የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን አክሽን (Ethiopian Mass Media Action- EMMA) ‹‹የኢትዮጲያ ሚዲያዎችን የለውጥ ጉዞ›› (Ethiopian Media Changes and Continuity) በሚል ጭብጥ ላይ ባተኮረው ሐገር አቀፍ የጥናት እና ምርምር አብራችሁን እንድትሰሩ እና በኢትዮጵያ ሚዲያ የፖሊሲ ማዕቀፍ ተጠቃሽ የሆነ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ ስለመጠየቅ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን አክሽን (Ethiopian Mass Media Action- EMMA) ከተጣለበት ሐገራዊ ኃላፊነት በመነሳት የባለሙያውን፣ የዘርፉን ተቋማዊ ስራዎችበጥናት እና ምርምር ላይ ተመስርቶ ውጤታማ የመገናኛ ብዙሐን ትስስር ለመፍጠር በማለም በሐገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራማሪዎች ለዶክትሬት ማሟያ እና ገለልተኛ ተቋማት የሀገሪቱን ፊፎርም ለማገዝ የሰሯቸውን ጥናቶች ያካተተ የምርምር ህትመት መፅሄት ጥራት እና ደረጃ በጠበቀ ፣ ፖሊሲዎቻችሁን ባከበረ መልኩ የተመረጡ ፅሁፎችን በማቅርብ ተገቢውን ግምገማ ፣ አሰተያየት በመቀበል በጆርናላችሁ ህትመት ሽፋን እንዲያገኝ በማድረግ እና ከመጋቢት 25-30/2013 ዓ.ም በበባህር ዳር በሚዘጋጀው ሐገር አቀፍ የምርምር አወደ ጥናት ለህትመት አውደ ጥናት የሚቀርቡ ፅሁፎችን በአማርኛ ወይም በእንግሊዘኛ እነድትልኩ ይጋብዛል፡፡፡፡
‹‹የኢትዮጲያ ሚዲያዎችን የለውጥ ጉዞ›› (Ethiopian Media Changes and Continuity) አውደጥናት የምርምር ስራው ሙሉ ሽፋን https://am.africanewschannel.org ብቻ የሚያገኝ ቢሆንም‹ የዚህ የትምህርት ተቋማት፣ ገለልተኛ የምርምር ተቋማት፣ የፖሊሲ አውጭዎች፣ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የሚዲያ ፖሊሲ ተኮር አወደጥናት በተለያዮ ሰፊ የብሮድካስት፣ የህትመት እና የኦንላየን ሚዲያዎች ሽፋን ያገኛሉ፡፡ በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC)፣ በአማራ ቴሌቪዥን (ATV)፣ በጀርመን ድምፅ ራዲዮ (DW)፣ ቮይስ ኦፍ አሜሪካ (VOA), EBS በሌሎችም ራዲዮ ጣቢያዎች፣ በአዲስ አድማስ፣ ሪፖርተር ጋዜጦች እና በሌሎችም ሚደያዎች ሽፋን ያገኛል፡፡
በተለይም በአፍሪካ ኒውስ ቻናል (Africa News Channel) https://www.africanewschannel.org/category/education/journal/ የጆርናል ህትመት ገፅ የወጡት ጥናቶች የእናንተን ጆርናል ኢንዴክስ በማደረግ ሙሉ ሽፋን እንደሚሰጣቸው ስምምነት ላይ ደርሳናል፡፡
· በመሆኑም ፣ በዚህ በ2020 የኢትዮጵያ ሚዲያ ፖሊሲ አትኩረቶች
· የኢትዮጵያ የለወጥ ገፆች ከአብይ አህመድ የስልጣን ዘመን በኃላ
· የኢትዮጵያ ሚዲያ ተቆጣጣሪዎች እና የቁጥጥር መንገዶች
· የኢትዮጵያ ሚዲያ ፖለቲካል ኢኮኖሚ እና አይዲዎሎች ቅርጾች
· የኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪክ
· የኦን ላየን ሚዲያ እና የፖለቲካ አክቲቪዝም ገፅታ
· በጥላቻ ንግግር እና የሃሰት መረጃዎች በኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች እና መከላከያ መንገዶች
· የልማታዊ ሚደያ ዘገባዎች እና ሌሎችም ላይ አተኩረዋል፡፡ ይህ የተሰናሰለ ረጅም ጊዜ የወሰደ እና ለሀገር ትልቅ ሚና የሚኖራቸው እነዚህን የጥናት ውጤቶች ከእናንተ ጋር በመቀናጀት የኦንላየን የህትመት ሽፋን ስናዘጋጅ፣ እንደባለድርሻነታችሁ የጥናቱ ቁልፍ ንግግር ፣ ዋና መግቢያ ፣ ማጠቃላየ እና አውንታዊ ሃሳቦችን በመገምገም በጆርናል ዋና አርታኢዎቹ በአውደ ጥናቱ መክፈቻ እና መዝጊያ ላይ ይጠበቃል፡፡
በመሆኑም ይህ በቀጣይ አመታትም በትብብር እና በቅንጅት የሀገራችንን ለውጦች በጥናት ምርምር እያገዝን ተደራሽነታቸውን በትብብር እያሰፈን ፣ ሙያዊ አሰተሳሰብን ለማዳበር በምናደርገው ጥረት አጋርነታችሁ እና ቀና ትብብራችሁ እንደማይለየን እንተማመናለን፡፡
Send your abstract: radioethiopia81@gmail.com
Call for Papers for the Africa Media and Communication International Conference
The Africa Media Development, Africa Union, ARMA Media Production, and Amhara Region Media and Journalists Association are pleased to announce its 1st National Conference under a main theme “Ethiopian Media Current Statius, History, Challenges and Continuity” to be held on April 25 & 26, 2021 at Bahir Dar, Ethiopia. The objective of this conference is […]