦርድ አባላት ስለሚከፈል አበል

ለቦርዱ ሰብሳቢና አባላቱ ሊከፈል የሚገባውየአበል አይነትና መጠኑ በኮርፖሬሽኑ ስራ አመራር ተዘጋጅቶ ሲቀርብ በክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት ይወሰናል፡፡

  1. ስለዋና ሥራ አስፈጻሚው አሰያየምና ሥልጣን
  2. የኮርፖሬሽኑዋና ስራ አስፈጻሚ በርዕሠ-መስተዳድሩ አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማል፡፡
  3. ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዚህ አዋጅና ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኮርፖሬሽኑን ሥራዎች ይመራል፣ ኮርፖሬሽኑን ያሥተዳድራል፡፡
  4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ(2)ድንጋጌ ስር የሰፈረው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ሥራ አስፈጻሚው የሚከተሉት ዝርዝር ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

ሀ)የኮርፖሬሽኑን የዕለት ተለት ሥራዎች በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል፤

ለ)የኮርፖሬሽኑን ጽሕፈት ቤት ያደራጃል፤

ሐ) ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የኮርፖሬሽኑን

ጋዜጠኞች፣ ቴክኒሻኖችናሌሎች ሠራተኞች ይቀጥራል፣ ያሥተዳድራል፣

ያሰናብታል፤

መ)የኮርፖሬሽኑን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜየስራ እቅድ፣እንዲሁም

ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብርና የማስፈጸሚያ በጀት ረቂቆች

አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል፣ በርሱም አማካኝነት ለክልሉ ምክር ቤትቀርቦ እንዲሰማና

እንዲጸድቅ ያደርጋል፤

ሠ)ለኮርፖሬሽኑ በተፈቀደው በጀትና የስራ ፕሮግራም መሰረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል፤

ረ) ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ኮርፖሬሽኑን ይወክላል፤

ሰ)የኮርፖሬሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት ወቅታዊ ሪፖርቶችን እያዘጋጀ

ለቦርዱና ለክልሉ ምክር ቤት ያቀርባል፤

ሸ)የኮርፖሬሽኑን መካከለኛ የአመራር አካላት አመላመልና ምደባ ይወስናል፤

ቀ)  በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ያከናውናል፡፡

  • ዋና ሥራ አስፈጻሚውለኮርፖሬሽኑ ሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገው መጠን ከሥልጣንና ተግባራቱከፊሉንለበታች የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችናሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • ስለ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ሥልጣን
  • የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራአስፈጻሚዎች በቦርዱ ተመልምለው በዋና ሥራ አስፈጻሚው አቅራቢነት በርዕሠ-መሥተዳድሩ ይሾማሉ፤
  • የምክትል ሥራ አስፈጻሚዎች ተጠሪነት ለዋና ሥራ አስፈጻሚው ሆኖ፡-

ሀ) ለኮርፖሬሽኑ የተሰጡትን ሥራዎች በማቀድ፣ በማደራጀት፣በመምራትና በማስተባበር

ረገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ያግዛሉ፤

ለ) የተመደቡባቸውን የሥራ ዘርፎች ይመራሉ፣ ይቆጣጠራሉ፤

ሐ) በዋና ሥራ አስፈጻሚው ተለይተው የሚሰጧቸውን ተግባራት ያከናውናሉ፤

መ) ለሥራ ቅልጥፍናና ውጤታማነት ባስፈለጋው መጠንከሥልጣንናተግባሮቻቸው

ከፊሉን ለጋዜጠኞች፣ ለቴክኒሻኖችና ለሌሎችሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፉ

ይችላሉ፡፡

  • በኮርፖሬሽኑ ውስጥ ከአንድ በላይ የሆኑ ምክትል ስራ አስፈጻሚዎች ያሉ እንደሆነ

ከነዚሁ መካከል በተለይ የፅሁፍ ዉክልና የተሰጠው ሰው መኖሩ ካልተረጋገጠ በስተቀር

ዋና ስራ አስፈጻሚው በማይኖርበት ወይም ሥራውን ለማከናወን

በማይችልበት ጊዜና ሁኔታ እርሱን ተክቶ የሚሠራው በሹመት ቀደምትነት ያለው

ምክትል ስራ አስፈጻሚ ይሆናል፡፡

  1. ስለጽሕፈት ቤት ኃላፊው ሥልጣን
  2. የኮርፖሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በዋና ሥራ አስፈጻሚውመልማይና

አቅራቢነት በቦርዱ ይሾማል ፤

(2) የኮርፖሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተጠሪነቱ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኖ ፤

