Skip to content
  • Ethiopian Mass Media Action | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት

May 9, 2022
  • ዜና
    • ፖለቲካ
    • ንግድ
    • ጤና
    • ስልጣኔ
    • አካባቢያዊ
    • መዝናኛ
      • የኢትዮጲያ ቆንጆ
      • የኢትዮጲያ ሙዚቃ
      • የኢትዮጲያ ድራማ
  • ልዩ ዕትም
    • ምርጫ እና ዲሞክራሲ
    • ሰብዓዊ መብት
  • ኢመብድ
  • ስፖርት
  • ራዲዮ እና መክስተትርዒት
  • ጉብኝት
  • ዕድሎች
    • የትምህርት ዕድል
    • የስራ ማስታወቂያ
    • የተለያዩ ስልጠናዎች
  • ኢመብድ ሽልማት
  • ትምህርቶች
    • ጋዜጠኝነት
    • የሚዲያ ጥናት
    • የህዝብ ግንኙነት
    • የኢመብድ ጥናታዊ ጽሁፍ ማህደር
    • የጥበብ ትምህርት ቤት

Search Field


Warning: sprintf(): Too few arguments in /home/africanewschanne/public_html/am/wp-content/themes/blook/assets/resources/breadcrumb-trail/inc/breadcrumbs.php on line 254
  • Home
  • News

ግጭት አገናዛቢ ዘገባ ; Conflict Sensitive Reporting for Ethiopian Journalists and Media Amharic Handbook

Reporting on Food Security and Rural Development in East Africa

  • News

ህግን የተፃረረ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት Gov’t interference in the media

Ayele Addis April 17, 2022

የተካሄደው መላመልና አሻሻም ሂደት እንዲስተካከል እንጠይቃለን ; የሚመለከታችሁ አካላትም ይህ ህግን የተፃረረ አካሄድ እንዳይደገምና ልምድ ሆኖ በመንግስት ስርዓት ውስጥ እንዳይቀጥል ድምጻችሁን እንድታሰሙ እንጠይቃለን፡ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት ያጸደቀው ፖርላማው ከዓመት በፊት ያወጣውን የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2ዐ13 በተፃረረ መሆኑን ተመልክተናል፤

በመጀመሪያ ደረጃ አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጁ ከረቂቁ ጀምሮ ምክር ቤታችን በትኩረት ሲከታተለው የነበረና በብዙ መድረኮች ላይ ተገኝቶም ሀሳብ ያዋጣ ሲሆን አዋጁ ከመፅደቁ በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተጠራ የህዝብ አስተያየት መቀበያ መድረክ ላይ ተገኝቶ ለሚዲያ ስራ አስቸጋሪ ያላቸውን ሀሳቦች አቅርቦ የተከራከረ ከመሆኑም በላይ ከፍትሕ ሚኒስትሩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ሰፊ ውይይት አካሂዷል፤

የአዋጁ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት ገለልተኛ የህግና የሚዲያ እውቀት ባላቸው ግለሰቦች መዋቀሩን ምክር ቤታችን በበጎ ጎኑ የተመለከተው ሲሆን ይህንኑ ተከትሎም በፍትህ ሚኒስቴር ስር የተዋቀረው የህግ ማሻሻያ አማካሪ ቡድን ስራውን ከመጀመሩ በፊት ባለፈው የፕሬስ አዋጅ ላይ ያሉና አላሰራ ያሉ ድንጋጌዎች የትኞቹ እንደሆኑ አስቀድሞ የዳሰሳ ጥናት ባከናወነበት ወቅት ከተገኙ ውጤቶች መሀከል አንዱና ዋናው የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን በቦርድ አባልነትም ሆነ በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩ ግለሰቦች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊና የገዢው ፖርቲ ቁልፍ ሰዎች የመሆናቸው ሁኔታ ሚዲያውን በነፃነትና በገለልተኝነት እንዳያገለልሉ እንቅፋት መሆኑን ያመላከተ ነበር፤

በዚህም የተነሳ አዲስ በሚረቀቀው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ላይ ቦርዱንም ሆነ ባለስልጣኑን የሚመሩት ግለሰቦች ከፖርቲ አባልነትና ወሳኝ ከሆነ የመንግስት የስራ ሀላፊነት ነጻ እንዲሆኑ ከፍተኛ ትግል ተደርጎበታል፤ ይህኑን የሚዲያውና የፕሬስ ነፃነት አቀንቃኝ ወገኖች አስተያየት መነሻ በማድረግ በአዋጁ ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል፡፡

ሆኖም ሰሞኑን የምክር ቤቱ የተደረገው የቦርድ አባላት አሰያየምና የሹመት አሰጣጥ በአዋጁ ከተቀመጠው ድንጋጌ ያፈነገጡ ሆነው አግኝተናቸዋል፤