ሀ )የኮርፖሬሽኑን አሥተዳደራዊ ሥራዎች ይመራል፣ ያስተባብራል፤

ለ)ኮርፖሬሽኑ በውስጥና በውጭ ካሉት ደንበኞች ጋር ያለውን የአገልግሎት

አሰጣጥ ግንኙነት ይመራል፣ ያቀላጥፋል፤

ሐ)በዋና ሥራ አስፈጻሚው የሚሰጡትን ሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ያከናውናል፡፡

  1. ስለቅሬታ አቀራረብና አወሳሰን
ማንኛውም ጋዜጠኛ፣ቴክኒሻን ወይም ሌላ ሠራተኛ  ከሥራው ጋር በተያያዘ በደል ደርሶብኛል ብሎ ያመነ እንደሆነ ስለደረሰበት በደል አቤቱታውን አዘጋጅቶና በማስረጃ ደግፎ ለኮርፖሬሽኑ የማቅረብ መብት አለው፤ ሆኖም ይኸው አቤቱታ ቅሬታው ተፈጥሯል ከተባለበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
ቅሬታን ስለማጣራትና ስለመወሰንኮርፖሬሽኑ በደል አድርሶብኛል የሚል ማንኛውም ጋዜጠኛ፣ቴክኒሻን ወይም ሌላ ሠራተኛ ወይም ፍሪላንሰር ወይም የዜና ወኪል በደሉ ደርሶብኛል ከሚልበት ቀን አንስቶ በሚቆጠሩ አስር(10) የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በጽሁፍ አዘጋጅቶ በመጀመሪያ ለኮርፖሬሽኑ ቅሬታ ሰሚ አካል ያቀርባል፡፡ቅሬታው የቀረበለት አካልም ጉዳዩ በቀረበለት በአስራአምስት (15) የሥራ ቀናት ውስጥ ጉዳዩን ከመረመረና ካጣራ በኋላ ምላሹን በጽሁፍ መስጠት አለበት፡፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2)መሠረት የኮርፖሬሽኑ ቅሬታ ሰሚ ኣካል በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔው በደረሰውአስር (10) የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን በጽሁፍ አዘጋጅቶ ለዋና ሥራ አስፈጻሚውያቀርባል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚውም የቀረበውን አቤቱታ ተመልክቶ በአስር(10) የሥራ ቀናት ውስጥ እንደነገሩ ሁኔታ ሊቀበለው ወይም ውድቅ ሊያደርገውይችላል፡፡በዚህ ደረጃ በተሰጠው ውሣኔ ያልረካማንኛውም ሰው ውሣኔውኢ-ፍትሐዊ ነውየሚልበትን ምክንያት ጠቅሶ በአስር(10) የሥራ ቀናት ውስጥ የይግባኝ አቤቱታውን ለቦርዱ ከማቅረብ አይታገድም፡፡ቦርዱም ጉዳዩ በደረሰው በሰላሳ (30) ተከታታይ  ቀናት ውስጥ ተገቢ መስሎ የታየውን ምላሽ ይሰጣል፡፡ ቦርዱ በዚህ ደረጃ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ (5)ስር የሰፈረው ድንጋጌ ቢኖርም ቦርዱ በሠጠው ውሳኔ ላይ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለ ብሎ ያመነ ማንኛውም ወገን ቦርዱ ውሳኔውንካሳለፈበት ቀን ጀምሮ በዘጠና(90)ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በጽሁፍ አዘጋጅቶ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡  