በመጀመሪያ ደረጃ የባለስልጣኑ የቦርድ አባላት ከመሰየማቸው በፊት ምልመላው የሚካሄደው ‹ግልጽ በሆነ የህዝብ ጥቆማ እና በመገናኛ ብዙሃን በሚተላለፍ ማስታወቂያ ነው› ይላል በአዋጁ አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 2 ላይ፡-

2/ የቦርዱ አባላት እጩዎችን የመመልመልና የማፅደቁ ሂደት ሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን ያለበት ሲሆን፤ በሂደቱም፡-

ሀ) ሕዝቡ እጩ ግለሰቦችን በመጠቆምና በእጩዎች ላይ አስተያየት እንዲሰጡ እድል እንዲሰጣቸው ይደረጋል፤

ለ) የዚህን አዋጅ ዓላማዎችና መርሆች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የእጩዎች አመራረጥ ሂደትና የተመረጡ እጩዎች ዝርዝር በመገናኛ ብዙሃን ወይም በሌሎች ኤሌክትሮኒክ ማሰራጫዎች ታትሞ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል፤

ሐ) የእጩዎች ምልመላ የኢትዮጵያን ብዝሃነት ያማከለ ፌደራላዊ ውክልና እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ይላል፡፡

፤ ይህ አልተደረገም፤ በመገናኛ ብዙሃንም ህዝቡ እንዲጠቁም ዕድል አልተሰጠውም፤አስተያየትም አልተሰጠም፤ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ይህንኑ በተመለከተ ላነሷቸው ጥያቄዎች በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር የሰጧቸው ምላሾች ተገቢ ሆነው አላገኘናቸውም፤

በሁለተኛ ደረጃ የቦርዱ አባላት የሚመረጡበትን መስፈርት በተመለከተ በአንቀፅ 11 ላይ 7 ያህል መስፈርቶችን አስቀምጧል፤ ከእነዚህ መስፈርቶች መሀከል በ6ኛ ደረጃ ላይ፡-

6/ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ወይም ተቀጣሪ ያልሆነ፤› ይላል፤

ነገር ግን በምክር ቤቱ የተሾሙ ግለሰቦችን ስንመለከት ሰብሳቢውን ጨምሮ ሌሎች አባላት የብልፅግና ፖርቲ አባላት ብቻ ሳይሆኑ ቁልፍ የመንግስት ስልጣን ላይ የተቀመጡ ግለሰቦች ናቸው፤

ለሌላው የቦርዱ አባት ስብጥርን በተመለከተ በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 5 ላይ ቢያንስ ሁለት የቦርድ አባላት ከመገናኛ ብዙሃን ተቋማት እንዲሆኑ ይደነግጋል፤

5/ ከቦርድ አባላት መካከል፡-

ሀ) ሁለቱ ከሲቪል ማኅበረሰብ፣ ሁለቱ ከመገናኛ ብዙሃን እና ሁለቱ በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ጠቀሜታና አግባብነት ካላቸው የተለያዩ ተቋማትና የህብረተሰብ ክፍሎች፤

ለ) ሦስቱ አግባብነት ካላቸው የመንግሥት አካላት፤ የተውጣጡ ይሆናሉ፡፡› ይላል፤

ከተሾሙት ግለሰቦች መሀከል ግን አንድም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያ አልተካተተም፤ በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ አግባብነት ካላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሚለው መስፈርትም እነማን እንደተመረጡ ግልፅ አይደለም፤ ከሲቪክ ድርጅቶች እንዲካተቱ የተመረጡት ሁለት ግለሰቦችም ከ3ሺ በላይ የሲቪክ ድርጅቶች ባሉበት ሀገር ሁለቱም ከኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሆናቸው የአዋጁን መንፈስ የሚቃረን ሆኖ አግኝተነዋል፤

በንዑስ አንቀፅ (ለ) ላይ የተመለከተው ‹አግባብነት ካላቸው የመንግስት አካላት› የሚለውም ቢሆን የፖለቲካ ፖርቲ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ተቀጣሪዎች እንዳይሆኑ አዋጁ በግልጽ ከልክሏል፤

ሌላው ምክር ቤቱ ከወራት በፊት የሰየመው የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የዳይሬክተሮች ሹመትም ህግን የተከተለ እንዳልሆነ መመልከት ይቻላል፤ ይኸውም የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዳይሬክተሮች የሚሾሙት በአዋጁ አንቀፅ 17 ንዑስ አንቀፅ 1 መሠረት ቦርዱ ከተሰየመ በኋላ በቦርዱ አቅራቢነት እንጂ ከቦርዱ በፊት መሆን አልነበረበትም፤

17. የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባራት

1/ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በቦርዱ ተመልምል በመንግሥት አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሰየማል፡፡ይላል፡፡

ነገር ግን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመው ፖርላማው ሹመታቸውን ያፀደቀው መቅደም ያለበትን የቦርዱን አባላት ሳይሰይም ነው፡፡

ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ቁልፍ ሚና ካላቸው የዲሞክራሲ ተቋማት መሀከል አንዱ የሆነው የመገናኛ ብዙሃን ነፃና ገለልተኛ ሆኖ መቋቋምና ስራውን ያለ አድልዎ መስራት ካልቻለ የሚታሰበው ለውጥ እውን የመሆኑ ጉዳይ አጠያያቂ ይሆናል፤

መንግስት አዲሱን የመገናኛ ብዙሃን አዋጁ እንዲሻሻል ሲያደርግ ባለፉት 27 ዓመታት በህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጡት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በተሻለ ሁኔታ እንዲከበር በማሰብ እንደሆነ እንገነዘባለን፤ ሆኖም ከፍተኛ ትግልና ተሳትፎ ተደርጎበት የወጣው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ግልጽ የሆነ የህግ ጥሰት ሲገጥነመው መከላከል የዘርፉ ተዋናንያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ድርሻ በመሆኑ ሰሞኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተካሄደው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ አባላት ህገ ወጥ አመላመልና የአሻሻም ሥርኣት እንዲታረም በአንክሮ እንጠይቃለን፤

ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታችሁ አካላትም ይህ ህግን የተፃረረ አካሄድ እንዳይደገምና ልምድ ሆኖ በመንግስት ስርዓት ውስጥ እንዳይቀጥል ድምጻችሁን እንድታሰሙ እንጠይቃለን፡፡

Share

Facebook
Twitter
Pinterest
LinkedIn

About Post Author

Ayele Addis

ayeleradio@gmail.com
Happy
Happy
0 0 %
Sad
Sad
0 0 %
Excited
Excited
0 0 %
Sleepy
Sleepy
0 0 %
Angry
Angry
0 0 %
Surprise
Surprise
0 0 %
Next Post
  • News

Reporting on Food Security and Rural Development in East Africa

Ayele Addis April 22, 2022

Reporting on Food Security and Rural Development in East Africa Dates: 16 May 19 May | Location: OnlineApplication deadline: 27 April | APPLY This is an opportunity provided by the Rural Poverty and Agriculture programme: Find out more  Food security is a growing global concern. Food prices are at historic highs. But what is being done by […]

Related Post

  • News

Media Literacy Africa #Ethiopia Fact checking

Ayele Addis August 6, 2021August 6, 2021

የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ! በኢትዮጵያ ደረጃ የሚታየው መድረሻውን ያስቀመጠ የሀሰተኛ መረጃ ሻሞ ወይም እርባታ ሕዝብን እንደ ዋዛ እያሳከረ፣ አገርን ለአደጋ የሚዳርግ፣ ታስቦበት፣ በዕቅድ፣ በባለሙያ፣ በበጀት፣ በድርጅት፣ በመሪ፣ በሥልጠና የሚከናወን የዘመኑ የዲጂታል ጦርነት ነው። ሰሞኑን የፓሪስ ከተማ ክፉኛ ተንጣ ነበር። የናጣት በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ አንድ ሐሰተኛ መረጃ ሲሆን፣ መረጃው “የፓሪስ ውሃ ተመርዟልና አትጠጡ” የሚል […]

  • News

Call for Papers for the Africa Media and Communication International Conference

Ayele Addis January 15, 2021May 26, 2021

The Africa Media Development, Africa Union, ARMA Media Production, and Amhara Region Media and Journalists Association  are pleased to announce its 1st National Conference under a main theme “Ethiopian Media Current Statius, History, Challenges and Continuity” to be held on April 25 & 26, 2021 at Bahir Dar, Ethiopia. The objective of this conference is […]

  • News

Disinformation Misinformation Mal-information Fact Checking Ethiopia : Media Literacy Ethiopia

Ayele Addis August 6, 2021August 6, 2021

የሐሰት ዜናዎች የሐሰት ዜናዎች ጉዳይ (በተለይ ደግሞ በሶሻል ሚዲያ) አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሰዎች የዜና ምንጮችን ሳያጣሩ በመጻፍ እና በማጋራታቸው ምክንያት ብዙ ችግሮች ተፈጥረዋል። ሰዎች በሐሰት ዜናዎች ተጣልተው ለመፈናቀል ደርሰዋል። ብዙዎች የአእምሮ ሰላማቸውንም አጥተዋል። መንግሥትም ቢሆን የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት የተለያዩ የውይይት መድረኮችን እና ፓናሎችን ከማዘጋጀት አልፎ፥ በሚዲያ የሚሠራጩ ዜናዎችን ይዘት በተመለከተ ሕግ እያዘጋጀ መሆኑን እየሰማን […]

About Us

Useful Links

  • Privacy Policy
  • ቆንጆዋን ኢትዮጲያ ይጎብኙ
  • Status
  • የሥራ ማስታወቂያ

Subscribe

  • TOP STORIES
  • TOP VIDEOS
  • Job Vacancy
  • Scholarship
Copyright © 2022 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት. All rights reserved. | Theme: Blook By Themeinwp. | Powered by WordPress