ክፍል አራት

ስለሙያ ነፃነትና ተጠያቂነት

  1. ስለጋዜጠኞችና ቴክኒሻኖች  የሙያ ነፃነትና ተጠያቂነት
  2. ኮርፖሬሽኑ ይህንን አዋጅ ተከትሎ ወደፊት የሚያወጣው የአሠራር መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ጋዜጠኞች እና ቴክኒሻኖች ነፃና ገለልተኛ በመሆን ሥራቸውን በሙሉ ነፃነት ያከናውናሉ፡፡
  3. ጋዜጠኞችና ቴክኒሻኖች በሕግ መሠረት የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት በሚያከናውኑበት ወቅት ለሚደርስ ጉዳት የግል ተጠያቂነት አይኖርባቸውም፡፡
  4. በዚህ አንቀጽንኡስ አንቀጽ 2 ስር የሰፈረው ድንጋጌ ጋዜጠኞችና ቴክኒሻኖች በሥራ አፈፃፀምም ሆነ በሥነ-ምግባር ረገድ በሚታይባቸው ጉድለት በሕግ ከመጠየቅ አያድናቸውም፡፡
  5. በኮርፖሬሽኑ ጋዜጠኛወይም ቴክኒሻንበተሠራ ፕሮግራምና ህትመትውጤት ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ሰው ለኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡
  6. አቤቱታው የቀረበለት የስራ ኃላፊም ጉዳዩን በአፋጣኝ አጣርቶ በወቅቱ ውሳኔ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
  7. አቤቱታ የቀረበለት ኃላፊ ጉዳዩን ለማጣራት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አግባብ ያላቸውን ባለሙያዎች የሚያካትት አጣሪ ኮሚቴ ሊያቋቁም ይችላል፡፡
  8. አቤቱታውን የመረመረው የስራ ኃላፊ የተሠራው ፕሮግራም ወይም ህትመት ችግር ያለበት ሆኖ ያገኘው እንደሆነ ይህንኑ በማስረጃ በማረጋገጥና አግባብ ያለውን የሕግ ድንጋጌ በመጥቀስ እንዳይሰራጭ አግዶ፣ ተሰራጭቶ ከሆነምመረጃው በተላለፈበት የመገናኛ ዘርፍ ተመሳሳይ አምድ፣ ተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ተገቢው እርማት እንዲሰጥ በማድረግ ከኮርፖሬሽኑ ድረ-ገጽ ላይ ካወረደው በኋላ  እንደችግሩ የክብደት ደረጃ ጋዜጠኛውወይም ቴክኒሻኑበደል ደረሰብኝ የሚለውን ወገን ይቅርታ እንዲጠይቅ ወይም በኮርፖሬሽኑ ተአማኒነትና መልካም ስም ላይ ላስከተለው ጉዳት በሥነ-ምግባር ጥሰት ክስ እንዲመሠረትበት ሊያደርግ ይችላል፡፡
  9. ስለፖለቲካ ገለልተኝነት
  10. በኮርፖሬሽኑውስጥ የሚያገለግል ማንኛውም ጋዜጠኛወይም ቴክኒሻንየፖለቲካ ድርጅት አባል እንዳይሆን፣ በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችእንዳይሳተፍ፣በስራው ላይ የራሱን ፖለቲካዊ አመለካከትእንዳያንፀባርቅ ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ የግል አቋሙን እንዳያራምድ ተከልክሏል፡፡
  11. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ቢኖርም ጋዜጠኞች፣ቴክኒሻኖችም ሆኑ ሌሎች የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች በሙያ ማሕበር የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለሚዛናዊነት

የኮርፖሬሽኑጋዜጠኛወይም ቴክኒሻን የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፡-

  1. ከፍራቻ፣ከአድልዎ፣ ወይም ከጥላቻ በተለይም ከግለሰባዊና ከወገናዊ ጥቅም ወይም ከህዝብና ከሚዲያ ግፊት የመነጨ አንዳች ተፅእኖ ሳያድርበት በሕግ መሰረት ተግባሩን የማከናወን፤
  2. በዘገባው የሁሉንም ወገኖች ሃሳብ ሚዛናዊ በሆነ መልክ አካቶ የመስራት፤
  3. ምንጊዜም ቢሆን የግለሰቦችን ሰብአዊ መብትና ክብር የመጠበቅና የመደገፍ፡፡
  4. ተጠሪነት
  5. የጋዜጠኞች የበላይ ኃላፊ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነው፡፡
  6. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ(1) ስር የሰፈረው አጠቃላይ ድንጋጌ ቢኖርም እያንዳንዱ ጋዜጠኛወይምቴክኒሻንከርሱ ቀጥሎ ላለው የቅርብ ሀላፊ ተጠሪይሆናል፡፡

ክፍል አምስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

  • ስለኮርፖሬሽኑ የበጀት ምንጭና አሥተዳደሩ
  • የኮርፖሬሽኑ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተወጣጣ ይሆናል፡-

ሀ) በክልሉ መንግሥት የሚመደብለት በጀት፤

ለ) በዚህ አዋጅ መሠረት ከሚሰጣቸው አገልግሎቶችየሚሰበስበውክፍያ፤

ሐ) ሌሎች ምንጮች፡፡

  • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1)ስር ከተዘረዘሩት ምንጮች የሚገኙት ገቢዎችበኮርፖሬሽኑ ሥም በሚከፈት የባንክ ሂሳብ ተቀማጭ ሆነውየኮርፖሬሽኑን ሥራዎች ለማከናወን ይውላሉ፡፡
  • የኮርፖሬሽኑ የሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ መመሪያ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  • ስለሂሳብ መዛግብት
  • ኮርፖሬሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብትንና ሠነዶችን ይይዛል፣ ይጠብቃል፡፡
  • የኮርፖሬሽኑፋይናንስም ሆነ ንብረት-ነክ ሰነዶች በክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየጊዜውይመረመራሉ፡፡
  • የመተባበር ግዴታ

የኮርፖሬሽኑ ጋዜጠኞች እና ቴክኒሻኖች በዚህ አዋጅና በሌሎች ተዛማጅ ሕጎች የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት በሚያከናውኑበት ጊዜ ትብብር እንዲያደርግ የተጠየቀ ማንኛውም ሰው ከአቅም በላይ ያልሆነና በራሱ ላይ አንዳች ጉዳት የማያስከትልበት ሆኖ እስከተገኘ ድረስ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

  • የወንጀል ተጠያቂነት
  • የኮርፖሬሽኑ ጋዜጠኞችና ቴክኒሻኖች ለህዝብ መረጃ ለማድረስ ይረዳቸው ዘንድ የሚያቀርቡለትን ጥያቄ ያለበቂ ምክንያት ለመመለስ ፈቃደኛ ሆኖ ያልተገኘ ማንኛውም ሰው በሀገሪቱ የወንጀል ሕግ የበለጠ የሚያስቀጣው ካልሆነ በስተቀር ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር) በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
  • የኮርፖሬሽኑ ጋዜጠኞችና ቴክኒሻኖችሥራቸውን በነፃነት እንዳያከናውኑ ጣልቃ ገብቶ ያሰናከለ ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕጉ የበለጠ የሚያስቀጣው ካልሆነ በስተቀር ከአንድ ዓመት በማያንስና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑእ እስራት ይቀጣል፡፡
  • ማንኛውም የኮርፖሬሽኑ ጋዜጠኛወይም ቴክኒሻን በዚህ አዋጅአንቀፅ 19 ንዑስ አንቀጽ (1)ስር የተመለከተውን ክልከላ በመተላለፍ ከስራው ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ወገንተኝነትንያንፀባረቀ ወይም ስለዚሁ ጉዳይ በግል የማሕበራዊ መገናኛውላይ ከጻፈ ወይም የማሕበረ-ሰብ አንቂነት ተግባር ካከናወነ በወንጀል ሕጉ የበለጠ የሚያስቀጣዉ ካልሆነ በስተቀር ከአንድ አመት በማያንስና ከሶስት አመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል፡፡
  • ስለተሻሩና ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው  ሕጎች
  • የሚከተሉትሕጎች በዚህ አዋጅ ተሽረዋል፡-

ሀ)የተሻሻለው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር

88/1995 ዓ.ም፤

ለ) የተሻሻለው የአማራ ክልል ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ማቋቋሚያአዋጅ

ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 200/2005 ዓ.ም፡፡

  • ይህንን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሕግ፣ደንብ፣መመሪያ ወይም የተለመደ አሠራር በዚህ አዋጅ ውስጥ በተሸፈኑትጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
  • ደንብየማውጣት ሥልጣን

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ለዚህ አዋጅ ሙሉ ተፈፃሚነት የሚያስፈልጉትን ደንቦች ሊያወጣ ይችላል፡፡

  • መመሪያ የማውጣት ሥልጣን

           ይህንን አዋጅና በአዋጁ መሰረት የሚወጡትን ደንቦች ለማስፈፀም የሚያስፈልጉትን መመሪያዎች ቦርዱ ሊያወጣ ይችላል ፡፡

  • አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ

ይህአዋጅ ከመጋቢት 03 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት

Share

Facebook
Twitter
Pinterest
LinkedIn

About Post Author

Ayele Addis

ayeleradio@gmail.com
Happy
Happy
0 0 %
Sad
Sad
0 0 %
Excited
Excited
0 0 %
Sleepy
Sleepy
0 0 %
Angry
Angry
0 0 %
Surprise
Surprise
0 0 %
Next Post
  • News

Ethiopian Mass Media Action (EMMA) give training for Ethiopian journalists

Ayele Addis January 19, 2022

The training series that would cover professionals from reporters to the leadership shall have continuity and be categorized as short, medium, and long term. The following are among the major topics that give attention: 1.         Basics of radio, television, and website journalism; 2.         Editorial training on selection and production of the news; 3.         Production of […]

Related Post

  • News

Monthly Journalists and Media Situation Report in Ethiopia

Ayele Addis February 15, 2022February 15, 2022

 “Respect the rights of journalists who advocate for the rights of citizens!” By Amhara Region Journalists Association: Bahir Dar, Ethiopia: Contact: Amharamedia@gmail.com and Ayeleradio@gmail.com It is to be recalled that Amhara Journalists association and international organizations have been witnessing the progress of press freedom in Ethiopia in recent years. However, there are indications that this […]

  • News

Analysis of Ethiopian Mass Media Development :

Ayele Addis January 31, 2022

Review by Ayele Addis Ambelu ayeleradio@gmail.com Kassahun Wodajo Woldemariam*Researcher Scholar at the Department of Journalismand Mass Communication, Andhra University Professor (Dr.) P. Bobby Vardhan**Head, Department of Journalism andMass Communication, Andhra University Abstract The purpose of this study is to describe the historical development of the Ethiopian mass media in the two consecutive regimes. To serve […]

  • News

Weekly Sponsor : ELELETA Purified Water Bahir Dar

Ayele Addis February 11, 2022February 11, 2022

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • TOP STORIES
  • TOP VIDEOS
  • Job Vacancy
  • Scholarship
Copyright © 2022 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress